ኢትዮጵያ ከIMF ብድር ለማግኘት የብርን የመግዛት አቅም ለማዳከም ትስማማለች ? ሌላ አማራጭ የለም ? Leave a comment

የምጣኔ ሃብቱ ባለሞያ አቶ ያሬድ ኃይለመስቀል ፦

” devaluation የሚቀር አይመስለኝም። በምን ያህል ደረጃ devalue ይደረጋል የሚለው ጥያቄ ነው እንጂ devalue ሳይደረግ IMF / World Bank ገንዘብ ይሰጣል ብዬ እንደ ራሴ አልገምትም።

አማራጭ ፖሊስ በራሱ መጥፎ አልነበረም። ቅደም ተከተሉን አለማስተካከል ነው ትልቁ ስህተት። ለምሳሌ ከሌሎች መጀመር ይቻል ነበር።

liberalization ሊቀድም ይችል ነበር ከdevaluation ፤ liberalization ሲደረግ አዲስ ካፒታል ወደ ሀገር ውስጥ እንዲገባ ማድረግ ይቻላል።

በዚህ ሂደት ካፒታል / ዶላር ይገኝ ነበር። ይህ ደግሞ የዶላርም ይሁን የሌላ ውጪ አሳሳቢ አይሆንም ነበር። እዳንም መቀነስ ይቻላል። አሁን ግን እዳ ይጨምራል።

ለምሳሌ ፦ የዛሬ 7 ዓመት ለባቡር ወይም ለሌላ የተበደርነው ዶላር ቢኖር መንግሥት ይጠበቅበት የነበረው 22 ብር ቀረጥ ሰብስቦ ወደ 21 ዶላር ቀይሮ መስጠት ነበር አሁን 56 እና 57 ታክስ መሰብሰብ አለበት።

የኑሮው ውድነት ?

ካለንበት ችግር በመነሳት የብር የመግዛት አቅም እንዲዳከም ቢወሰን በዋጋ ንረት ላይ በኑሮው መወደደ ላይ የሚያደርሰው ተፅእኖ ከባድ ነው።

ብዙ ነገር imported inflation የሚባለው ነዳጅ 39 ብር ነበር አሁን ከ70 በላይ ሆኗል ፤ ማዳበሪያውም ፣ ስንዴውም ፣ መኪናውም በብዛት 21 ቢሊዮን ዶላር የሚገመት እቃ ወደ ሀገር ይገባል 3 – 4 ቢሊዮን የሚገመት export ታደርጋለች ይሄ ልዩነት ላይ ያለው 17 ቢሊዮን ብር የሚመጣውን እቃ ዋጋ ሊጨምረው ይችላል። ይሄ በእያንዳንዱ ቦታ ተበታትኖ በየሰዉ ኑሮ ላይ ተፅእኖ ያደርጋል።

inflation አሁን ትንሽ ረገብ አለ ቢባልም ከፍተኛ ነው። እንደገና ከፍ ሊል ይችላል።

ካፒታል ያላቸው ሰዎች ምንም ችግር የለባቸውም። ለምሳሌ ነጋዴ እቃ ቢወደድም ቢረክስም ችግር የለበትም የገዛበት ላይ ጨምሮ ነው የሚሸጠው ምናልባት ብዙ ላይሸጥ ይችላል ያ ሊጎዳው ይችላል።

ቁርጥ ያለ ገቢ ያለው ሰው ሊጎዳ ይችላል። ለምሳሌ የዛሬ 7 ዓመት 22 ሺህ ብር ደመወዝ የሚከፈለው ሰው 1000 ዶላር አካባቢ ነው አሁን ግን 450 ነው የሚያገኘው ስለዚህ ደመወዙ 50% ቅናሽ አድርጓል። በሌላ በኩል የመኖሪያ፣ የምግብ ዋጋ ጨምሯል።

ብዙ አማራጭ ያለ አይመስለኝም ከ devalue አንጻር። ያለውን ብር መቀበል ነው። አልያም ብሩን አልፈልግም ብሎ ሌላ አማራጭ መፈለግ ነው። ወይም የሚባለውን አድርጎ የሚያስከትለውን ችግር መፍትሄ መፈለግ ነው። ”

ይህ የምጣኔ ሃብት ባለሞያ አስተያየት የተወሰደው ከሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ መሆኑን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ይገልጻል።

በድህረ ገጻችን ኢትዮ አማዞን በመግባት የሚፈልጉትን እቃ ማዘዝ  ብቻ  ሳይሆን የርስዎንም እቃዎች መሸጥ እንደሚችሉ ስናሳውቅዎት በደስታ ነው ። ለማስታወቂያ ወይንም ለመግቢያ ምንም ክፍያ አይጠበቅብዎትም፤  ለተጨማሪ መረጃ   ድህረ ገጻችንን ይጎብኙ። https://ethio-amazon.com/

ለበለጠ መረጃ ሊንኩን በመንካት የቴሌግራም ግሩፓችንን ይቀላቀሉ!https://t.me/ethioamazon

ምንጭ ፡-(@tikvahethiopia)

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Cart

Your Cart is Empty

Back To Shop