በኢትዮጵያ ሕገመንግሥታዊ ጉዳዮች ላይ የተሰበሰበው የሕዝብ አስተያየት ምን አመለከተ? Leave a comment


አፍሮ ባሮሜትር በአውሮፓዊያኑ የጊዜ ቀመር 1999 ነው የተቋቋመው። ዋና መቀመጫውን ደግሞ ጋና መዲና አክራ ላይ አድርጓል።

በመጀመሪያው ዙር ላይ 12 አገራት ውስጥ ነበር ሥራውን የጀመረው። አሁን ዘጠኝ ዙር ላይ ደርሷል። የሚሸፍናቸው አገራት ቁጥርም አርባ ደርሰዋል።

ተቋሙ በሚንቀሳቀስባቸው አገራት የሕዝብን አስተያየት በመሰብሰብ ለፖሊሲ እና ለሕግ አውጪዎች፣ ለውሳኔ ሰጪዎች እንዲሁም ደግሞ ፕሮግራሞች እና ፕሮጀቶችን ለሚቀርጹ አካላትተጨባጭ እና ተዓማኒ መረጃእንደሚሰጥ ይገልጻል።

አፍሮ ባሮሜትር በየአገሩ 12 ርዕሰ ጉዳዮችን ይዳስሳል። አንዳንዴ ደግሞ እንደየአገሩ ሁኔታ የሚመረጡም ይኖራሉ።

የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታን ታሳቢ በማድርግበሁለት ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ ጥናቶች ናቸው የተደረጉትሲሉ በአፍሮ ባሮሜትር የኢትዮጵያ ብሔራዊ አጋር የሆኑት አቶ ሙሉ ተካ ለቢቢሲ ገልጸዋል።

በሁለት ትላልቅ ጉዳዮች ላይም አተኩሯል። የመጀመሪያው ፌደራሊዝም ነው።

ኢትዮጵያ ፌደራላዊ ወይስ የተማከለ (አህዳዊ) የመንግሥት ሥርዓት ያስፈልጋታል? የሚለው ቀዳሚው ተቋሙ የሕዝብ አስተያየት ያሰባሰበት ጉዳይ ነው።

ሁለተኛው ደግሞ በሥራ ላይ ባለው ኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት ላይ ያተኮረ ነው።

በሕገ መንግሥቱ አንዳንድ አወዛጋቢ አንቀጾች ላይ የሕዝቡ አስተያየት ምን ይመስላል የሚለውን ለማየት ተደረገ ጥናት ነበር።

በቅርቡ ከተደረገው ጥናት ጋር የሚመሳሰል ተመሳሳይ ጥናት ከዚህ ቀደም ተካሂዷል። ይህምአሁን በጊዜ ሂደት ያለውን ለውጥ ለማየት የተደረገ ጥናት ነውይላሉ አቶ ሙሉ።

·      

ፌደራላዊ ወይስ የተማከለ አስተዳደር?

ኢትዮጵያ የተማከለ ወይስ ፌደራላዊ አስተዳደር ያስፈልጋታል የሚለው ላይ በተሰበሰበ የሕዝብ አስተያየት “54 በመቶ የሚሆነው አስተያየት ሰጪ ኢትዮጵያዊ የፌደራል የመንግሥት ሥርዓት እንዲኖራት ምርጫውን ሰጥቷል።

ይህ ቁጥር 2020 ከተደረገው የጥናት ውጤት ጋር ሲነጻፈርያኔ 61 በመቶ ነበር፤ አሁን በሰባት ነጥብ ዝቅ ብሎ እናገኘዋለንይላሉ አቶ ሙሉ።

42 በመቶዎቹ ደግሞ የተማከለ የመንግሥት ሥርዓትን መርጠዋል።እነዚህ ደግሞ 2020 ከተደረገው አንጻር አምስት በመቶ ጭማሪ ያለው ነው።

ከዚሁ ጋር ተያይዞ የቀረበው ጥያቄ ኢትዮጵያ ፌደራላዊ ሥርዓትን የምትከተል ከሆነ ምን ዓይነት የፌደራል ሥርዓት ትከተል? የሚል ነው።

አሁን እንዳለው ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ላይ የተመሠረተ ይሁን ወይስ በመልክዓ ምድራዊ አቀማመጥ ላይ የተመሠረተ ወይስ ሌሎች ነገሮችን ታሳቢ በማድረግ የሚቀረጽ ይሁን የሚል ጥያቄ ቀርቧልይላሉ አቶ ሙሉ።

የፌደራላዊ ሥርዓቱ በብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ላይ የተመሠረተ ይሁን የሚሉት 49 በመቶ ሆነዋል ብሏል አፍሮ ባሮሜትር የሰበሰበው የሕዝብ አስተያየት። በመልክዓ ምድር ላይ ይመሥረት ያሉት ደግሞ 48 በመቶ ናቸው።

ይህ ጥያቄ በከተማ እና በገጠር ነዋሪዎች ዘንድ ያለውን አስተያየትን በተመለከተም የከተማ ነዋሪዎች በመልክዓ ምድር ላይ የተመሠረተ ፌደራላዊ ሥርዓትን ሲመርጡ (54 በመቶው) በገጠር አካባቢዎች ደግሞ ብሔሮችን፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች መሠረት ያደረገው ፌደራላዊ ሥርዓትን ይምርጣሉ (51 በመቶ) ብሏል አፍሮ ባሮሜትር በጥናቱ መሠረት።

አሁን ተሰብስቦ ይፋ በተደረገው የአፍሮ ባሮሜትር የሕዝብ አስተያየት መለኪያ መሠረት 2020 ከተደረገው አንጻር ሲታይ አገሪቱ ሊኖራት ይገባል ተብሎ በሕዝቡ ዘንድ ከሚታሰበው የፌደራላዊ ሥርዓት አወቃቀር አንጻር ብዙም ለውጥ ያልታበት ሆኗል።

ሕገ መንግሥቱ እና አንቀጽ 39

አፍሮ ባሮሜትር ሦስት አስርት ዓመታን ሊያስቆጥር በተቃረበው የኢትዮጵያ በሕገ መንግሥት ውስጥ ዋነኛ ጉዳዮች በሚባሉት ዙሪያም የሕዝቡን አስተያየት የሚለኩ ጥያቄዎችን አቅርቧል።

በሕገ መንግሥቱ ውስጥ ከተካተቱ ጉዳዮች መካከል ለአስርታት የልዩነት ነጥቦች በሆኑ አንቀጾች ላይ በተሰበሰበው የሕዝብ አስተያየት የተለያዩ ሐሳቦች ተንጸባርቀዋል። ከሕገ መንግሥቱ ወነኛ አነጋጋሪ ጉዳዮች ከሆኑት መካከል የአንቀጽ 39 ጉዳይ ቀዳሚው ነው።

አቶ ሙሉ እንደሚሉትበፖለቲከኞች ስምምነት ያልደረሱበት የአንቀጽ 39
ጉዳይ ልክ እንደ እንደ ፖለቲከኞቹ ሁሉ በአስተያየት ሰጪዎች ዘንድም ስምምነት የለም። በዚህ አንቀጽ ላይ አስተያየት ሰጪዎች እኩል በሚባል ሁኔታ የድጋፍ እና የተቃውሞ ድምጽ ሰጥተዋል።

በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 39 ላይ የሠፈረው አንቀጽ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች የራሳቸውን ዕድል በራሳቸው የመወሰን ገደብ አልባ መብት ያላቸው መሆኑን እና ይህ ራሳቸውን ከፌዴሬሽኑ ገንጠለው ነፃ አገር እስከመመሥረት የሚደርስ እንደሆነ ይታወቃል።

በዚህ ዙሪያ ለዓመታት በተደረጉ ክርክሮች ሕገ መንግሥቱ በአገሪቱ ውስጥ መብቶች እንዲከበሩ በማድረግ በጋራ የሚኖርበት አገር መገንባት እንጂ የመለያየት ሐሳብ ማንጸባረቅ የለበትም የሚሉ እንዳሉ ሁሉ፣ ሌሎች ደግሞ አንቀጹ የሕዝቦች መብት ማስከበሪያ ዋስትና ነው በማለት ሲደግፉት ቆይተዋል።

አፍሮ ባሮሜትር ባሰባሰበው የሕዝብ አስተያት መለኪያ ላይም ይህ ጉልህ ልዩነት እንደተንጸባረቀ አቶ ሙሉ ገልጸዋል። በዚህም መሠረት ከፊሉ አስተያየት ሰጪ አንቀጽ 39 ከሕገ መንግሥቱ እንዲወጣ ሲፈለግ፣ ቀሪው ደግሞ ባለበት እንዲቀጥል እንደሚሻ ፍላጎቱን አሳውቋል።

ከዚህ አንጻር አንቀጹ ከሕገ መንግሥቱ እንዲነሳም ሆነ ባለበት እንዲጸና አስተያየት ከሰጡት ሰዎች መካከልብልጫ ያለው ወገን የለም። እኩል በሚባል ደረጃ የተቃዋሚው እና የደጋፊው መጠን የተቀራረበ ነውሲሉ ገልጸዋል።

እንደ አፍሮ ባሮሜትር ጥናት ከሆነ 67 በመቶ የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን ሕገ መንግሥቱ እንዲሻሻል ይፈልጋሉ። 16 በመቶዎቹ በአዲስ እንዲቀየር የሚፈልጉ ሲሆኑ 16 በመቶዎቹ ደግሞ ባለበት እንዲቀጥል ፍላጎታቸውን መሆኑን አሳይተዋል።


የሥልጣን ዘመን ገደብ

አፍሮ ባሮሜትር የሕዝብ አስተያየት ከሰበሰበባቸው ሕገ መንግሥታዊ ጉዳዮች መካከል የአገሪቱ መንግሥት ከፍተኛ አመራር የሆኑት የጠቅላይ ሚንስትሩ የሥልጣን ዘመን መገደብ ጉዳይ አንዱ ነው።

በኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት መሠረት የአገሪቱ ርዕሰ ብሔር የሆኑት ፕሬዝዳንት የሥልጣን ጊዜ በሁለት የሥራ ዘመን ሲገደብ፤ የጠቅላይ ሚንስትሩ የሥልጣን ቆይታ ጊዜ ግን ገደብ የለውም።

66 በመቶ አስተያየት ሰጪዎች የጠቅላይ ሚንስትሩ የሥልጣን ዘመን እንዲገደብ ፍላጎት እንዳላቸው አመልክተዋል።በዚህ ጉዳይ ላይ ሁለት ሦስተኛ የሚሆኑ አስተያየት የሰጡ ኢትዮጵያውያን የጠቅላይ ሚንስትሩ የሥልጣን ዘመን እንዲገደብ ይፈልጋሉ።

የፌደራል መንግሥቱን የሥራ ቋንቋን በተመለከተም በተሰበሰበው አስተያየት የተገኘው ውጤት ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው አስተያየት ሰጪዎች ተጨማሪ ቋንቋ እንዲካተት እንደሚፈልጉ አሳውቀዋል።

ከፌደራሉ መንግሥት የሥራ ቋንቋ ከሆነው አማርኛ ሌላ ተጨማሪ ቋንቋ ለፌደራሉ መንግሥት ያስፈልጋል የሚሉ አስተያየት ሰጪዎች ብዛት 67 በመቶ ነው። 2020 በተደረገው ላይ ቁጥሩ 69 በመቶእንደነበረ አቶ ሙሉ ያስታውሳሉ።

ሌላው በሕዝብ አስተያየት መለኪያው ጥናት ውጤት ላይ ከተካተቱ አነጋጋሪ ከሆኑ ጉዳዮች መካከል የዋና ከተማዋ የአዲስ አበባ ጉዳይም ተካቷል።

አቶ ሙሉ “53 በመቶቹ አዲስ አበባ እንደ ሌሎች የአገሪቱ ክልሎች ሁሉ ራሷን የቻለች ክልል ሆና የፌደሬሽኑ አባል እንዲሆን ይፈለጋሉ። ይህ 2020 ከተመዘገበው 18 በመቶ ከፍ ብሎ ታዝበነዋልብለዋል።

የትኞቹ ጉዳዮች ላይ ያተኩራል?

አፍሮ ባሮሜትር በተለያዩ ዙሮች 12 ‘ትልልቅርዕሰ ጉዳዮች ላይ የሕዝብ አስተያየትን መሠረት በማድረግ ጥናቶችን ያከናውናል።

በዲሞክራሲ፣ በአስተዳደር፣ በብሔርተኝነት፣ በማኅበረሰብ፣ በዜግነት፣ በምጣኔ ሃብት፣ በሕዝብ አገልግሎት እና በመሳሰሉ ላይ ኢትዮጵያን ጨምሮ 40 አገራት ውስጥ ጥናቶችን ያከናውናል። በተጨማሪም ደግሞ እንደየአገሩ ሁኔታ አከራካሪ በሆኑ ጉዳዮች ላይም የተለዩ ጥናቶችን ይሠራል።

የዚህ ዓላማምየአፍሪካውያን ዜጎች ድምጽ የፖሊሲ ውሳኔ አሰጣጥ አምድ እንዲሆን ነውየሚሉት አቶ ሙሉ፣ ጥናቶቹ ውሳኔ ሰጪዎች፣ ሕግ አውጪዎች፣ ፖሊሲ እና ፕሮግራም የሚቀርጹ አካላት እንዲሁም አጋሮችየሕዝቡን ፍላጎት ታሳቢ አድርገው በመረጃ ላይ የተመሠረተ ሥራ እንዲሠሩ የሚያግዝ ግብዓት በማቅረብ ማገዝ ነውይላሉ።

ለዚህም አፍሮ ባሮሜትር የሕዝብ አስተያየትን በመሰብሰብ የሚያገኛቸውን ውጤቶችን እና አሃዛዊ መረጃዎችን እየተነተነ ማቅረብ፣ ወይይቶችን ማዘጋጀት የተገኙ ውጤቶችን ያሰራጫል።

በተጨማሪም እነዚህን መረጃዎች የሚመለከታቸው አካላት በሚያከናውኗቸው ሥራዎች ውስጥ ሁሉ ታሳቢ እንዲያደርጉትም ክትትል እንደሚያደርጉም አቶ ሙሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል።

ናሙናዎቹ ምን ያህል ወካይ ናቸው?

በሕዝብ አስተያየት ጥናት ላይ ምን ያህል ናሙናው ሕብረተሰቡን ይወክላል የሚለው ትልቅ ቦታ ይሰጠዋል። የናሙና ወካይነት ሲነሳ መታሰብ ያለበት የኢትዮጵያ ሕዝብ አሰፋፈር እና ባህሪ መሆኑን አቶ ሙሉ ይናገራሉ።

በአፍሮ ባሮሜትር ጥናት ውስጥ የሚሰበሰበው ናሙና በአገራቱ ውስጥ በገጠር እና በከተማ አካባቢዎች ያሉትን ነዋሪዎች ፍላጎት እና አስተያየት የሚያንጸባርቅ መሆኑን አቶ ሙሉ ገልጸዋል።

ተቋሙ በኢትዮጵያ ውስጥ ባካሄደው በዚህ አገር አቀፍ ጥናት ሁሉንም የአገሪቱን ክፍሎች የሚያካትት እንዲሆን ቀደም ሲል የነበሩትን 11 ክልሎችን እና ሁለት የከተማ መስተዳደሮችን አካቷል።

ናሙናው የተደለደለው በሕዝብ ብዛት መሠረት መሆኑን አቶ ሙሉ አነስተዋል። በዚህም ብዙ የሕዝብ ቁጥር ያለው ክልል ትልቁን የናሙና ድርሻ ይወስዳል ማለት ነው።

ናሙናው ከጾታ ስብጥር አንጻርም ለወንዶች እና ለሴቶች በመቶኛ እኩል 50 በመቶ 50 በመቶ ድርሻን ሰጥቶ አስተያየት መሰብሰቡን ይናገራሉ።

የኢትዮጵያ ሕዝብ የተለያየ ነው። ይህ ናሙናም ብዝሃነት እንዲኖረው አድርገናል። ይህንንም በጥናታችን ላይ እንዲጸባረቅ አድርገናል። ናሙናችን በዚህ ምክንያት በአገር አቀፍ ደረጃ ወካይ ነው እንላለንብለዋል።

ናሙናው የተወሰደው ከግንቦት 18 እስከ ሰኔ 15 ቀን 2015 . ድረስ ነው።

ጥናቱ የተደረገው በዘፈቀደ ናሙና የመሰብሰብ ዘዴ (ራንደም ሳምፕሊንግ) ሲሆን፣ ናሙናዎቹም በአገሪቱ ማዕከላዊ የስታቲስቲክስ መረጃ መሠረት ወካይ እንደሆኑ ተደርገው የተመረጡ ናቸው።

ራንደምሊ ሲመረጡ የተወሰኑ ግጭት ያለባቸው ጣቢያዎች ገጥመውናል። ወደ አንድ በመቶ የሚሆን የናሙና አካል ማለት ነው። ግጭት እያለ ነጻ ሆነው አስተሳሰባቸውን መግለጽ ስለማይችሉ ለዚያች ብቻ አዲስ ዕጣ በማውጣት ተተክቶ ጥናት ተደርጓል። አጋጣሚ ሆኖ 99 በመቶ ናሙናችን የነበረው ብዙ ግጭት በሌለባቸው አካባቢዎች ነበርሲሉ ግጭት ባለባቸው አካባቢዎች በምን መልኩ ናሙናዎችን እንደወሰዱ ገልጸዋል።

ውጤቱን ማን ይጠቀምበታል?

አፍሮ ባሮሜትር ኢትዮጵያ ውስጥ ያከናወነው ይህ ጥናት ሦስተኛው ነው።

2020 ለሚመለከታቸው አካላት የሰጧቸው ጥናት ግኝቶችን የፖለቲካ ፓርቲዎች በተለይ ፕሮግራሞቻቸውን ለመከለስ ተጠቅመውበታል ብለዋል።

የፌደራል እና የተማከለ የመንግሥት አስተዳደርን እንደ መርኅ የሚያራምዱ የፖለቲካ ፓርቲዎች እና ድርጅቶች ቁጥሩን በመመልከት አብዛኛው ሕዝብ ወደ እነሱ አስተሳሰብ እንዲመጣ በተወሰነ ደረጃም ቢሆን ጥቅም ላይ ሲያውሉት ተመልክተናልብለዋል አቶ ሙሉ።

የአሁኑንም ይመለከቷቸዋል ላሏቸው አካለት ካለፈው ጋር እንዲያነጻጽሩት የግኝት ውጤታቸውን ሰጥተዋቸዋል።

በሚቀጥለው ውጤቱን ለፌደሬሽን ምክር ቤት እና ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንሰጣለን። በቀጣይ የሚኖረው (ተጽዕኖ) አብረን እናያለን። 2020 በነበረው ከቀጠለ ግን ብዙ ጉዳዩ የሚመለከታው የማኅበረሰብ አካላት የማስተማሪያ ግብዓቶቻቸውን አስተካክለው ሕዝቡ ወደ እነሱ እንዲመጣ ሲሠሩ አስተውለናልብለዋል።

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Cart

Your Cart is Empty

Back To Shop

የሚፈልጉትን ይዘዙን

Order what you want