የኦስካር ሽልማት አሸናፊው እና ዝነኛው ተዋናይ ጂን ሃክማን፣ ባለቤቱ ቤትሲ አራካዋ እና ውሻቸው በመኖሪያ ቤታቸው ሞተው ተገኙ።
የጥንዶቹ እንዲሁም የውሻቸው አስከሬን በኒው ሜክሲኮ ግዛት በሚገኘው ሳንታ ፌ መኖሪያ ቤታቸው ተገኝቷል።
ከስድስት አስርት ዓመታት በላይ በተዋናይነት የተጫወተው ዝነኛው ሃክማን ‘ዘ ፍሬንች ኮኔክሽን’ ‘እንዲሁም ‘አንፎርጊቭን’ በተሰኙ ፊልሞቹ ዝናው ናኝቷል። በፊልሙ ዘርፍ ትልቅ ስፍራ የሚሰጠውን የኦስካር ሽልማት ሁለት ጊዜ ማሸነፍ ችሏል።
“ጥንዶቹ ጂን ሃክማን እና ባለቤቱ ረቡዕ ከሰዓት በኋላ ሰንሴት ትሬይል በተሰኘው መኖሪያ ስፍራቸው ሞተው ተገኝተዋል” ሲል የሳንታፌ ግዛት ፖሊስ ባወጣው መግለጫ አትቷል።
“በአሟሟታቸው ላይ ምርመራ የቀጠለ ቢሆንም እስካሁን መንስዔው ከተፈጥሯዊ ውጭ ነው ብለን አናምንም” ብሏል።
ተዋናዩ ጂን ዕድሜው 95 ነበር። የክላሲካል ፒያኖ ተጫዋች የነበረችው ባለቤቱ 64 ዓመቷ ነበር።
ተዋናዩ በአውሮፓውያኑ 1971 ለወጣው አስፈሪ ፊልም ‘ዘ ፍሬንች ኮኔክሽን’ ጂሚ በተሰኘ ገጸ ባህርይ ባሳየው ምርጥ ብቃት በምርጥ ተዋናይ ዘርፍ የኦስካር ሽልማትን ማሸነፍ ችሏል።
በአውሮፓውያኑ 1992 ‘አንፎርጊቭን’ ፊልም ላይ ባሳየው ብቃት ምርጥ ደጋፊ ተዋናይ በመሆን ሁለተኛውን ኦስካር ማሸነፍ ችሏል።
ከዚህም በተጨማሪ በአውሮፓውያኑ 1967 ‘ቦኒ ኤንድ ክላይድ’ በተሰኘ ፊልም፣ እንዲሁም በ1970ዎቹ ‘አይ ኔቨር ሳንግ ፎር ማይ ፋዘር፣ በአውሮፓውያኑ 1988 ሚሲሲፒ ላይ በተጫወታቸው ገጸ ባህርያት ለኦስካር ሽልማት ታጭቶ ነበር።
ሐክማን በፊልም ኢንዱስትሪው ዘርፍ ማንኛውንም ገጸ ባህርይ መጫወት ይችላል ይባላል።
ሐክማን በነዚህ ዓመታት ውስጥ ከ100 በላይ ገጸ ባህርያትን ወክሎ የተጫወተ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ በአውሮፓውያኑ 1970 እና 80ዎቹ የወጡት ሱፐርማን ፊልሞች ተጠቃሾች ናቸው።
ሐክማን ከታዋቂዎቹ አል ፓቺኖ፣ ጂን ዋይልደር፣ ዋረን ቤቲ እና ዲያን ኪተን ጋር ተጫውቷል። እንዲሁም በከፍተኛ ሁኔታ ታዋቂነትን ባገኙት ‘ራን አዌይ ጁሪ’፣ ‘ዘ ሮያል ቴኔን ባውምስ’ እና በታዋቂው ዳይሬክተር ፍታንሲስ ፎር ኮፖላ በተሰራው ‘ዘ ኮንቨርሴሽን’ ላይ ተጫውቷል።
ሐክማን በአውሮፓውያኑ 1930 በካሊፎርኒያ ነው ውልደቱ። ወላጆቹ ከከተማ ከከተማ ሲዘዋወሩም ነው የኖሩት።
በ16 ዓመቱ ዕድሜውን ዋሽቶ በአሜሪካ የባህር ኃይል ለአራት አመት ተኩል ያህል አገልግሏል። በቻይና፣ ሐዋይ እና ቻይና ተመድቦ የሰራ ሲሆን በ1951 ከባህር ኃይል ወጣ።
ወታደራዊ አገልግሎቱን ተከትሎ፣ ሐክማን የልጅነት ትወና ህልሙን ለማሳካት ወደ ካሊፎርኒያ ለመመለስ ከመወሰኑ በፊት በኒውዮርክ ኖሯል።
በኢሊኖይ ዩኒቨርሲቲ የጋዜጠኝነት እና የቴሌቪዥን ፕሮዳክሽን አጥንቶ በጋዜጠኝነት ስራ ዘርፍ ተሰማርቶ ነበር።
በድህረ ገጻችን ኢትዮ አማዞን በመግባት የሚፈልጉትን እቃ ማዘዝ ብቻ ሳይሆን የርስዎንም እቃዎች መሸጥ እንደሚችሉ ስናሳውቅዎት በደስታ ነው ። ለማስታወቂያ ወይንም ለመግቢያ ምንም ክፍያ አይጠበቅብዎትም፤ ለተጨማሪ መረጃ ድህረ ገጻችንን ይጎብ/ኙ። https://ethio-amazon.com/
ለበለጠ መረጃ ሊንኩን በመንካት የቴሌግራም ግሩፓችንን ይቀላቀሉ!https://t.me/ethioamazon
ምንጭ፡– (ቢቢሲ)