የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ኃላፊ አንቶኒ ብሊንከን፣ የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በዩክሬን ያወደሙትን ለመጠገን መክፈል አለባቸው አሉ።
በዩክሬን፣ ኪየቭ ውስጥ ባደረጉት ንግግር አሜሪካ በግዛቷ ያሉ የሩሲያ ኃብት ንብረቶች ላይ ማዕቀብ የመጣል አቅም እንዳላት ገልጸዋል።
እነዚህን ኃብት ንብረቶች ዩክሬንን መልሶ ለመገንባት እንደሚያውሉም አክለዋል።
ዩክሬን “ለኔቶ እየቀረበች ነው” ሲሉ ተናግረዋል። ለዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ ወታደራዊ ዕርዳታ “መንገድ ላይ ነው” ብለዋል።
“ፑቲን ያወደመውን ሩሲያ መክፈል አለባት። ዓለም አቀፍ ሕግ ያንን ያዛል። የዩክሬን ሕዝብም መልሶ ግንባታው ይገባዋል” ሲሉ ብሊንከን በኪየቭ ፖሊቴክ ዩኒቨርስቲ ባደረጉት ንግግር ጠቁመዋል።
የአሜሪካ ኮንግረስ በሰጠው ይሁንታ መሠረት የሩሲያ ኃብት ንብረቶች ላይ ማዕቀብ ለመጣል ማቀዳቸውንም አሳውቀዋል።
የቡድን 7 አገራት በቢሊዮን የሚቆጠር ዶላር ፈሰስ በማድረግ “ፑቲን ጊዜ ከጎኑ እንዳልቆመ እንዲያውቅ” ያደርጋሉ ሲሉ አክለዋል።
ዩክሬን ከሁለት ዓመት በፊት ከተወረረች ወዲህ በአውሮፓ ያሉ ወደ 181 ቢሊዮን ዶላር የሚያወጡ የሩሲያ ኃብቶች ላይ ማዕቀብ ተጥሏል።
ሩሲያ በዩክሬን ሁለተኛ ትልቁ ከተማ በሆነው ካርኪቭ ጥቃት በሰነዘረችበት ወቅት ነው ብሊንከን ጉብኝቱን ያካሄዱት።
የአሜሪካ ምክር ቤት ከሦስት ሳምንታት በፊት 61 ቢሊዮን ዶላር ለዩክሬን ለመላክ ስምምነት ላይ ደርሷል።
“ከመቼው በላይ ዩክሬንን ከኔቶ ጋር እያቀራረብን ነው። ከኔቶ ጋር ያላት ትስስር ጥብቅ እንዲሆን እናደርጋለን” ብለዋል።
ለዩክሬን ሕዝብ “ብቻችሁን አይደላችሁም። ሁሌም ከጎናችሁ ነን” የሚል መልዕክት አስተላልፈዋል።
ሩሲያ አዲስ የከፈተችው ጥቃት ላይ ቻይና፣ ኢራን እና ሰሜን ኮርያ እጃቸው እንዳለበት ተገልጿል።
የሩሲያን ወታደሮች የሚመክቱ ወታደሮች ስለማሰማራትም ብሊንከን ተናግረዋል።
ዩክሬን የወሰደቸው እርምጃ አስፈላጊ እንደሆነ በንግግራቸው ጠቅሰዋል።
ከዘለንስኪ ጋር ሲገናኙ “ዩክሬን ላሳየችው ታላቅ ፅናት” እንዲሁም ለፕሬዝዳንቱ “ጥንካሬና የአመራር ብቃት” ያላቸውን ክብር ገልጸዋል።
“ጊዜው ከባድ ቢሆንም የአሜሪካ እርዳታ እየመጣ ነው። በጦር ሜዳም ልዩነት ያመጣል” ብለዋል።
በድህረ ገጻችን ኢትዮ አማዞን በመግባት የሚፈልጉትን እቃ ማዘዝ ብቻ ሳይሆን የርስዎንም እቃዎች መሸጥ እንደሚችሉ ስናሳውቅዎት በደስታ ነው ። ለማስታወቂያ ወይንም ለመግቢያ ምንም ክፍያ አይጠበቅብዎትም፤ ለተጨማሪ መረጃ ድህረ ገጻችንን ይጎብኙ። https://ethio-amazon.com/
ለበለጠ መረጃ ሊንኩን በመንካት የቴሌግራም ግሩፓችንን ይቀላቀሉ!https://t.me/ethioamazon
ምንጭ ( ቢቢሲ ዜና )
ነው። በጦር ሜዳም ልዩነት ያመጣል” ብለዋል።