ከባለቤቷ ጋር ወሲብ መፈጸም ያቆመች ፈረንሳያዊት ለፍቺያቸው ጥፋተኛ ልትባል እንደማይገባ የአውሮፓውያኑ ፍርድ ቤት ወሰነ…… Leave a comment

ከባለቤቷ ጋር ወሲብ መፈጸም ያቆመች አንዲት ፈረንሳያዊት ለፍቺያቸው ጥፋተኛ ልትሆን አትገባም ሲል የአውሮፓውያኑ የሰብዓዊ መብቶች ፍርድ ቤት ውሳኔ አስተላለፈ።

የአውሮፓ የሰብዓዊ መብቶች ፍርድ ቤት ለ69 ዓመቷ ሴት በመወሰን ፍርድ ቤቶች በጋብቻ ውስጥ ወሲብን አሻፈረኝ ማለትን ለፍቺ ጥፋት ምክንያት አድርገው ሊቆጥሩት አይገባም ብሏል።

ፈረንሳይ በአውሮፓውያኑ የሰብዓዊ መብቶች የተደነገገውን የግለሰቧን ግላዊ እና የቤተሰብ መብቶችን ተላልፋለች ሲል የሰብዓዊ መብቶች ፍርድ ቤት ሲል አስተላልፏል። ፍርድ ቤቱ በዚህም ለአስር ዓመታት ሲጓተት የነበረውን የህግ እሰጣገባ ቋጭቶታል።

ኤች ደብልዩ ተብላ በምህጻረ ቃል የተጠቀሰችው ይህች ግለሰብ ውሳኔውን “የመድፈር ባህል” ለማስቀረት እና በጋብቻ ውስጥም ቢሆን ወሲብ ለመፈጸም ስምምነት ያስፈልጋል የሚለውን አንድ እርምጃ ያስኬደ ነው ስትል አሞግሳዋለች።

ለበርካታ ዓመታት በፍርድ ቤት ሲያወዛግብ የቆየው ይህ ጉዳይ በፈረንሳይ በጋብቻ ውስጥ የወሲብ ስምምነትን እና የሴቶች መብትን በተመለከቱ ውይይቶችን ያስነሳ ሆኗል። የኤች ደብአሊው ጠበቃ ሊሊያ ምሂሰን ውሳኔውን ያረጀ እና ያፈጀውን “የጋብቻ ግዴታ” የሚለውን እሳቤ ያፈረሰ ብለውታል።

አክለውም የፈረንሳይ ፍርድ ቤቶች በወሲብ ውስጥ በየትኛውም ቦታ ስምምነትን አስፈላጊነት እና እኩልነት ከመሳሰሉ ዘመናዊ ሃሳቦች ጋር ራሳቸውን እንዲያራምዱ የጠየቃቸው እንደሆነም አስረድተዋል። ኤች ደብልዩን የደገፉ የሴቶች መብት ቡድኖች የፈረንሳይ ዳኞች ጎጂ አመለካከቶችን የሚያስቀጥል “ጥንታዊ የጋብቻ ባህል” መጫኑን ቀጥለዋል ሲሉ ተችተዋል።

በፓሪስ አቅራቢያ ሌ ቼስናይ ነዋሪ የሆነችው ኤች ደብልዩ ከባለቤቷ ጋር የተጋቡት በአውሮፓውያኑ 1984 ነበር። ጥንዶቹ አራት ልጆችን አፍርተዋል። ከነዚህም ውስጥ አንደኛዋ ልጃቸው ሙሉ እንክብካቤ የምትፈልግ አካል ጉዳተኛ ስትሆን ይህንን ሙሉ ኃላፊነት ኤች ደብልዩ ወሰደች።

የመጀመሪያ ልጃቸው ከተወለደ በኋላ ጋብቻቸው የተቀዛቀዘ ሲሆን በአውሮፓውያኑ 1992 ኤች ደብልዩ የጤና እክሎች ያጋጥማት ጀመር።

በአውሮፓውያኑ 2002 ባለቤቷ የቃላት ጥቃት እንዲሁም አካላዊ ድብደባዎችን አድርሶበታል። እነዚህ ጥቃቶች ከጀመሩበት ከሁለት ዓመት በኋላ የወሲብ ግንኙነት በማቆም በአውሮፓውያኑ 2012 ለፍቺ ጥያቄ አቀረበች።

ፍርድ ቤቱ በፍቺያቸው ላይ በሚወስንበት ወቅት የጋብቻ ግዴታ አለማሟላት በሚል መወሰኑን ተከትሎ ግለሰቧ ይግባኝ ጠየቀች።

ግለሰቧ ለይግባኝ ፍርድ ቤት አቤቱታዋን ብታስገባም ይሄው የፈረንሳይ ፍርድ ቤት ለባለቤቷ ወሰነ። እንደገና ጉዳዩ ወደ ፈረንሳይ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰበር ሰሚ ችሎት ቢሄድም ፍርድ ቤቱ ያለምንም ማብራሪያ ይግባኙን ውድቅ አደረገ።

ይህንንም ተከትሎ ነው ግለሰቧ ጉዳይዋን ወደ አውሮፓ የሰብዓዊ መብቶች ፍርድ ቤት በአውሮፓውያኑ 2021 ያመጣችው።

ፍርድ ቤቱ በበኩሉ መንግሥታት በወሲብ ጉዳዮች ላይ ጣልቃ መግባት የሚችሉ በጣም ከባድ በሆኑ ምክንያቶች እንደሆኑ ወስኗል።

በፈረንሳይ ህግ ውስጥ የተጠቀሰው የጋብቻ ግዴታዎች የሚለው ሃሳብ በወሲብ ውስጥ በየትኛውም ወቅት ስምምነትን አስፈላጊነት ችላ ያለ ነው ሲል ፍርድ ቤቱ ወስኗል።

ፍርድ ቤቱ ለመግባባት መስማማት ማለት በማንኛውም ሁኔታ ለወደፊቱ ወሲብ እፈጽማለሁ የሚል ስምምነት እንዳልሆነ አጽንኦት ሰጥቷል። በትዳር ውስጥ መደፈር ከባድ ወንጀል መሆኑን የሚክድ እንደሆነ ሊቆጠር ይችላል ብሏል።

በድህረ ገጻችን ኢትዮ አማዞን በመግባት የሚፈልጉትን እቃ ማዘዝ  ብቻ  ሳይሆን የርስዎንም እቃዎች መሸጥ እንደሚችሉ ስናሳውቅዎት በደስታ ነው ። ለማስታወቂያ ወይንም ለመግቢያ ምንም ክፍያ አይጠበቅብዎትም፤  ለተጨማሪ መረጃ   ድህረ ገጻችንን ይጎብ/ኙ። https://ethio-amazon.com/

ለበለጠ መረጃ ሊንኩን በመንካት የቴሌግራም ግሩፓችንን ይቀላቀሉ!https://t.me/ethioamazon

ምንጭ፡– (ቢቢሲ)

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Cart

Your Cart is Empty

Back To Shop