ዜጎችን ለስራም ሆነ ለትምህርት ወደ ውጭ ሀገር የመላክ ፍቃድ ለስራና ክህሎት ሚኒስቴር ብቻ የተሰጠ ሃላፊነት መሆኑን ሚኒስቴሩ ገልጿል።
በዚህ ጉዳይ በሚኒስቴሩ የውጭ ሀገር ስራ ስምሪት የኤጀንሲዎች ፈቃድ መስጫ ዴስክ ሃላፊ አቶ ተክሌ ተስፉ ለመናኸሪያ ሬዲዮ 99.1 ቃላቸውን ሰጥተው ነበር።
” አሁን ላይ በተለያዩ ከተሞች በተለይ በአዲስ አበባ ከተማ የተለያዩ ኤጀንሲዎች ሰዎችን ‘ ካናዳ እና ወደ ሌሎችም የውጭ ሀገራት ስራ እናስቀጥራችኃለን ‘ በሚል የሚያስተላለፉት ማስታወቂያ ፈጽሞ ፈቃድ የሌለው እና ህገ ወጥ ነው ‘ ብለዋል።
ይህን ስራ በሚሰሩት ላይ በጥቆማና በፍለጋ ሲደረስባቸው እርምጃ እንደሚወሰድባቸው ገልጸዋል።
” ለኤጀንሲዎች ፈቃድ መስጠቱንም ሆነ መቆጣጠሩንም የሚመለከተው የመንግስት ተቋም ስራና ክህሎት ሚኒስቴር ነው ” ሲሉ ገልጸዋል።
በፌደራልም በክልልም ያሉ ኤጀንሲዎች በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ፈቃድ ከተሰጣቸው ብቻ ስራው ላይ መሰማራት እንደሚችሉ አስገንዝበዋል።
በአዲስ አበባ እና በክልል ከተሞች እየተበራከቱ መጥተዋል ያሏቸው ህገ ወጥ ኤጀንሲዎችን በጥብቅ ክትትልና ቁጥጥር እርምጃ እንደሚወሰድባቸው አስጠንቅቀዋል።
ዜጎችን ያለ ፍቃድ ” ወደ ውጭ እንልካለን ” የሚሉ ህገ ወጦች ምንም አይነት እውቅና የሌላቸው መሆኑን ህብረተሰቡ እንዲረዳው ሲሉ ለሬድዮ ጣቢያው (መናኸሪያ 99.1 ኤፍ ኤም) በሰጡት ቃል አስገንዝበዋል።
በድህረ ገጻችን ኢትዮ አማዞን በመግባት የሚፈልጉትን እቃ ማዘዝ ብቻ ሳይሆን የርስዎንም እቃዎች መሸጥ እንደሚችሉ ስናሳውቅዎት በደስታ ነው ። ለማስታወቂያ ወይንም ለመግቢያ ምንም ክፍያ አይጠበቅብዎትም፤ ለተጨማሪ መረጃ ድህረ ገጻችንን ይጎብኙ። https://ethio-amazon.com/
ለበለጠ መረጃ ሊንኩን በመንካት የቴሌግራም ግሩፓችንን ይቀላቀሉ!https://t.me/ethioamazon
ምንጭ ፡-(@tikvahethiopia)