በሶማሊያ መዲና ሞቃዲሾ በሚገኝ ታዋቂ የባህር ዳርቻ ላይ አጥፍቶ ጠፊ እና ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃት ቢያንስ 32 ሰዎች መገደላቸውን ፖሊስ አስታወቀ።
ከሞቱት በተጨማሪ ወደ 63 የሚጠጉ ሰዎች መቁሰላቸውን እና አንዳንዶቹም የከፋ መሆኑን የፖሊስ ቃለ አቀባይ አብዲፋታህ አደን ሐሰን ተናግረዋል።
በሞቃዲሾ አብዲአዚዝ ሰፈር ላይ በተፈጸመው ጥቃት በርካታ አስክሬኖች እንዲሁም የቆሰሉ ሰዎችን የሚያሳይ ቪዲዮ ወጥቷል።
ጥቃቱ የተፈጸመው የአገሪቱን ደቡብ እና መካከለኛ ሰፊ ግዛቶችን የሚቆጣጠሩት የአልሸባብ ታጣቂዎች መሆናቸውን የሃገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።
አልሻባብ ከአልቃይዳ ጋር ግንኙነት ያለው ሲሆን ለባለፉት አስርት ዓመታትም በተባባሩት መንግሥታት ድርጅት በሚደገፈው የሶማሊያ መንግሥት ላይ የሽምቅ ውጊያ እያካሄደ ይገኛል።
“ፍንዳታው ከደረሰ በኋላ የተኩስ እርምታ መሰማቱን ተከትሎ ምን እየተካሄደ እንደሆነ ለማወቅ አስቸጋሪ” ሆኖ እንደነበር እና በርካቶች በፍርሃት መዋጣቸውንም አንድ የዓይን እማኝ ለኤኤፍፒ የዜና ወኪል ተናግረዋል።
ቃለ አቀባዩ አንዳንዶች ከጥቃቱ ለማምለጥ መሬት ላይ የተኙ ሲሆን ሌሎች ደግሞ መሸሻቸውን አስረድተዋል።
“በባህርዳርቻው ስፍራ የቆሰሉ ሰዎችን አይቻለሁ። በርካቶች በድንጋጤ እየጮሁ የነበረ ሲሆን ሟቾችን ለመለየት አስቸጋሪ አድርጎት ነበር” ሲሉ አክለዋል።
ለጥቃቱ ቢያንስ አምስት ግለሰቦች ተጠያቂ መሆናቸውን የገለጹት ቃለ አባዩ አንድ አጥቂ ራሱን ሲያፈነዳ ሌሎች ሶስቱ ተገድለዋል ብለዋል። አንደኛው አጥቂ በህይወት መያዙንም የፖሊስ ቃለ አቀባዩ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል።
በድህረ ገጻችን ኢትዮ አማዞን በመግባት የሚፈልጉትን እቃ ማዘዝ ብቻ ሳይሆን የርስዎንም እቃዎች መሸጥ እንደሚችሉ ስናሳውቅዎት በደስታ ነው ። ለማስታወቂያ ወይንም ለመግቢያ ምንም ክፍያ አይጠበቅብዎትም፤ ለተጨማሪ መረጃ ድህረ ገጻችንን ይጎብ/ኙ። https://ethio-amazon.com/
ለበለጠ መረጃ ሊንኩን በመንካት የቴሌግራም ግሩፓችንን ይቀላቀሉ!https://t.me/ethioamazon
ምንጭ፡– (ቢቢሲ)