ትራምፕን ከፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ያገዱት ዳኞች የግድያ ዛቻ እየደረሳቸው መሆኑ ተገለጸ Leave a comment

ዶናልድ ትራምፕ በመጪው የአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ በኮሎራዶ ግዛት መሳተፍ አይችሉም በሚል እግድ ያስተላለፉ ዳኞች የግድያ ዛቻ እየደረሳቸው መሆኑ ተነገረ።

የኮሎራዶ ፖሊስ የግድያ ዛቸውን እየመረመር መሆኑን እና በዳኞች መኖሪያ አቅራቢያ ተጨማሪ የፖሊስ ኃይል ማሰማራቱን አስታውቋል።

ኤፍቢአይ ደግሞ ለምርመራው ድጋፍ እያደረኩ ነው ብሏል።

ባለፈው ሳምንት የኮሎራዶ ግዛት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኞች የቀድሞ ፕሬዝዳንት ከሦስት ዓመታት በፊት በተከሰተው በካፒቶል ሂል አመጽ ተሳትፈዋል በሚል ትራምፕን በግዛቱ በፕሬዝዳንታዊ ምርጫ እንዳይሳተፉ ማገዳቸው ይታወሳል።

ይህ የፍርድ ቤቱ ውሳኔ በ2024 የአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ዕጩ ሆኖ ለመቅረብ ያቀዱትን ፕሬዝዳንት ትራምፕ ሙሉ በሙሉ ከተወዳዳሪነት የሚያግድ ባይሆንም በኮሎራዶ እንዳይወዳደሩ በማገድ ለተቀናቃኞቻቸው የተሻለ የማሸነፍ ዕድልን ይሰጣል።

የኮሎራዶ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኞች ዶናልድ ትራምፕ ከካፒቶል ሂል አመጽ በፊት “ለደጋፊዎቻቸው የትግል ጥሪ አስተላልፈዋል . . . ደጋፊዎቻቸውም ለዚህ ጥሪ ምላሽ ሰጥተዋል” በማለት ትራምፕ በአመጹ በቀጥታ መሳተፋቸውን ገልጸዋል።

የፍርድ ቤቱ ውሳኔ ይፋ ከሆነ በኋላ ከአንዳንድ የትራምፕ ደጋፊዎች በኢንተርኔት አማካይነት ዳኞች ላይ ያነጣጠር ዛቻ አዘል አስተያየቶች ሲሰጡ ነበር።

ታዲያ ዛቻ አዘል አስተያየቶቹ የዳኞችን የመኖሪያ አድራሻ እና ስልክ ቁጥር ያሉ የግል መረጃን መያዛቸው ፖሊስ ጉዳዩን በትልቅ ትኩረት እንዲከታተለው አድርጓል።

በቀድሞ ትዊተር አሁን ኤክስ ተብሎ በሚታወቀው እንዲሁም በቴሌግራም ማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ ዳኞቹን ሰቅሎ ወይም በጥይት መትቶ የመግደል ዛቻዎች ተለጥፈዋል።

የኮሎራዶ ግዛት መዲና የሆነችው የዴንቨር ፖሊስ የትኛውንም አይነት ዛቻ እና ትንኮሳ በጥልቀት እንደሚመረምር ገልጿል።

በኮሎራዶ ዳኞች ላይ እየደረሰ ስላለው የግድያ ዛቻን በተመለከት እስካሁን ድረስ በዶናልድ ትራምፕ በኩል የተሰጠ አስተያየት የለም። ይሁን እንጂ የምርጫ ቅስቀሳ ቡድናቸው የኮሎራዶ ግዛት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ያስተላለፈውን ውሳኔ በመቃወም ጉዳዩን ወደ ፌደራል መንግሥቱ ጠቅላይ ፍርድ ቤት እንወስደዋለን ብለዋል።

ትራምፕ የፍርድ ቤቱን ውሳኔ በመቃወም ለጠቅላይ ፍርድ ቤቱ እስከ ታኅሣሥ 25/2016 ዓ.ም. ድረስ አቤቱታ ማቅረብ ይችላሉ።

ከዚህ ቀደም በተመሳሳይ ትራምፕን በኒው ሃምፕሻየር፣ በሚኒሶታ እንዲሁም ሚሺጋን ግዛቶች በምርጫ እንዳይወዳደሩ ለማገድ የተደረጉ ጥረቶች ሳይሰምሩ ቀርተዋል።

በኮሎራዶም ሆነ ትራምፕ በቀጣይ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ እንዳይሳተፉ ለማገድ ጥረት በተደረገባቸው ግዛቶች፤ እአአ 2020 በተካሄደው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ አሸናፊ የነበሩት ጆ ባይደን ናቸው።ቀጣዩ የአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ጥቅምት 26/2017 ዓ.ም. ለማድረግ ዕቅድ ተይዞለታል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Cart

Your Cart is Empty

Back To Shop

የሚፈልጉትን ይዘዙን

Order what you want