በቱኒዝያ የባህር ዳርቻ በነዳጅ ማቀነባባሪያ ለበርካታ ቀናት ያለ እርዳታ የቀሩ ስደተኞች ተገኙ….. Leave a comment

ሜዲትራኒያን ባሕርን ለመሻገር የሞከሩ ኢትዮጵያዊያን አሊያም ኤርትራዊያንን ጨምሮ 32 ፍልሰተኞች በቱኒዚያ የባህር ዳርቻ ለበርካታ ቀናት ያለ እርዳታ ከቆዩ በኋላ በረድኤት ድርጅት ሕይወታቸው ታደገ።

ፍልሰተኞች ተሳፍረውበት የነበረው ጀልባ አደጋ ከደረሰበት በኋላ “ሴቶች፣ ህፃናት እና ወንዶች” ካለ ምግብ እና ውሃ ለቀናት መቆየታቸውን ሜድትሪና የተሰኘው ረድኤት ድርጅት ገልጿል።

አንድ ሰው በነዳጅ ማቀነባበሪያው ውስጥ ሕይወቱ ማለፉንም አስታውቋል።

መንግሥታዊ ያልሆነው ድርጅት ከነዳጅ ማቀነባበሪያው 32ቱንም ፍልሰተኞች ማክሰኞ ከሰዓት እንደታደገ የገለፀ ሲሆን፤ ፍልሰተኞቹ ክትትል እተደረገላቸው ነው ብሏል።

ይሁን እንጂ ፍልሰተኞችን የያዘው ጀልባ መዳረሻው የት እንደሆነ ግልፅ አይደለም። በአቅራቢያ የሚገኙ አገራት ለጀልባዋ ደኅንነትን የሚያረጋግጥ ማረፊያ ወደብ አልመደቡም ብሏል።

ከጉዳዩ አስቸኳይነት አንፃር የትኛውም የአውሮፓ አገር ጣልቃ አለመግባቱን የጠቀሰው ድርጅቱ፤ ፍልሰተኞቹ በዓለም አቀፍ ውሃ በቱኒዚያ እና ማልታ የፍለጋ እና ሕይወት አድን ድንበር ላይ ነበሩ ብሏል።

የአየር በረራዎችን የሚከታተል አንድ መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት ከአራት ቀናት በፊት በነዳጅ ማቀነባበሪያው የፕላስቲክ ጀልባ እንደተመለከተ ተናግሯል።

አደጋ የደረሰባቸው ፍልሰተኞች በባሕር ችግር ወቅት የሕይወት አድን የአስቸኳይ ጊዜ ስልክ መደወል መቻላቸው ታውቋል።

በዚህ የስልክ ለውውጥ ፍልሰተኞቹ ያለ ምግብ ለቀናት መቆየታቸውን እና ያሉበት ሁኔታ አሳሳቢ መሆኑን ተናግረዋል።

ከዚህ በተጨማሪም የአንድ ሰው ሕይወት ማለፉንም በስልክ አሳውቀዋል።

በረድኤት ድርጅቱ የተጋራው እና በነዳጅ ማቀነባበሪያው በአንድ ሰው የተቀረፀ ተቀሳቃሽ ምስል ነጭ ቲሸርት የለበሰ ግለሰብ “በረሃብ እና በብርድ እየተሰቃየን ነው” ሲል ይደመጣል።

በትግርኛ ቋንቋ የተናገረው ግለሰቡ ሊቢያን ከለቀቁ አምስተኛ ቀን እንደሆናቸው እና የተሳፈሩበት ጀልባ ከአቅም በላይ ፍልሰተኞችን ጭና እንደነበር ተናግሯል።

“እዚህ በሕይወት የተረፉ እና በባሕር ያልሞቱ ሰዎች በረሃብ እና በድካም እየተሰቃዩ ነው። በሚቀጥሉት ጥቂት ሰዓታት የሆነ አካል ምንም የማያደርግ ከሆነ በግልፅ እንሞታለን። በሕይወት ለመትረፍ ዕድላችን ውስን ነው” ብሏል።

የባሕር ማዕበሉ የነዳጅ ማቀነባበሪያ ምሰሶዎችን ሲገጭ ከግለሰቡ ጀርባ የቆሙት ፍልሰተኞች በብርድ ሲንቀጠቀጡ ይታያሉ።

በመንግሥታቱ ድርጅት መረጃ መሰረት እ.አ.አ በ202፣ 210 ሺህ ሰዎች ማዕከላዊ ሜዲትራሊያንን ለመሻገር ሞክረዋል።

60 ሺህ የሚሆኑት ፍልሰተኞች ተይዘው ወደ አፍሪካ ዳርቻዎች እንዲመለሱ ተደረገ ሲሆን፤ ሁለት ሺህ የሚሆኑት ደግሞ ባሕር ላይ ሕይወታቸውን አጥተዋል።

በድህረ ገጻችን ኢትዮ አማዞን በመግባት የሚፈልጉትን እቃ ማዘዝ  ብቻ  ሳይሆን የርስዎንም እቃዎች መሸጥ እንደሚችሉ ስናሳውቅዎት በደስታ ነው ። ለማስታወቂያ ወይንም ለመግቢያ ምንም ክፍያ አይጠበቅብዎትም፤  ለተጨማሪ መረጃ   ድህረ ገጻችንን ይጎብ/ኙ። https://ethio-amazon.com/

ለበለጠ መረጃ ሊንኩን በመንካት የቴሌግራም ግሩፓችንን ይቀላቀሉ!https://t.me/ethioamazon

ምንጭ፡– (ቢቢሲ)

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Cart

Your Cart is Empty

Back To Shop