ሩዋንዳ 4 ሺህ ቤተ ክርስቲያናትን ከደህንነነት ጋር በተያያዘ ዘጋች…… Leave a comment

ሩዋንዳ የአገሪቱን የጤና እና የደህንነት ደንቦችን የጣሱ ከ4 ሺህ በላይ ቤተ ክርስትያናትን መዝጋቷን አስታወቀች።

ባለፈው ወር የተዘጉት እነዚህ ቤተ ክርስቲያናት የድምጽ መከላከያ መግጠምን ጨምሮ ደንቦችን ተላልፈው ተገኝተዋል ተብሏል።

በአብዛኛው የተዘጉት ቤተ ክስርቲያናት የፕሮቴስታንት ሲሆኑ በወንዞች ዳርቻ አካባቢ ያሉ ውስን መስጊዶች ተካትተውበታል።

“እንዲህ አይነት እርምጃ የተወሰደው ማህበረሰቡ ጸሎታቸውን እንዳያከናውኑ ለመከልከል ሳይሆን የምዕመናኑን ደህንነት እና ጸጥታ ለማረጋጋጥ ነው” ሲሉ የአካባቢው አስተዳዳሪ ዣን ክላውድ ሙሳብይማና ለመንግሥት ሚዲያ ተናግረዋል።

አንዳንዶቹ የተዘጉ ቤተ ክርስቲያኖች በድንኳን የተተከሉ እንዲሁም ንጽህና የጎደላቸው ሲሆን ይህም ምዕመናኑን ለአደጋ ያጋለጠ መሆኑን አስተዳዳሪው ዣን ክላውድ ተናግረዋል።

በሩዋንዳ የአምልኮ ስፍራዎች መስፋፋትን የሚቆጣጠረው ህግ ከአምስት ዓመት በፊት ከወጣ በኋላ የአሁኑ የመጀመሪያው ትልቅ እርምጃ ነው።

የአምልኮ ስፍራዎቹ በተደራጀ እና አስተማማኝነቱ በተጠበቀ አካባቢ እንዲሰሩ እንዲሁም ህዝብን የሚያውክ ከፍተኛ ድምጽን ይከለክላል።

በተጨማሪም ህጉ ሁሉም ሰባኪዎች ቤተ ክርስቲያን ከማቋቋማቸው በፊት የሃይማኖት ትምህርት ስልጠናዎችን እንዲወስዱ ያስገድዳል።

ህጉ በጸደቀበት በአውሮፓውያኑ 2018 ወደ 700 የሚጠጉ ቤተ ክርስቲያናት ተዘግተው ነበር።

በወቅቱም የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ፖል ካጋሜ አገሪቱ በርካታ የአምልኮ ስፍራዎች አያስፈልጋትም ብለዋል።

ይህንን ያህል ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የእምነት ስፍራዎች የሚያስፈልጉት አገልግሎታቸውን ለማስቀጠል ለሚችሉት ለበለጸጉ ኢኮኖሚዎች ነው ሲሉም ተደምጠዋል።

በቅርቡ አገሪቱ ባደረገችው ምርጫ 99 በመቶ ድምጽ በማግኘት ለአራተኛ ጊዜ አገሪቱን ለመምራት ያሸነፉት ካጋሜ ተቺዎቻቸውን በማፈን እንዲሁም ማህበረሰቡ ላይ ጥብቅ ቁጥጥር በመጫን ይወቀሳሉ።

አገሪቱ በአምልኮ ስፍራዎች ላይ እየወሰደችው ያለው እርምጃ በከተማ አስተዳደሮች ከሩዋንዳ አስተዳደር ቦርድ (አርጂቢ) ጋር በተመባበር እየተተገበረ ይገኛል።

ቤተ ክርስቲያናቱ እነዚህን ደንቦች ተግባራዊ ለማድረግ የባለፉት አምስት ዓመታት የነበራቸው መሆናቸውን ባለስልጣናቱ ጠቁመው የአሁኑ ከበድ ያለ ውሳኔ ትክክለኛ ነው ብለዋል።

በድህረ ገጻችን ኢትዮ አማዞን በመግባት የሚፈልጉትን እቃ ማዘዝ  ብቻ  ሳይሆን የርስዎንም እቃዎች መሸጥ እንደሚችሉ ስናሳውቅዎት በደስታ ነው ። ለማስታወቂያ ወይንም ለመግቢያ ምንም ክፍያ አይጠበቅብዎትም፤  ለተጨማሪ መረጃ   ድህረ ገጻችንን ይጎብ/ኙ። https://ethio-amazon.com/

ለበለጠ መረጃ ሊንኩን በመንካት የቴሌግራም ግሩፓችንን ይቀላቀሉ!https://t.me/ethioamazon

ምንጭ፡– (ቢቢሲ)

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Cart

Your Cart is Empty

Back To Shop