አዋኪ ድርጊት በሚፈፀምባቸው ንግድ ቤቶች ላይ እርምጃ እየተወሰደ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ አሳውቋል። Leave a comment

ሰሞኑን በቦሌ ክፍለ ከተማ ከ3 ሺህ 80 የሺሻ ዕቃ እና 80 ኪሎ ግራም አደንዛዥ ዕፅ ተይዞ መወገዱን ገልጿል።

በህጋዊ ንግድ ሽፋን ሺሻ እና አደንዛዥ ዕፅ ሲጨስባቸው ከተገኙ ቤቶች ነው ይሄ የተያዘው።

ፖሊስ በሰጠው መረጃ በድንገተኛ ቁጥጥር ከተደረገባቸው መካከል ፦

– መኖሪያ ቤቶች

–  ፔንሲዮኖች፣

– ማሳጅ ቤቶች እና የምሽት ጭፈራ ቤቶች ይገኙበታል፡፡

ይህ ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል ተብሏል።

ከዚህ ጋር በተያያዘ በተለይም በአዲስ አበባ በጋራ መኖሪያ ቤቶች ያለው አዋኪ ድርጊት እጅግ ትኩረት የሚሻ እንደሆነ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከቤተሰቦቹ የደረሰው መልዕክት ያስረዳል።

በተለይ ተማሪዎች፣ ህፃናት፣ የወለዱ እናቶች፣ ቀን ስራ ደክመው የሚገቡ በርካታ ዜጎች ባሉባቸው የጋራ መኖሪያ ቤቶች አካባቢ ብዙ አዋኪ ድርጊቶች በመኖራቸው ትኩረትን ያሻል።

የግል መኖሪያ ቤቶች ለሺሻ ማጬሻ ፣ ለመጠጥ መጠቻ፣ ለሲጋራ ማጬሻ እየዋሉ ማህበረሰቡ እንደሚታወክ ተጠቁሟል።

ምሽት ላይም ቢሆን ከጭፈራ ቤቶች የሚወጣው ድምጽ ማህበረሰቡን ሰላም የሚነሳ በመሆኑ ቁጥጥር እንዲደረግ ተጠይቋል።

በድህረ ገጻችን ኢትዮ አማዞን በመግባት የሚፈልጉትን እቃ ማዘዝ  ብቻ  ሳይሆን የርስዎንም እቃዎች መሸጥ እንደሚችሉ ስናሳውቅዎት በደስታ ነው ። ለማስታወቂያ ወይንም ለመግቢያ ምንም ክፍያ አይጠበቅብዎትም፤  ለተጨማሪ መረጃ   ድህረ ገጻችንን ይጎብኙ። https://ethio-amazon.com/

ለበለጠ መረጃ ሊንኩን በመንካት የቴሌግራም ግሩፓችንን ይቀላቀሉ!https://t.me/ethioamazon

ምንጭ ( @tikvahethiopia )

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Cart

Your Cart is Empty

Back To Shop

የሚፈልጉትን ይዘዙን

Order what you want