ዩክሬን በአሜሪካ የጦር መሣሪያ በሩሲያ የሚገኙ ዒላማዎችን እንድትመታ ባይደን ፈቀዱ Leave a comment

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን፣ ዩክሬን ሩሲያ ውስጥ ያሉ ዒላማዎችን በአሜሪካን የጦር መሣሪያ እንድትመታ ፈቃድ ሰጡ።

ዒላማዎችን መምታት የምትችለው በካርኪቭ አካባበቢ ብቻ እንደሆነ ተገልጿል።

አንድ የአሜሪካ ባለሥልጣን ለቢቢሲ እንደገለጹት፣ ዩክሬን የአሜሪካን መሣሪያን “መልሶ ለማጥቃት” እንድትጠቀም እንዲያስችሉ ትዕዛዝ ተሰጥቷቸዋል።

“እያጠቃቸው ያለውን የሩሲያ ኃይል መልሶ ለማጥቃት” የጦር መሣሪያዎቹ እንደሚውሉ አክለዋል።

ባለፉት ጥቂት ሳምንታት በካርኪቭ ግዛት የሩሲያ ኃይሎች ከፍተኛ ጥቃት ፈጽመው አካባቢዎችን መቆጣጠር ጀምረዋል።

አካባቢው በሩሲያ እና ዩክሬን ድንበር አቅራቢያ ነው።

በከተማው ላይ በደረሰ ጥቃት ሦስት ሰዎች እንደተገደሉና 16 ሰዎች እንደቆሰሉ የዩክሬን ባለሥልጣናት ገልጸዋል።

የአሜሪካው ባለሥልጣን እንዳሉት አሜሪካ በሩሲያ ላይ “የሚሳዔል መሣሪያ እና የረዥም ርቀት መሣሪያ ላለመጠቀም” የያዘችውን አቋም አልቀየረችም።

የቢቢሲ የአሜሪካ አጋር ሲቢኤስ ያነጋገራቸው የአሜሪካ ባለሥልጣን የሩሲያ የጦር አውሮፕላን መምታትን አዲሱ የአሜሪካ ፖሊስ አካል እንደሆነ ተጠይቀዋል።

“ዩክሬናውያን ሊያጠቃቸው እየመጣ ያለን የሩሲያ አውሮፕላን በሩሲያ ሰማይ ላይ መትተው እንዳይጥሉ አልነገርናቸውም” ብለዋል።

ዩናይትድ ኪንግደም፣ ዩክሬን እንዴት ከምዕራባውያን የተሰጣትን መሣሪያ እንደምትጠቀም የወጣው መርኅ እንደሚላላ ገልጻለች። ሌሎች የአውሮፓ መሪዎችም ተመሳሳይ ውሳኔ እንዲተላለፍ ጠይቀዋል።

አሜሪካ እስካሁን መርኅ የማላላት ፍላጎት ባታሳይም፣ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ኃላፊ አንቶኒ ብሊንከን አሜሪካም ውሳኔዋን እንደምታላላ ገልጸዋል።

“እንደየአስፈላጊነቱ አካሄዳችንን እንለውጣለን” ሲሉ ብሊንከን ተናግረዋል።

እነዚህ ውሳኔዎች ግጭቱን የበለጠ እንደሚያባብሱት ስጋት አለ።

ዩክሬን ከምዕራባውያን ተጨማሪ መሣሪያ እየጠበቀች ሳለ ሩሲያ የበለጠ ይዞታዋን ማስፋፋት ችላለች።

ባለፈው ሳምንት መደብር ላይ በደረሰ ጥቃት 12 ሰዎች ተገድለዋል።

የካርኪቭ አገረ ገዢ ኦሌህ ሲንሆቦቭ እንዳሉት፣ አምስት ሕንጻ ያለው ፎቅ ላይ ጥቃት ተፈጽሟል። ሕንጻው ሲወድም እሳትም ተነስቷል ብለዋል።

የሩሲያ ኃይሎች “ንጹኃን የሚገለገሉበትን መሠረተ ልማት ዒላማ አድርገዋል” ሲሉም ከሰዋል።

በድህረ ገጻችን ኢትዮ አማዞን በመግባት የሚፈልጉትን እቃ ማዘዝ  ብቻ  ሳይሆን የርስዎንም እቃዎች መሸጥ እንደሚችሉ ስናሳውቅዎት በደስታ ነው ። ለማስታወቂያ ወይንም ለመግቢያ ምንም ክፍያ አይጠበቅብዎትም፤  ለተጨማሪ መረጃ   ድህረ ገጻችንን ይጎብኙ። https://ethio-amazon.com/

ለበለጠ መረጃ ሊንኩን በመንካት የቴሌግራም ግሩፓችንን ይቀላቀሉ!https://t.me/ethioamazon

ምንጭ ( ቢቢሲ ዜና )

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Cart

Your Cart is Empty

Back To Shop

የሚፈልጉትን ይዘዙን

Order what you want