“… ኮንትራክተሮችና ባለንብረቶች አደጋ አጋጥሞ ስንደርስ እንኳ ቦታው_ላይ_አይገኙም ” – አቶ ንጋቱ ማሞ Leave a comment

የአዲስ አበባ ከተማ እሳትና አደጋ ሥራ አመራር ኮሚሽን፥ በከተማው በአደጋ የሚከሰት ሞት ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ጊዜ አንጻር ዘንድሮ መጨመሩን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጸ። በብዛት የሞት አደጋ እየደረሰባቸው ያሉት ደግሞ የቀን ሠራተኞች መሆናቸውን ጠቁሟል።

የኮሚሽኑ የሕዝብ ግንኙነተ ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ምን አሉ ?

“ ከተማው ውስጥ ብዙ የግንባታ ሥራዎች ይከናወናሉ። በተለይ አሁን ሕይወታቸውን እያጡ ያሉት በኮንክትራክሽን / በግንባታ ዘርፉ ያሉ የቀን ሠራተኞች ናቸው። ”

“ የቀን ሠራተኞች በኮንስትራክሽን ዘርፉ ላይ ብዙ ጊዜ ጉልበታቸውን ነው ይዘው የሚገቡት፤ አደጋ ሊያጋጥም ይችላል የሚል ቴክኒካል እውቀት ላይ የተመሰረተ መረጃ የላቸውም።  እንዴት የሥራ ላይ አደጋን መከላከል እንደሚችሉ ስለጠና እንኳ አይሰጥም። ”

“ የቀን_ሠራተኞች_እንፈልጋለን  የሚሉ ማስታወቂያዎችን የኮንስትራክሽን ሳይቶች ላይ እናያለን። በዚያው ሥራ ያጣ መንገደኛ ይገባል ግን ሥራውን ለመከናውን ምን ሊያጋጥም ይችላል ? ብሎ አስቀድሞ የመገመት እውቀት አይኖርም። ”

“ ኮንትራክተሮችና ባለንብረቶች ላይ ትልቁ ኃላፊነት ይወድቃል። እነርሱ ደግሞ በሚፈለገው ደረጃ ለዘርፉ ትኩረት እየሰጡ አይደለም። አደጋ አጋጥሞ ስንደርስ እንኳ ቦታው_ላይ_አይገኙም። ፈቃድ ከወሰዱ በኋላ ግንባታው እስኪጠናቀቅ የደህንነት መርሆዎችን ያለመከተል ሁኔታ አለ። ”

መፍትሄውን ምንድነው ?

“ መፍትሄውማ ፈቃድ ሰጪው አካልም ፈቃድ ከሰጠ በኋላ በየጊዜው ጠብቅ ቁጥጥር በማድረግ ለአደጋ የተጋለጡ አሰራሮችን እየለዩ በህንጻ አዋጁ መሠረት እርምጃዎችን ቶሎ ቶሎ መውሰድ ያስፈልጋል። ”

ሰሞኑን የ7 ሰዎችን ህይወት የቀጠፈው የድንጋይ እና አፈር ናዳ አደጋ በኮንስትራክሽን ሥራ ላይ ባሉ ሠራተኞች ላይ ባለመድረሱ ለየት ያለ ቢሆንም ይህንኑ አደጋ ጨምሮ በ2016 ዓ/ም እስካሁን 12 ሰዎች በተለያዩ ጊዜዎችና አደጋዎች ሞተዋል። የሟቾች ቁጥር ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ጊዜ ጋር ሲነጻጸር ጨምሯል።

በድህረ ገጻችን ኢትዮ አማዞን በመግባት የሚፈልጉትን እቃ ማዘዝ  ብቻ  ሳይሆን የርስዎንም እቃዎች መሸጥ እንደሚችሉ ስናሳውቅዎት በደስታ ነው ። ለማስታወቂያ ወይንም ለመግቢያ ምንም ክፍያ አይጠበቅብዎትም፤  ለተጨማሪ መረጃ   ድህረ ገጻችንን ይጎብኙ። https://ethio-amazon.com/

ለበለጠ መረጃ ሊንኩን በመንካት የቴሌግራም ግሩፓችንን ይቀላቀሉ!https://t.me/ethioamazon

ምንጭ (Tikvah Ethiopia )

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Cart

Your Cart is Empty

Back To Shop