በኦንላይን ስራ “በ9 ወር ሚሊየነር ሆኛለሁ” የሚለው ኢትዮጵያዊው ወጣት Leave a comment

ናትናኤል እናቱእንጀራ ይውጣልህብለው መርቀውታል። የማይሞክረው ነገር የለም። የማይገናኙ የሚመስሉ ሥራዎችን ይሠራል። የእንጨት ሥራ፣ ሙዚቃ ማጫወት (ዲጄ) ቪዲዮ ኤዲቲንግ፣ ግራፊክስ እና ዲዛይን፣ ዳንስ ማሠልጠን እና ዲሽ መግጠም ያውቅበታል። የእናቱ ምርቃት ደርሶ እንጀራ የወጣለት ግንበኦን ላይን ቢዝነስ’ [በኢንተርኔት አማካይነት የሚሠራ ሥራ] ይመስላል።  በዚህ ሥራ በዘጠን ወራት ውስጥ 1.2 ሚሊዮን ብር በላይ ማግኘት እንደቻለ ይገልጻል።

ናትናኤል ተፈሪ ሥራን እጅግ ይወዳል። ያለ ሥራ መቀመጥ አይፈልግም። አባቱ በጠና ሲታመሙ ግን እርሳቸውን ለማስታመም ሥራ ማቆም ግድ ሆነበት።  ሥራ ከጀመረባት ባሕር ዳር ወደ አዲስ አበባ ተመለሰ። በዚህ መካከል፣ ጓደኛው ቤት ሆኖ ሊሠራበት የሚችለውን ድረ ገጽ ጠቆመው። ይህ ድረ ገጽአፕወርክ’ (up work) ይሰኛል። አፕወርክበዓለም ዙሪያ ያሉ ሥራ ፈላጊዎች ከአሠሪዎች ጋር ይገናኛሉ። እዚህ ላይ ያሉ ሥራዎችንእሠራቸዋለሁ ብዬ ካሰብኩ ፕሮፖዛል እልክላቸዋለሁ። አሪፍ አድርጌ መሥራት እንደምችል ያመኑበት ሰዎች ያናግሩኛልሲል ይጠቅሳል ናትናኤል። ናትናኤል የመጀመሪያው ሥራውን ያገኘው ከለንደን ነበር። እዚያ ያለ አንድ ደንበኛ በድረገጹ አማካኝነት አጫጭር ቪዲዮዎችንኤዲትየሚያደርግለት ሰው ሲፈልግ ነበር። ናትናኤል ይህንን ሥራ መሥራት እንደሚችል አመነ። ከሰውዬው ጋር ተጻጻፉ፣ ሥራውን መሥራት እንደሚችል አሳመነው።

ሥራው ደንበኛው ቀርጾ የላከውን የማስተማሪያ ቪዲዮ ኤዲት ማድረግ እና ተጨማሪ የምሥል መረጃዎችን አካቶ መልሶ መላክ ነው። ናትናኤል አፕወርክ፣ ሊንክዲን እና ፋይቨር በተባሉ ድረገጾች አማካኝነት ሥራ ያገኛል ለዚህ ሥራ መነሻ ገንዘብ አላስፈለገውም።አስተማማኝየሆነ ኮምፒውተርም ሆነ ኢንተርኔት አልነበረውም።ዩኒቨርሲቲ ስገባ በገዛሁት በተሰበረ፣ በሚንቀራፈፍ እና አሮጌ በሆነ ላፕቶፕ ነበር የጀመርኩትይላል። ኢንተርኔት ለማግኘት ደግሞዋይፋይ ያላቸው ሰዎች ቤት ወይም ካፌይሄድ ነበር።

ናትናኤል የመጀመሪያውን ሥራ 40 ዶላር ወይም በዚያን ጊዜ በነበረው ይፋዊ ምንዛሪ 2 ሺህ ብር አካባቢ አግኝቶበታል። እዚህ ጋ፣ ናትናኤል ካገኘው ገንዘብ በላይበጣም ጠቅሞኛልየሚለው ደንበኛው በድረ ገጹ አምስት ኮከብ እና እጅግ አበረታች አስተያየት መስጠቱን ነው። “‘በጣም ግሩም ሥራ ነው። ሌሎችም ከእርሱ ጋር እንድትሠሩ እመክራለሁየሚል አስተያየት ሰጥቶኛል፥ በጣም ነበር ደስ ያለኝይላል። በዚህም ገርበብ ያለው የሥራ ዕድል ወለል ብሎ ተከፈተ።

አሁን አፕ ወርክበተጨማሪፋይቨርእናሊንክዲንበተሰኙ ሥራ ማፈላለጊያዎች አማካይነት በርካታ ሥራዎችን እየሠራ ነው። ከቤቱ መውጣት ሳይጠበቅበት አሜሪካ፣ ስፔን፣ ዩናይትድ ኪንግደም (ዩኬ) እና ዱባይ ያሉ ሥራዎችን እየሠራጠቀም ያለገንዘብ ያገኛል። ከዚያም አልፎ ሦስት ሰዎችን ቀጥሮ ማሠራት ጀምሯል።ባለውለታዬየሚለው እና ሰባራ ላፕቶፑን ከፍተኛ ፍጥነት ባላቸውውድሦስት ኮምፒውተሮች ቀይሯል።  ልብ በሉ! ይህ ሁሉ የሆነው ዘጠኝ ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ነው።

ቢዝነሱ የእኔንም የቤተሰቤንም ሕይወት በሆነ ደረጃ ቀይሮታልየሚለው ናትናኤልበኦንላይን ሥራ ብቻ ምንም ሳላወጣ፣ ከቤቴ ሳልንቀሳቀስ፣ ከአንድ ሚሊዮን ሁለት መቶ ሺህ ብር በላይ ሠርቻለሁ። አሁንም እየሠራሁ ነው። የኢንተርኔት እና የመብራት ችግር ነው እንጂ ከዚህ በላይ እሰራ ነበርሲል ገልጿል። ተከታታይ ሥራ የሚሰጡትን ደንበኞችንም አፍርቷል።አንድ ደንበኛዬ ሀበሻ ነው ከዩኬ መጥቶ ቤተሰቤን ጠይቋል። በርቱ ብሎን ሄዷል። አሁንም አብረን እየሠራን ነውይላል። በድረገጾቹ አማካኝነት ቪዲዮ ኤዲትንግ፣ ግራፊክስ ዲዛይን እና ተንቀሳቃሽ ካርታ (map animation) የሚያሠሩ ደንበኞችን እያገኘ 5 እስከ 1 ሺህ ዶላር ያገኛል። የሚገርመው፣ እነዚህን ሥራዎች በሙሉ ዩቲዩብ እየተመለከተ የተማራቸው ናቸው።

ናትናኤልበኦንላይን ገንዘብ ለመሥራት አንድ ስልክ በቂ ነውይላል።ባለን ካልሠራን ቢኖረንም አንሠራም። ባለን መጀመር አለብን። ስንጥር ነው ፈጣሪ የሚጨመረው። በፊት ዋይፋይ ለማስገባት አቅም አልነበረኝም. . . ዋይፋይ ያለበት ቤት እየሄድኩ፣ ኢንተርኔት ያለበት ካፌ እየሄድኩ ነበር የምሠራውሲል አክሏል። በእነዚህ ሥራ ማፈላለጊያዎች አማካኝነትኮምፒውተር ሳያስፈልገን በቀላሉ መሥራት የምንችላቸው ብዙ ሥራዎችእንዳሉም ይናገራል። ለአብነት፣ አንዳንድ ሰዎች አጫጭር ድምጾች (voice over) እንዲነበብላቸው ድረገጾቹ ላይ ሰው ያፈላልጋሉ። ለዚህ ሥራ የሚያስፈልገው ድምጽ የሚቀርጽ ስልክ ብቻ ነው።

የቀረጽነው ድምጽ ጥሩ ባይሆን እንኳን [ድምጹን] ማስተካከል የሚችሉ ነጻ ድረገጾች (ዌብሳይቶች)” እንዳሉ ይጠቅሳል። ሌሎች ደንበኞች ደግሞ መረጃ የሚያሰባስብላቸው ሰው ሊፈልጉ ይችላሉ። ስልክ እና ኢንተርኔት ያለው ሰው መረጃዎችን ከኢንተርኔት ላይ እየፈለገ ማስገባትም (Data entry) በቀላሉ ሊሠሩ ከሚችሉ ሥራዎች አንዱ ነው።

የኦንላይን ሥራእና አጭበርባሪዎች

ናትናኤል መጀመሪያበኦንላይንገንዘብ የሠራው አፕ ወርክነው። አሁን ከዚያም አልፎበፋይቨርእናሊንክድኢንአማካኝነት ሥራ ያገኛል።አፕወርክበአውሮፓውያኑ 2013 አሜሪካ፣ ካሊፎርኒያ ውስጥ የተጀመረ ሥራ አገናኝ ድረገጽ ነው።ፋይቨርደግሞ 2010 እስራኤል፣ ቴላቪቭ ውስጥ የተመሠረተ ሲሆን፣ 10 ሺዎች ለሚቆጠሩ ሰዎች ሥራ እና ገንዘብ አስገኝቷል።

20 ዓመት በፊት የተጀመረውሊንክዲን እንዲሁ። በእነዚህ ድረገጾች በትርፍ ወይም በሙሉ ጊዜ የሚሠሩ በሺዎች የሚቀጠሩ ሥራዎች አሉ። መሥራት የሚፈልጉ ሰዎች ክህሎታቸውን፣ የሥራ ልምዳቸውን እና ሌሎች መረጃዎችን በእነዚህ ድረገጾች አማካኝነት ይጭናሉ። ተመሳሳይ ገጾቹ ላይ ማሠራት የሚፈልጉ ግለሰቦች ወይም ኩባንያዎችም ይገኛሉ። አሠሪዎች ከሚያወጡት ማስታወቂያ ስር ሥራ ፈላጊዎች የሚያስከፍሉትን የገንዘብ መጠን ያስቀመጣሉ። አሰሪው የሥራ ፈላጊውን መረጃዎች እና የገንዘብ መጠን አይቶያዋጣኛልላለው ሥራውን ይሰጣል።

ይህንን የመሰሉ በርካታ ድረገጾች አሉ። ችግሩ ሁሉም ትክክል አይደሉም አንዳንዶቹ ለቀማኛ አሳልፈው ይሰጣሉ። አንዳንድ አጭበርባሪዎች ደግሞ በትክክለኞቹ ገጽ በኩል ሊመጡ ይችላሉ። አጭበርባሪዎች በሥራ ድረገጾች አማካኝነት ሥራ ፈላጊዎችን ዒላማ እንደሚያደርጉ ቢቢሲ በአንድ ወቅት ያገኘው መረጃ አመልክቷል። ሊንክንዲን ሐሰተኛአሰሪ ነን ባዮችንየሚያስወግደበት አሠራር መዘርጋቱንም ጠቅሷል። ያኔ ቢቢሲ ያነጋገራቸው የቅጥር እና የቴክኖሎጂ ባለሙያዎች፣ አጭበርባሪዎች በብዙ መንገድ እንደሚመጡ አስረድተዋል።

ሁሉም ባለሙያዎች ሥራ ፈላጊዎች ሥራ ከመጀመራቸው አስቀድሞቀጣሪ ነንየሚሉ ኩባንያ ወይም ግለሰቦች ትክክለኛ መሆናቸውን እንዲያጣሩ ይመክራሉ። የናትናኤልም ሀሳብ ተመሳሳይ ነው።የምንሠራበትን ዌብሳይት ትክክለኝነት ሳናረጋግጥ ሥራ ከጀመርን እና ችግር ከገጠመን ተስፋ እንድንቆርጥ እና ሌሎችን እንዳናምን ነው የሚያደርገንይላል። ቀጥሎምማንኛውንም ሥራ ከመጀመራችን በፊት 10 ደቂቃ ወስደን [ሰለ ድረገጹ] ብናጣራ ሁሉንም ማወቅ እንችላለን። ያየነውን ሁሉ ማመን የለብንም፤ ማጣራት ይኖርብናልሲል ገልጿል።

የኦንላይን ሥራ ትጋት ይፈልጋል

ናትናኤል በኦንላይን የሚሠሩ ሥራዎች ጥሩ ገንዘብ ቢሠራባቸውም ትዕግሥት እንደሚፈልጉ ይገልጻል።የኦን ላይን ሥራ ትጋት ይፈልጋል። አሁን እኔ ከጓደኞቼ ጋር የምዝናናበትን ጊዜ ቀንሼ፣ ከቤተሰቤ ጋር በደንብ ጊዜ ማሳለፍ ብፈልግም እሱንም ቀነስ አድርጌ፣ እንቅልፌን ቀነስ አድርጌ ነው የምሠራው። የወደፊቱን ለማሳካት ያለኝ አማራጭ ትጉህ መሆን ብቻ ነውይላል።  ቀጥሎበምንም ነገር ተስፋ አልቆርጥምሲል ጨምሯል።  ለናትናኤል ትጋት እና ተስፋ አለመቁረጥ መገለጫዎቹ የሆኑት ግን ከዚህ ሥራም ቀደም ብሎ ነው። ወጣቱ ቤተሰቦቹን መደገፍ የጀመረው እንደሚጠበቀው የምረቃ ጋወን ካጠለቀ፣ መነሳነስ ካዞረ እና ሥራ ከጀመረ በኋላ አልነበረም።

26 ዓመቱ ናትናኤል በኮምፒውተር ሳይንስ ከባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ተመርቋል።  ያኔ ከቤተሰብ የሚላክለት ገንዘብ አልነበረም። በታቀራኒው እርሱ ወደ አዲስ አበባ ገንዘብ ይልካልወደ ቤተሰቦቹ።  በተለይ የሁለተኛ ዓመት ተማሪ ሳለ አባቱ በጠና ከታመሙ በኋላ ቤተሰቡንቀጥ አድርጎአስተዳድሯል።  አምስት ወንድም እና እህቱን አስተምሯል። በሚገኘው ገንዘብ የአባቱን ሕክምና፣ የቤት አስቤዛ፣ የእህት እና ወንድሞቹ የትምህርት ቤት ወጪ ይሸፍን እንደነበር ይናገራል። ዩኒቨርሲቲ እየተማረ፣ አዳራሽ ተከራይቶ 20 እስከ 30 የሚሆኑ ሰዎችን ዳንስ እያሠለጠነ ገንዘብ ያገኝ ነበር።  ሲመሽ ደግሞበዲጄነትባሕር ዳር የሚገኝ ዕውቅ ሪዞርት ውስጥ ይሠራ ነበር።

ቅዳሜ እና እሁድ ፎቶ ቤቶች ሄዶ የሠርግ ቪዲዮዎችን ኤዲት ያደርግ ነበር። እየተማረ ይህንን ሁሉ እየሠራ በወር 8 እስከ 10 ሺህ ብር ያገኝ እንደነበር ጠቅሷል። ከዚያ ቀደም ብሎ ከአባቱ የተማረውን የእንጨት ሥራ ሠርቷል። ከዚያ በፊት ደግሞ በአስራዎቹ እድሜ ላይ እያለ ዲሽ ይጠግን ነበር። አባቱ ከወራት በፊት ሕመማቸው ጥንቶ አርፈዋል። አሁን ሙሉ በመሉ ቤተሰቡን የማስተዳደር ኃላፊነትን ወስዷል። በሥራዎቹ ያዳበረው ትጋት እና ተስፋ አለመቁረጥ ወደፊት ሩቅ ለሚያስብበትየኦንላይን ቢዝነስእጅግ እንደጠቀመው ይናገራል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Cart

Your Cart is Empty

Back To Shop

የሚፈልጉትን ይዘዙን

Order what you want