በአፋር እና በሶማሊ (ኢሳ) ወንድማማች ሕዝቦች መካከል የተኩስ አቁም ስምምነት መደረሱ ተነግሯል።
ይህ ስምምነት በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት ፕሬዚደንት ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም አደራዳሪነት የተደረሰ መሆኑን ም/ቤቱ ገልጿል።
ከሁለቱ ክልሎች የተውጣጡ የሀገር ሽማግሌዎች ለበርካታ ወራት ሲያወያዩ ሰላምን ለመፍጠር ሲመክሩ እንደነበር ተነግሯል።
በመጨረሻም ፥ በአፋር እና በኢሳ ማኅበረሰቦች መካከል የነበረውን የወንድማማቾች ደም መፋሰስ እንዲቆም የሁለትዮሽ ስምምነት ላይ ተደርሶ የተኩስ አቁም ስምምነት ተደርጓል።
የጠቅላይ ም /ቤቱ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚደንት ሼይኽ አብዱልከሪም ሼይኽ በድረዲን ፤ ስምምነቱ ውጤታማ እንዲሁን የሁለቱም ክልል መንግስታት ትልቅ ኃላፊነት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።
የጠቅላይ ምክር ቤት የፕሬዚደንቱ ልዩ አማካሪ ዑስታዝ አቡበከር አሕመድ በሁለቱ ወንድማማች ሕዝቦች መካከል የነበረው ደም መፋሰስ ” በምሥራቅ አፍሪካ ረጅም ዘመን ያስቆጠረ ነው ” ብለዋል።
አሁን ላይ በተደረገው ጥረት ሰላም እንዲሰፍን የሚያስችል ውጤት መገኘቱ ገልጸዋል።
በእስልምና አስተምህሮ የአንድን ሰው ሕይወት ማዳን ዓለምን ሁሉ ማዳን መሆኑን ገልጸው ፥ ” በመነጋገር ችግሮችን የመፍታት አካሄድ የሰላም ችግር ባሉባቸው በሌሎችም የሀገራችን ክልሎች ሁሉ ሊተገበር ይገባል ” ብለዋል።
በድህረ ገጻችን ኢትዮ አማዞን በመግባት የሚፈልጉትን እቃ ማዘዝ ብቻ ሳይሆን የርስዎንም እቃዎች መሸጥ እንደሚችሉ ስናሳውቅዎት በደስታ ነው ። ለማስታወቂያ ወይንም ለመግቢያ ምንም ክፍያ አይጠበቅብዎትም፤ ለተጨማሪ መረጃ ድህረ ገጻችንን ይጎብኙ። https://ethio-amazon.com/
ለበለጠ መረጃ ሊንኩን በመንካት የቴሌግራም ግሩፓችንን ይቀላቀሉ!https://t.me/ethioamazon
ምንጭ ፡-(@tikvahethiopia)