አንድ ግለሰብ ያለ ፓስፖርት እና የአየር ትኬት አሜሪካ እንዴት ሊገባ ቻለ ?? Leave a comment

አንድ 46 ዓመት ጎልማሳ ያለ ፓስፖርት እና የአየር ትኬት አውሮፕላን ተሳፍሮ ከዴንማርክ ተነስቶ በአሜሪካዋ ሎስ አንጀለስ ከተማ ከደረሰ በኋላ በቁጥጥር ሥር ዋለ። ሰረጌይ ኦቺጋቫ የተባለው ግለሰብ ያለ ፍቃድ እና በቂ የጉዞ ሰነድ ሳይዝ ድንበር በመሻገሩ በአሜሪካ በቁጥጥር ሥር ውሎ ክስ ተመስርቶበታል።

ግለሰቡ በሎስ አንጀለስ በቁጥጥር ሥር ሲውል የሩሲያ እና የእስራኤል መታወቂያዎች ይዞ የተገኘ ሲሆን እስካሁን ግን ዜግነቱን መለየት አልታቻለም።ወንጀል መርማሪዎች ግለሰቡ ከዴንማር እስከ ሎስ አንጀለስ 12 ሰዓታት በሚወስደው ጉዞ ላይ እራሱን ለመደበቅ ምንም ዓይነት ጥረት አለማድረጉን ይለቁንም ከሌሎች ተሳፋሪዎች ጋር ለማውራት ጥረት ሲያደርግ ነበር ብለዋል።

ኦቺጋቫ ጥቅምት 24/2016 .. ሎስ አንጀለስ ከተማ ደርሶ በቁጥጥር ስር ከዋለ በኋላ ፓስፖርቱን አውሮፕላን ውስጥ መርሳቱን ለመርማሪዎቹ ተናግሮ ነበር። ይሁን እንጂ ምንም ዓይነት የጉዞ ሰነድ ተሳፍሮበት በነበረው አውሮፕላን ላይ አልተገኘም።ከዚህ በተጨማሪም መርማሪዎች ወደ አሜሪካ ለሚደረግ ጉዞ ግለሰቡ ምንም ዓይነት የአየር ትኬት አለመቁረጡን እንዲሁም ከየትኛው አገር ሆኖ የአሜሪካ ቪዛ አለመጠየቁን አረጋግጠዋል።

ኦቺጋቫ ለመርማሪዎች በሰጠው ቃልየአውሮፕላን ቲኬት ሳይኖረኝ አይቀርም . . . እርግጠኛ ግን አይደለሁምስለማለቱ የከተፈተበት የወንጀል ክስ ሰነድ ያሳያል።ግለሰቡ ለቀረበበት ክስ ጥፋተኛ አይደለሁም ያለ ሲሆን ከሁለት ሳምንታት በኋላ ፍርድ ቤት ይቀርባል ተብሎ ይጠበቃል። መርማሪዎች ግሰለቡ ምንም ዓይነት የጉዞ ሰነድ ሳይዝ እንዴት አውሮፕላን መሳፈር ቻለ የሚለውን ለመመለስ እየመረመሩ ይገኛሉ።

ኦቺጋቫ ግን ከዴንማርክ ተስቶ ወደ አሜሪካ እየበረረ በነበረው ስካንዲኔቪያን አየር መንገድ በረራ ላይ እንዴት እንደተሳፈረ እንደማያስታውስ ተናግሮ።ለሦስት ተከታታይ ቀናት እንቅልፍ አልተኛሁም፣ በዴንማርክ አየር ማረፊያ የደኅንነት መቆጣጠሪያዎችን እንዴት እንዳለፍኩም አላስታውስምብሏል።

ይህ የሩሲያ እና የእስራኤል መታወቂያዎች ይዞ የተገኘው ግለሰብ ቀድሞውኑ እንዴት ዴንማርክ ሊገባ እንደቻለ ምርመራ እየተደረገ ነው።ኦቺጋቫ ለአሜሪካ መርማሪዎች በሰጠው ቃልከረዥም ዓመታት በፊትበሩሲያ የምጣኔ ሃብት ባለሙያ ሆኜ ሠርቻለሁ ብሏል። ስካንዲኔቪያን አየር መንገድ ሠራተኞች ያልተመዘገበ ትርፍ ተጓዥ ይዘው መብረራቸውን ያወቁት ከመርማሪዎች ጥያቄዎች ሲቀርቡላቸው ነበር። የበረራ አስተናጋቾች ኦቺጋቫ በበረራው ወቅት በተደጋጋሚ ወንበር እየቀየር ሲቀመጥ እንደነበረ ተናግረዋል።

የበረራ አስተናጋቾች ለተጓዦች ምግብ ሲያቀርቡም ኦቺጋቫ ተጨማሪ ምግብ እየጠየቀ ሲመገብ እንደነበረ የተናገሩ ሲሆን አንድ የበረራ አስተናጋጅ ኦቺጋቫ ሌሎች ተሳፋሪዎችን ለማነጋገር ጥረት ቢያደርግም ተሳፋሪዎች ግን መልስ አልሰጡት ስትል ተናግራለች።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Cart

Your Cart is Empty

Back To Shop

የሚፈልጉትን ይዘዙን

Order what you want