ቡሩንዲ በሀገሯ ግብረሰዶምን በፍፁም እንደማትቀበል አሳወቀች። Leave a comment

” የግብረሰዶም ድርጊትን የተላመዱና የሚለማመዱ በውጭ የሚኖሩ #ብሩንዲያውያን ወደ ሀገር ቤት እንዳይመለሱ ” – የቡሩንዲው ፕሬዜዳንት

የቡሩንዲው ፕሬዝዳንት ኢቫሪስቴ ንዳይሺሚዬ ቡሩንዲ ሀገራቸው ግብረሰዶምን በፍፁም እንደማትቀበል አሳውቀዋል።

ፕሬዝዳንቱ በጋዜጠኞች ተጠይቀው ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን ከግብረሰዶም ጋር ታያይዞ ” ሃያላኑ ሃገራት ለአፍሪካ ሀገራት እርዳታ እየለገሱ ለግብረሰዶማውያን መብት የመስጠት ግዴታን የሚያስቀምጡ ከሆኑ እርዳታቸውን እዛው መያዝ አለባቸው ” ሲሉ ተናግረዋል።

ግብረሰዶም በቡሩንዲ ወንጀል ነው ያሉት ፔሬዝዳንቱ ይህ ወንጀል እስከ ሁለት አመት እስር እንደሚያስቀጣ ገልፀዋል።

” በግሌ እንደዚህ አይነት ሰዎችን (ግብረሰዶሞችን) ቡሩንዲ ውስጥ ካየን ስታዲየም ውስጥ አስገብተን በድንጋይ መውገር አለብን ብዬ አስባለሁ፤ ይህንን ለሚያደርጉ ደግሞ ሃጢያት አይሆንም  ” ብለዋል።

ፕሬዝዳንቱ በአፍሪካ አህጉር ከ30 በላይ ሀገራት ይህን ድርጊት የማይቀበሉ እና ወንጀል መሆኑን ያስታወሱ ሲሆን የመጽሐፍ ቅዱስን ቃል በማጣቀስ ” አምላክ ግብረሰዶምን ይቃወማል ” ብለው በሀገራቸው ድርጊቱን በፍፁም እንደማይቀበሉት አስረድተዋል።

የዚህ አይነት የድርጊት መብት እንዲከበር ከምዕራባውያን ሀገራት ግፊት የሚደረግበትን መንገድ አስመልክቶ የተጠየቁት ፕሬዝዳንቱ ይህንን የሚመርጡ ሰዎች ወደ ምዕራቡ ዓለም ሄደው እነዚያን ልማዶች እንዲያደርጉ አስጠንቅቀው ድርጊቱ ከሀገሪቱ እና ከአህጉሪቱ ባህል እና እሴት ውጪ በመሆኑ በጭራሽ በሀገራቸው እንማይፈቀድ አስጠንቅቀዋል።

” ሰይጣንን የመረጡ እና የግብረሰዶም ድርጊትን የተላመዱና የሚለማመዱ በውጭ የሚኖሩ #ብሩንዲያውያን ወደ ሀገር ቤት እንዳይመለሱ ” ሲሉም አክለዋል።

በግብረሰዶማዊነት ጉዳይ በሌሎች በርካታ የአፍሪካ ሀገራት የተጠናከረ ህግ እያወጡ ሲሆን የጋና የፓርላማ አባላት ድርጊቱ በሶስት አመት እስራት የሚያስቀጣ ህግ እና የድርጊቱ ተከራካሪ ሆነው ዘመቻ የሚያደርጉ ሰዎችን እስከ 10 አመት እስራት ሊያስቀጣ የሚችል ህግ እያወጡ መሆኑ ተዘግቧል።

ኡጋንዳም ከእድሜ ይፍታህ እስራት እስከ #ሞት ድረስ የሚያስቀጣ ጠንካራ ህግ ማውጣቷ የሚዘነጋ አይደለም።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Cart

Your Cart is Empty

Back To Shop

የሚፈልጉትን ይዘዙን

Order what you want