በአዲስ አበባ ከተጠራው ሰልፍ ጋር በተያያዘ 4 አስተባባሪዎች እና 97 ሰዎች ታሰሩ Leave a comment

በመጪው እሁድ ኅዳር 30/2016 .. በአዲስ አበባ ከተማ ይካሄዳል የተባለውን ሰላማዊ ሰልፍ ከሚያስተባብሩት ፖለቲከኞች መካከል አራቱ በፖሊስ መያዛቸው ሲነገር፣ ከዚሁ ጋር በተያያዘ 97 ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን መንግሥት አስታወቀ።

ከሰልፉ አስተባባሪዎች ውስጥ አራቱ ሐሙስ ኅዳር 27/2016 .. በቁጥጥር ስር የዋሉት ሊካሄድ የታቀደውን ሰላማዊ ሰልፍለማስቀረት ነውየሚል ጥርጣሬ እንዳላቸው ከሰልፉ አስተባባሪዎች አንዱ የሆኑት የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ) ሊቀመንበር ረዳት ፕሮፌሰር ዝናቡ አበራ ለቢቢሲ ተናግረዋል።

ከአስተባባሪዎቹ መታሰር በኋላ ምሽት ላይ ከፀጥታ እና ደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይል የወጣ መግለጫበሰላማዊ ሰልፍ ሽፋን አዲስ አበባ ውስጥ ሁከት እና ብጥብጥ ለመፍጠር በኅቡዕ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ቡድኖች ሴራ መክሸፉንገልጾ፣ በዚህም 97 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አስታውቋል።

ነገር ግን በፀጥታ ኃይሉ ከተያዙት ሰዎች መካከል አራቱ የሰልፉ አስተባባሪዎች ስለመኖራቸው ያለው ነገር የለም።

ሐሙስ ጠዋት ከታሰሩት አስተባባሪዎች ውስጥ የኢሕአፓ ተቀዳሚ ምክትል ሊቀመንበር መጋቢ ብሉይ አብርሃም ሃይማኖት እና የቀድሞ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) አባል አቶ ናትናኤል መኮንን እንደሚገኙበት የሰልፉ አስተባባሪዎች የሆኑት አቶ የሺዋስ አሰፋ እና ረዳት ፕሮፌሰር ዝናቡ ለቢቢሲ አረጋግጠዋል።

በተጨማሪም በቅርቡ የመሥራች ጠቅላላ ጉባኤውን ያካሄደው የትንሳኤ ሰባ እንደርታ ፓርቲ አመራሮች አቶ ጊደና መድኅን እና አቶ ካልኣዩ መሐሪም በዛሬው ዕለት የታሰሩት ሌሎች የሰልፉ አስተባባሪዎች እንደሆኑም ገልጸዋል።

ከፀጥታ እና ደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይሉ በመግለጫው እንዳለው ወደ አዲስ አበባ ከተማየታጠቁ ኃይሎችን እና ቡድኖችን አስርጎ የማስገባት ሙከራ መደረጉን እና በሰልፍ ሽፋን ሁከት እና ግርግርለመፍጠር ዕቅድተልዕኮ የወሰዱ 97 ተጠርጣሪዎችመያዙን አመልክቷል።

ጨምሮም በአማራ እና በኦሮሚያ ክልሎች ያሉ ታጣቂዎችን ሴራ ለማክሸፍ በአዲስ አበባ የተለያዩ አካባቢዎች ድንገተኛ ፍተሻ መካሄዱን እናከፀረሰላም ኃይሎች ጋር በትብብር የሚሠሩያላቸው ተጠርጣሪዎችን ከጦር መሳሪያዎች እና ከመገናኛ ሬዲዮዎች ጋር በቁጥጥር ስር ውለዋል ብሏል።

ግብረ ኃይሉ በአማራ እና በኦሮሚያ ክልሎች በአንዳንድ አካባቢዎች የሚንቀሳቀሱት ኃይሎች በስም ያልጠቀሳቸው ነገር ግንየውጭ ኃይሎችባላቸው ወገኖች አገር ለማፍረስ ይደገፋሉ በማለት የቀሩትንም ለመያዝ ዘመቻው እንደሚቀጥል ገልጿል።

በቁጥጥር የዋሉት አራቱ የሰልፉ አስተባባሪዎች በፖሊስ ቁጥጥር የዋሉት ከተለያዩ ቦታዎች መሆኑን የሚያስረዱት የኢሕአፓ ሊቀመንበር፤ አራቱም በአዲስ አበባ ሜክሲኮ አካባቢ በሚገኘው የፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ እንደሚገኙ ተናግረዋል።

አራቱ ፖለቲከኞች እስካሁን ደረስቃል ስላልሰጡበምን ምክንያት በቁጥጥር ስር እንደዋሉ እንዳልታወቀ ረዳት ፕሮፌሰር ዝናቡ ተናግረዋል።

ቢቢሲ የአራቱን ፖለቲከኞች የእስር ምክንያት በተመለከተ ከፌደራል ፖሊስ መረጃ ለማግኘት ያደረገው ጥረት አልተሳካም።

የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ቃል አቀባይ ጄይላን አብዲ ስለ እስሩ ለቀረበላቸው ጥያቄመረጃ የሚሰጠው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ኮማንድ ፖስት ነውየሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

የኢህአፓ ሊቀመንበር ረዳት ፕሮፌሰር ዝናቡ ግን ፖለቲከኞቹ የታሰሩት በአስተባባሪነት እየተሳተፉበት ያለውን እና ለእሁድ ዕለት የተጠራውን ሰላማዊ ሰልፍ ለማስቀረት ነው የሚል ጥርጣሬ እንዳላቸው አስረድተዋል።

ከአራት ኪሎ ተነስቶ በመስቀል አደባባይ እንዲጠናቀቅ የተጠራው ሰልፍ ሦስት ዋነኛ ዓላማዎች እንዳሉት 12 የሰልፉ አስተባባሪዎች ከፊርማቸው ጋር ለአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ጽህፈት ቤት ያስገቡት ደብዳቤ ያስረዳል።

አስተባባሪዎቹ በዋናነት የጠቀሱት ዓላማ፤ በአማራ እና ኦሮሚያ ክልሎችደም አፋሳሽ ተግባር ውስጥይገኛል ያሉት የመከላከያ ሠራዊትያለምንም ቅድመ ሁኔታ ወደ ጠቅላይ ጦር ሰፈሩ እንዲገባ ለመጠየቅየሚለው ይገኝበታል።

በአዲስ አበባ፥ በኦሮሚያ እና ሲዳማ ክልሎችያለ ምንም ምክንያትየታሰሩ የአማራ ተወላጆች ከእስር እንዲፈቱ መጠየቅም ከሰልፉ ዓላማዎች መካከል ተጠቅሷል።

አስተባባሪዎቹ በሦስተኛነት የጠቀሱት የሰልፍ ዓላማ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የሚገኙ ተፈናቃዮችበአስቸኳይ ወደቀያቸው እንዲመለሱ መጠየቅየሚለውን ነው።

አስተባባሪዎቹ ይህንን ሰልፍ እንደሚያካሂዱ ካስታወቁ በኋላ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ጠርቶ እንዳነጋገራቸው የኢሕአፓ ሊቀመንበሩ ተናግረዋል።

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽነር ጠርቶ ሰልፉ መካሄድ እንደሌለበት፤ ምንም ጥበቃ እንደማያደርግልን ነግሮን ነበርሲሉ ከከተማዋ ፖሊስ ተሰጠን ያሉትን ምላሽ ገልጸዋል።

ቢቢሲ፤ ለአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ምክትል ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ ያደረገው የስልክ ጥሪ ምላሽ ባለማግኘቱ ተሰጠ የተባለውን ምላሽ ማረጋገጥ አልቻለም።

ከዛሬው የአራቱ የሰልፉ አስተባባሪዎች እስር በኋላ ለመጪው እሁድ የተጠራው ሰልፍ ላይ የዕቅድ ለውጥ ይኖር እንደሆነ ጥያቄ የቀረበላቸው የሰልፉ አስተባባሪ እና የኢሕአፓ ሊቀመንበር ረዳት ፕሮፌሰር ዝናቡ12 [የሰልፉ] አስተባባሪዎች የቀረነው ገና አልተገናኘንም። ተገናኝተን፣ ሊሆኑ የሚችሉ ሁኔታዎችን አስቀምጠን ምን ማድረግ እንዳለብን ውሳኔ ላይ እንደርሳለንብለዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Cart

Your Cart is Empty

Back To Shop

የሚፈልጉትን ይዘዙን

Order what you want