የአሜሪካ ምክር ቤት ሪፐብሊካኖች ለዩክሬን እና ለእስራኤል የታቀደውን እርዳታ አገዱ Leave a comment

የአሜሪካ የህግ መወሰኛ ምክር ቤት (ሴኔት) የሪፐብሊካን ፓርቲ አባላት የሀገራችን ድንበር ጸጥታ አልተጠበቀም በሚል በምላሹ ለዩክሬን እርዳታ ለመሰጠት የቀረበውን ረቂቅ አግደውታል።

አባላቱ ለዩክሬንና ለእስራኤልጋዛ እርዳታ የታቀደውን በድምሩ 110 ሚሊዮን ዶላር እርዳታ ነው ያገዱት።

ሪፐብሊካኖች ለዩክሬን የሚሰጠው ማንኛውም እርዳታ ከአሜሪካ የስደተኝነትና ጥገኝነት ጥያቄ ማሻሻያዎች ጋር እንዲያያዝ ጥብቅ ፍላጎት አላቸው።

የባይደን ጽህፈት ቤት ኋይት ሃውስ አሜሪካ ለዩክሬን የምታቀርበው እርዳታ በቅርቡ እንደሚሟጠጥ ገልጿል።

የአሜሪካ የህግ መወሰኛ ምክር ቤት (ሴኔት) አባላት ለመጽደቅ 60 ድምጽ የሚያስፈልገውን ረቂቅ የእርዳታ ሰነድ 51 49 በሆነ ድምጽ ውድቅ አድርጎታል።

ይህ ውሳኔ ለዩክሬን ወደፊት የሚቀርብ እርዳታ መኖሩ ላይ ጥያቄ ያስነሳ ሲሆን ለክረምት እረፍት አንድ ቀን ወደ የቀረው የአሜሪካ ምክር ቤት (ኮንግረስ) ተመልሶ ይላካል።

በሴኔቱ የሚገኙ ሁሉም የሪፐብሊካን አባላትና ገለልተኛ የምክር ቤት አባላት የሆኑት በርኒ ሳንደርስ የእርዳታ ዕቅዱን በመቃወም እጅ አንስተዋል።

በርኒ ሳንደርስ ቀደም ብለው የዩክሬን እና እስራኤል እርዳታ ላይ ጥያቄ እንዳለቸው ገልጸው ነበር።

የቀኝ አክራሪ ለሆነው የኔታኒያሁ መንግስት አሁን የያዘውን የጦርነት መንገድ እንዲቀጥል 10 በሊዮን ዶላር የዘለለ እርዳታ ማቅረብ አለብን ብዬ አላምንምሲሉ ተደምጠዋል።

የምክር ቤት አባሉ የኔታኒያሁ የአሁኑ የጦርነት አካሄድ በሺ የሚቆጠሩ ሲቪል ሰዎችን ለሞት ዳርጓል ብለዋል።

ለረጀም ጊዜ ኔታኒያሁን በመቸት የሚታወቁት እኚሁ የምክር ቤት አባል የእስራኤል መንግሥት የሚያደርገው ነገር ያልተገባና ዓለም አቀፍ መርኾችን የጣሰ ነው ያሉ ሲሆን ሀገራቸው አሜሪካ ይህንን መደገፍ እንደሌለባትም ተናግረዋል።

የእርዳታ ሰነዱ ለምክር ቤት ከመቅረቡ አስቀድሞ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት እርዳታውን ለማጽደቅ የአሜሪካ ድንበሮች ላይ መሰረታዊ ለውጥ እንደሚያመጡ ተናግረው ነበር።

ጨምረውምሪፐብሊካኖች ፑቲን በተስፋ የሚጠብቀውን ስጦታ ለመስጠት ዝግጁ ናቸውብለዋል።

በሌላበኩል ትላንት የባይደን አስተዳደር ቀደም ብሎ የጸደቀውን ለዩክሬን እርዳታ የሚውል 175 ሚሊዮን ዶላር እርዳታ አጽድቋል።

ይህ እርዳታ ለዩክሬን የተለያዩ የጦር መሳሪያዎችን ለማቅረብ የሚያስችል ነው ተብሏል።

ቀደም ሲል የህግ መወሰኛ ምክር ቤቱ አባላት የድንበር ጥበቃን በተመለከተ እርስ በእርሳቸው ሲጯጯሁ የታዩ ሲሆን በርካታ ሪፕሊካኖች ስብሰባውን ረግጠው ወጥተዋል።

በቂ ማብራሪያ ባይሰጥም የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ዜለንስኪ በበይነ መረብ አማካይነት ከአሜሪካ ህግ አውጪዎች ጋር በመጨረሻ ሰዓት መነጋገራቸው ተሰምቷል።

የቀረበው በጀት የድንበር ጥበቃን በጀትን ቢያካትትም ሪፐብሊካኖች የጥገኝነት ጠያቂዎች ሁኔታ ላይ ህግ እንዲወጣ ይፈልጋሉ።

ረቂቅ ህጉ ውድቅ መሆኑን ተከትሎ የዩክሬን ፕሬዝደንት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አንድሪ ዬርማርክ በአሜሪካ የሰላም ኢንስቲትዩት ተገኝተው ባደረጉት ንግግር አሜሪካ ለዩክሬን ተጨማሪ እርዳታ ማቅረብ አልቻለችም ማለትጦርነቱን የመሸነፍ ከፍተኛ ዕድል አለማለት ነው ብለዋል።

በተጨማሪም ዩክሬን በሩስያ የተወሰዱባትን ግዛቶች ማስለመለስ ከማትችልበት ደረጃ ትደርሳለች ሲሉም አክለዋል።

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Cart

Your Cart is Empty

Back To Shop