በረዥም ርቀት ሩጫ ታሪክ ከፍተኛ ተፎካካሪ የሆኑት ቀነኒሳ በቀለ እና ኤሉድ ኪፕቾጌ በፓሪስ ኦሎምፒክ የሚያደርጉት ውድድር በጉጉት እየተጠበቀ ነው።
የ41 ዓመቱ ቀነኒሳ በ5,000 ሜትር እና 10,000 ሜትር ውድድሮች ሦስት ጊዜ ኦሎምፒክ አሸንፏል። ሆኖም ግን ከ2012 ጀምሮ በውድድሩ አልተሳተፈም። በ2012 ውድድሩን ያጠናቀቀው አራተኛ ወጥቶ ነበር።
ባለፈው ወር በለንደን ማራቶን ሁለተኛ የወጣው ቀነኒሳ ከኬንያዊው ኤሉድ ኪፕቾጌ ጋር የፊታችን ነሐሴ ላይ በፓሪስ ውድድሩን ያደርጋል።
የ39 ዓመቱ ኪፕቾጌ የቀድሞ የማራቶን የዓለም ክብረ ወሰን ባለቤት ነበር። ሦስት ተከታታይ ኦሎምፒኮችን በማሸነፍ የመጀመሪያው አትሌት መሆን ይሻል። በ2016 በሪዮ እና በ2020 በቶኪዮ በተከታታይ አንደኛ መውጣቱ አይዘነጋም።
የቀነኒሳ እና የኪፕቾጌ ፉክክር መነሻ ፓሪስ በ2003 የተካሄደው የዓለም ሻምፒዮን ሺፕስ ነው።
ኪፕቾጌ በ5,000 ሜትር ወርቅ ሲያገኝ ቀነኒሳ ነሐስ አግኝቷል።
ከአንድ ዓመት በኋላ በአቴንስ ኦሎምፒክ በ5,000 ሜትር ኪፕቾጌ ነሐስ ሲያገኝ ቀነኒሲሳ ብር አግኝቷል። እዛው አቴንስ ቀነኒሳ በ10,000 ሜትር ወርቅ አግኝቷል።
ኪፕቾጌ በ2013 ወደ ማራቶን ፊቱን ካዞረ በኋላ የዓለም ምርጥ ሲል ራሱን ያሞካሻል። ከሁለት የኦሎምፒክ ወርቆች በተጨማሪ 11 ጉልህ ቦታ የሚሰጣቸው ውድድሮችን አሸንፏል።
ቀነኒሳ በ2014 ፓሪስ ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ ማራቶን ሲያሸንፍ 42.16 ኪሎ ሜትርን በፍጥነት በማጠናቀቅ ስድስተኛው ፈጣን ሰው ሆኗል።
ከዚያ በኋላ ግን ጉዳቶች እየገጠሙት ሩጫውን ሲያስተጓጉሉ ተስተውሏል።
ኪፕቾጌ እና ቀነኒሳ በፓሪስ ለመጀመሪያ ጊዜ ፉክክር ካደረጉ 21 ዓመታት አስቆጥረዋል።
‘የረዥም ርቀት ሩጫ ሮናልዶ እና ሜሲ’
ቀነኒሳ ከ12 ዓመታት በኋላ ወደ ኦሎምፒክ መመለሱ ለአድናቂዎቹ አስደሳችና አጓጊም ነው።
በአትሌቲክስ ከፍተኛ ስም ካተረፉ መካከል አንዱ የሆነው ቀነኒሳ ታላቅነቱን የማስመስከሪያ መመጨረሻው መድረኩ ፓሪስ ይሆናል።
ቀነኒሳ እና ኪፕቾጌ የረዥም ርቀት ታሪክን የለወጡ ናቸው።
በረዥም ርቀት ሩጫ ልክ እንደ ክርስቲያኖ ሮናልዶ እና ሊዮኔል ሜሲ ናቸው።
ኪፕቾጌ እስከ ጥቅምት ድረስ የዓልም ሪከርድ ባለቤት ነበር። በ2019 ማራቶን ከሁለት ሰዓት በታች በመግባት የመጀመሪያው ሆኗል።
በቤጂንግ ውድድር ቀነኒሳ በ5,000 ወርቅ ሲያገኝ ኪፕቾጌ ብር አግኝቷል።
ለመጨረሻ ጊዜ ቀነኒሳ እና ኪፕቾጌ ፉክክር ያደረጉት በ2018 ነበር።
ያኔ ያሸነፈው ኪፕቾጌ ነበር።
በድህረ ገጻችን ኢትዮ አማዞን በመግባት የሚፈልጉትን እቃ ማዘዝ ብቻ ሳይሆን የርስዎንም እቃዎች መሸጥ እንደሚችሉ ስናሳውቅዎት በደስታ ነው ። ለማስታወቂያ ወይንም ለመግቢያ ምንም ክፍያ አይጠበቅብዎትም፤ ለተጨማሪ መረጃ ድህረ ገጻችንን ይጎብኙ። https://ethio-amazon.com/
ለበለጠ መረጃ ሊንኩን በመንካት የቴሌግራም ግሩፓችንን ይቀላቀሉ!https://t.me/ethioamazon
ምንጭ፡- (ቢቢሲ )