በሴራሊዮን የተፈፀመው ጥቃት የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ እንደ ነበር ባለሥልጣናት ተናገሩ Leave a comment

29 ህዳር 2023

እሑድ ዕለት በሴራ ሊዮን መዲና በሚገኙ ተቋማት ላይ የተፈፀመው ጥቃት የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ እንደነበር የአገሪቷ መንግሥት አስታወቀ። የማስታወቂያ ሚኒስትሩ አርኖህ ባህ ክስተቱ በዴሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጠን መንግሥት ለመገልበጥ እና ከሥልጣን ለማስወገድ የተደረገ የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ መሆኑን ተናግረዋል። ጥቃት ፈጻሚዎቹ የጦር ተቋማትን እና እስር ቤቶችን ላይ ጥቃት ያደረሱ ሲሆን 2 ሺህ የሚጠጉ እስረኞችን ማስለቀቃቸውንም ባለሥልጣናቱ ተናግረዋል።  በጥቃቱ ቢያንስ 19 የጸጥታ ኃይሎችና ሰላማዊ ሰዎች ተገድለዋል።ሙከራው ከሽፏል፤ በርካታው የመፈንቅለ መንግሥት መሪዎቹ በፖሊስ ቁጥጥር ሥር አሊያም በሽሽት ላይ ናቸው። ያመለጡትን ለመያዝ እና ለሕግ ለማቅረብ እንሞክራለንብለዋል ሚኒስትሩ። ከጥቃቱ ጋር በተያያዘም አስራ ሦስት የጦር መኮንኖች እና አንድ ሰላማዊ ግለሰብ መታሰራቸውንም ባህ ጨምረው ተናግረዋል። ምንም እንኳን ሰኞ ዕለት ከተማዋ ወደ መረጋጋት ብትመለስም በአጎራባቿ ከተማ ሙራይ ተኩስ ነበር ፖሊስ ተኩሱ ጥቃት ፈጻሚዎቹን ወደ ሕግ ለማቅረብ እየተካሄደ ያለው ዘመቻ አካል መሆኑን ገልጿል። የፖሊስ መኮንኖቹ በዚህ የተኩስ ልውውጥ የተጎዳ አካል እንደሌለ ገልጸው፣ ተጠርጣሪዎች ግን መያዛቸውን ተናግረዋል። ጥቃቱን ተከትሎ በመላ አገሪቷ ከእሑድ ጠዋት ጀምሮ የሰዓት እላፊ ተጥሏል።

ወታደሮችሴራ ሊዮንን ነጻ ለማውጣትእቅድ እንዳላቸው ሲገልጹ እንደነበር ቢቢሲ መታዘብ ችሏል። ጥቃት ፈጻሚዎቹ በፕሬዚደንቱ መኖሪያ አቅራቢያ የሚገኘውን የጦር መሥሪያ ቤት በመውረር ከወታደሮች መሣሪያ ለመንጠቅ ሙከራ አድርገዋል። በመዲናዋ የሚገኘውን ዋና እስር ቤት ሰብረው መግባታቸውንም የማስታወቂያ ሚኒስትሩ ተናግረዋል። በማኅበራዊ ሚዲያ የተጋሩ ተንቀሳቃሽ ምስሎችም እሑድ ዕለት ከፍሪታውን ከተማሴንትራል ፓዴማ ሮድከተሰኘው እስር ቤት በርካታ ሰዎች ሲያመልጡ አሳይተዋል። እስካሁን 23 እስረኞች ተይዘው ወደ እስር ቤቱ መመለሳቸውን የእስር ቤቱን ባለሥልጣናት ጠቅሶ ሮይተርስ የዜና ወኪል ዘግቧል። ሴንትራል ፓዴማ ሮድእስር ቤት አምልጠው የነበሩ 23 እስረኞች መልሰው በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ሪፖርቶች አመልክተዋል። ባለፈው ሰኔ ወር ላይ ፕሬዚዳንት ጁሊየስ ማዴባ ለሁለተኛ ጊዜ አገሪቱን ለመምራት በሰኔ ወር የተደረገውን ምርጫ አሸንፌያለሁ ማለታቸውን ተከትሎ በሴራ ሊዮን የፖለቲካ ውጥረት ነግሷል። የምርጫው ውጤት በተፎካካሪያቸው ውድቅ የተደረገ ሲሆን አሜሪካ እና አውሮፓ ኅብረትን ጨምሮ በዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ጥያቄ አስነስቷል።

በነሐሴ ወር በርካታ ወታደሮች ፕሬዚዳንቱን በመፈንቅለ መንግሥት ለመጣል አሲረዋል በሚል በቁጥጥር ስር ውለው ተከሰዋል። እሑድ ዕለት የተፈፀመውን ጥቃት ተከትሎም የምዕራብ አፍሪካ የኢኮኖሚ ማኅበረሰብ (ኢኮዋስ) በሴራ ሊዮን ያለውን ጸጥታ ለማጠናከር ቀጠናዊ ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን ገልጿል።  በተመሳሳይ የናይጄሪያ ብሔራዊ የጸጥታ አማካሪ ማላመ ኑሁ ሪባዱ፣በሴራ ሊዮን ዲሞክራሲን፣ ሰላምን፣ ጸጥታን እና መረጋጋትን ለማደናቀፍ የሚደረግ ማንኛውም ጥረት በኢኮዋስም ሆነ በናይጄሪያ ተቀባይነት የለውምሲሉ አስጠንቅቀዋል። በቅርብ ጊዜ የተፈፀሙ መፈንቅለመንግሥቶችን ተከትሎ በርካታ የምዕራብ እና ማዕከላዊ አፍሪካ አገራት በወታደራዊ አስተዳደር ሥር ይገኛሉ።  ከእነዚህ መካከል የሴራ ሊዮን ጎረቤት የሆኑት ጊኒ እና ማሊ እንዲሁም ኒጀር እና ቻድ ይገኙበታል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Cart

Your Cart is Empty

Back To Shop

የሚፈልጉትን ይዘዙን

Order what you want