ግራናዳ ከቢልባዎ የሚያደርጉት ጨዋታ ተመልካች በመሞቱ ምክንያት ተቋረጠ Leave a comment

በስፔን ሊጋ ግራናዳ ከአትሌቲክ ቢልባዎ የሚያደርጉት ጨዋታ የአንድ ተመልካች ሕይወት በማለፉ ምክንያት ተቋርጧል። በኑዌቮ ሎስ ካርሜኔስ ስታድየም የነበረው የላ ሊጋ ጨዋታ ሰኞ ዕለት ከተቋረጠበት እንደሚቀጥል ተሰምቷል። እሑድ ዕለት የነበረው ጨዋታ 17 ደቂቃ በኋላ የተቋረጠው አንድ ተመልካች የልብ ሕመም አጋጥሞት ከወደቀ በኋላ ነው። የጤና ባለሙያዎች ግለሰቡን ለማዳን ጥረት ሲያደርጉ ቆይተዋል። ጨዋታው ከአንድ ሰዓት ቆይታ በኋላ ተቋርጦ ተመልካቾች ወደቤታቸው እንዲመለሱ ተነግሯቸዋል።

ቢልባዎ 1-0 እየመራ ሳለ የተቋረጠው ጨዋታ ሰኞ ምሽት 5 ሰዓት 17ኛው ደቂቃ ጀምሮ በተመሳሳይ ውጤት እንደሚቀጥል ሊጋ ጠቁሟል። የሰንበቱን ጨዋታ ለማየት ቲኬት የቆረጡ ተመልካቾች ወደ ስታድየም መግባት ይችላሉ። ግራናዳ እግር ኳስ ክለብ ለሟችቤተሰቦችና ወዳጆች እንዲሁም ለመላው የግራናዳ ቤተሰብ መፅናናትን እንመኛለንብለዋል።

የአትሌቲክ ቢልባዎ ግብ ጠባቂ ኡናይ ሲሞን ደጋፊው እርዳታ እንደሚሻ በመጠቆሙ በግራናዳ ደጋፊዎች አድናቆት ተችሮታል። የሁለቱ ክለቦች ተጨዋቾች ጨዋታው ከተቋረጠ በኋላ 20 ደቂቃ ያክል ጠብቀው ወደ መልበሻ ክፍል እንዲገቡ ተደርገዋል። በሌላ የላ ሊጋ ጨዋታ የዘንድሮው ክስተት ጂሮና ወደ ባርሴሎና አቅንቶ ሶስት ነጥብ ይዞ ተመልሷል።

ጂሮና ወደ ካምፕ ሄዱ ባርሴሎናን በሜዳው 4-2 በመርታት የሊጉ አናት ላይ ተቀምጧል። ሊጋውን ጂሮና 41 ነጥብ ሲመራ፤ ሪያል ማድሪድ 39 ሁለተኛ፣ አንድ ተስተካካይ ጨዋታ አትሌቲካ ማድሪድ 34 ነጥብ ሶስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል። ባርሴሎና በጎል ድርሻ ተበልጦ በተመሳሳይ 34 ነጥብ ከአትሌቲኮ ዝቅ ብሎ አራተኛ ደረጃን ይዟል። አትሌቲክ ቢልባዎ ስድስተኛ ደረጃ ላይ ሲገኝ ግራናዳ አስራ ዘጠነኛ ደረጃን ይዞ ወራጅ ቀጣና ይገኛል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Cart

Your Cart is Empty

Back To Shop

የሚፈልጉትን ይዘዙን

Order what you want