ዶ/ር ሳምሶን ይስሀቅ ላጋጠመው የጤና እክል መታከሚያ ደጋግ ኢትዮጵያውያን እንዲተባበሩት ጠየቀ። Leave a comment

” የተጠየቀው የህክምና ወጪው በመንግሥት የሀኪም ደመወዝ እና በቤተሰቦቼ አቅም የሚቻል አይደለም ” – ዶ/ር ሳምሶን ይስሀቅ

ዶ/ር ሳምሶን ይስሀቅ ላጋጠመው የጤና እክል መታከሚያ ደጋግ ኢትዮጵያውያን እንዲተባበሩት ጠየቀ።

ዶክተሩ 2015 ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል በህክምና ሙያ ትምህርት ነው የተመረቀው።

ከተመረቀ በኃላም ለ6 ወራት በጠቅላላ ሀኪምነት ወገኑን ሲያገለግል ቆይቷል።

በድንገት ግን ሚዛኑን ስቶ መውደቅ እና ሌሎችም ምልክቶችን በማሳየቱ ወደ ጤና ተቋም ሄዶ ምርመራ ካደረገ በኋላ ‘ የጭንቅላት እጢ ‘ እንዳለበት ተነግሮታል። የናሙና ምርመራ ተደርጎ ‘ GradeIII Astrocytoma ‘ እንዳለበት ተገልጾለታል።

” ትልቅ ቦታ ደርሼ ማየት ለሚመኙት ቤተሰቦቼና ከኔ በታች ላሉት እህት ወንድሞቼ ዜናው በጣም ትልቅ ዱብዳ ነው የሆነባቸው ” ያለው ዶክተር ይስሃቅ ” የጥቁር አንበሳ የጭንቅላት ቀዶ ጥገና ሀኪሞች ወደ ውጪ ሀገር ሄጄ ህክምና ማድረግ እንዳለብኝ ወስነዋል ” ሲል ገልጿል።

ለህክምናው ወጪው እስከ 👉 2.3 ሚሊዮን ብር  እንደሚያስፈልግም እንደተነገረው አስረድቷል።

ይህን ከፍተኛ ወጪ በመንግስት ሰራተኛ የሀኪም ደሞዝም ሆነ በቤተሰቦቹ አቅም የሚቻል ባለመሆኑ ሁላችሁም የቻላችሁትን እንድትረዱት ተማጽኗል።

ዶ/ር ይስሃቅ ” በየሃይማኖታችሁ ፈጣሪ በመንገዴ ሁሉ እንዲረዳኝ በጸሎታችሁ አስቡኝ ” ሲልም ጠይቋል።

ከዶክተሩ የተላከ የህክምና ማስረጃን መመልከት የቻልን ሲሆን  ወላጅ እናቱን ብርሃኔ በየነን በስልክ ቁጥ ር +251911353752 ደውሎ ማነጋገር ይቻላል።

እገዛ ለማድረግ የምትፈልጉ ፦

ዶክተር ሳምሶን ይስሃቅ በየነ

ንግድ ባንክ ፦ 1000139965691

አዋሽ ባንክ ፦ 013201172039000

ብርሃኔ በየነ ሚደቅሳ (እናት)

ንግድ ባንክ ፦ 1000549927681

አዋሽ ባንክ ፦ 01347903970500

 

በድህረ ገጻችን ኢትዮ አማዞን በመግባት የሚፈልጉትን እቃ ማዘዝ  ብቻ  ሳይሆን የርስዎንም እቃዎች መሸጥ እንደሚችሉ ስናሳውቅዎት በደስታ ነው ። ለማስታወቂያ ወይንም ለመግቢያ ምንም ክፍያ አይጠበቅብዎትም፤  ለተጨማሪ መረጃ   ድህረ ገጻችንን ይጎብኙ። https://ethio-amazon.com/

ለበለጠ መረጃ ሊንኩን በመንካት የቴሌግራም ግሩፓችንን ይቀላቀሉ!https://t.me/ethioamazon

ምንጭ(@tikvahethiopia)

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Cart

Your Cart is Empty

Back To Shop