የኢራን መንግሥትን የተቃወመው ራፐር ሞት እንደተፈረደበት ጠበቃው ተናገረ Leave a comment

መንግሥትን የሚቃወሙ እንቅስቃሴዎችን በመደገፍ የታሰረው ኢራናዊ ራፐር በሞት እንዲቀጣ በፍርድ ቤት ውሳኔ መተላለፉን ጠበቃው ገለጸ።

ቱማጂ ሳሊህ የተባለው ሙዚቀኛ ከሁለት ዓመታት በፊት በኢራን የተቀሰቀሰውን ተቃውሞ በመደገፍ የራፕ ሙዚቃ አውጥቶ ነበር።

በወቅቱ በመላው ሀገሪቱ ማሻ አሚኒ የተባለች ሴት ሂጃብ በአግባቡ አልለበሽም በሚል በፖሊስ ቁጥጥር ስር እያለች ህይወቷ ማለፉን ተከትሎ አገሪቷን ያናወጠ ከፍተኛ ተቃውሞ ተቀስቅሶ ነበር።

ሙዚቀኛውም ይህንን ድርጊት የሚኮንን የራፕ ዘፈን አውጥቶ ነበር።

ከሙዚቀኛው ጠበቆች አንዱ የሆነው አሚር ሬሲያን ራፐሩ የተላለፈበትን ብይን በመቃወም ይግባኝ እንደሚጠይቅ ገልጿል።

በዚህ ጉዳይ ከኢራን መንግሥት በኩል የተባለ ነገር የለም።

ሙዚቀኛው ሳሊህ ከሁለት ዓመት በፊት ጥቅምት ወር በተሰበሰቡ ሰዎች ፊት የሚደረገውን ተቃውሞ በመደገፍ ንግግር ሲያደርግ ተይዞ በርካታ ክሶች ተመስርተውበታል።

ባለፈው ዓመት ሐምሌ ወር ላይ በጠቅላይ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ መሰረት ስድስት ዓመት ከ3 ወር እንዲታሰር ተወስኖ ነበር።

ሆኖም በዚህ ዓመት ጥር ላይ የኢራን አብዮታዊ ፍርድ ቤት በሙዚቀኛው በተመሰረቱት ክሶች ላይ አዲስ በመጨር ለፍርድ አቁሞታል ሲል ጠበቃው ለቢቢሲ ተናግሯል።

ሻራቅ ለተባለ የሀገር ውስጥ ጋዜጠኛ ትናንት ረቡዕ አስተያየቱን የሰጠው ጠበቃው ሬሲያን አቢዮታዊ ፍርድ ቤቱ የጠቅላይ ፍርድ ቤቱን ውሳኔ ወደ ጎን ማለቱን ተናግሯል። ይህንን “አስከፊ ቅጣት” ከማስተላለፋቸው በፊት አዲስ ክስ እንደተመሰረተበትም ጠቁሟል።

ሙዚቀኛው በትጥቅ በታገዘ አመጽ እና መንግሥት ላይ ፕሮፓጋንዳ በማሰራጨት ከቀረቡበት ክሶች አንዱ እንደሆነም ተናግሯል።

ሙዚቀኛው ይግባኝ የመጠየቂያ 20 ቀናት ተሰጥቶታል።

ሙዚቀኛው ሳሊህ በቅርቡ ከተቀሰቀው ተቃውሞ ቀደም ብሎም መንግስትን በአደባባይ በመተችት ይታወቃል። በዚህም ሳቢያ በኢራን መንግሥት የተለያዩ ሙዚቃ ድግሶች ላይ እንዳይሳተፍ ታግዷል። በዚህም የተነሳ ሙዚቀኛው ስራዎቹን በማህበራዊ ሚዲያዎች ብቻ ለማጋራት ተገዶ ነበር።

በሙዚቃ ስራዎቹም መንግሥትን በሙስና እና ሰላማዊ እንቅስቃሴዎችን በመገደብ አጥብቆ ተችቷል።

በሐምሌ ወር ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ 6 ዓመት ከተፈረደበት በኋላ በዋስ ተለቆ ነበር።

ሆኖም መንግሥት ላይ ያለበቂ ማስረጃ ሐሰተኛ ውንጀላዎችን በማቅረብ በሚል በተለቀቀ በቀናት ውስጥ ታስሯል። ይህ የሆነው በእስር ላይ እያለ ስቃይ እና እንግልት ደርሶብኛል የሚል ቪዲዮ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ከጫነ በኋላ ነው።

በቅርቡ በኢራን ጎዳናዎች ከፍተኛ የፖሊስ ስምሪት ይታያል። ይህም ሴቶች በእስላማዊ ህግ መሰረት ልብስ መልበሳቸውን ለመከታተል ነው።

በድህረ ገጻችን ኢትዮ አማዞን በመግባት የሚፈልጉትን እቃ ማዘዝ  ብቻ  ሳይሆን የርስዎንም እቃዎች መሸጥ እንደሚችሉ ስናሳውቅዎት በደስታ ነው ። ለማስታወቂያ ወይንም ለመግቢያ ምንም ክፍያ አይጠበቅብዎትም፤  ለተጨማሪ መረጃ   ድህረ ገጻችንን ይጎብኙ። https://ethio-amazon.com/

ለበለጠ መረጃ ሊንኩን በመንካት የቴሌግራም ግሩፓችንን ይቀላቀሉ!https://t.me/ethioamazon

ምንጭ ( ቢቢሲ ዜና )

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Cart

Your Cart is Empty

Back To Shop