የስዊድን ፓርላማ ፆታን በሕጋዊ መንገድ የመቀየሪያን እድሜ ከ18 ወደ 16 ዝቅ በማድረግ ሂደቱን የሚያቀል ህግ አጸደቀ።
ህጉ በ234 የድጋፍ ድምጽ እና በ94 ተቃውሞ ነው የጸደቀው።
ምንም እንኳን ስዊድን ጾታ መቀየርን በአውሮፓውያኑ 1972 ህጋዊ ለማድረግ የመጀመሪያዋ ሃገር ብትሆንም አዲሱ ህግ ከበድ ያለ ክርክር ማስነሳቱ አልቀረም።
አንዳንዶች ህጉ ጠቃሚ ለውጥ እንደሚያመጣ አስተያያታቸውን ቢሰጡም ተቺዎች ግን ተጨማሪ ጥናት እንደሚያስፈልግ ነው የተናገሩት።
በአሁኑ ጊዜ ጾታቸውን መቀየር የሚፈልጉ ስዊድናውያን ያላቸው ጾታ የራሳቸው እንዳልሆነ የሚሰማቸው፣ ጄንደር ዲስፎሪያ ያለባቸው መሆኑን የዶክተር ምርመራ ማረጋገጫ ማግኘት አለባቸው።
ነገር ግን በመጪው ዓመት ሐምሌ ወር ላይ ተግባራዊ በሚሆነው አዲስ ህግ ሂደቱ የቀለለ እንደሚሆን ተገልጿል።
ከብሔራዊ የጤና እና ደህንነት ቦርድ ፈቃድ እንዲሁም ከዶክተር ወይም ከስነልቦና ሙያ ጋር አጭር ምክክር በቂ ይሆናል።
በህጋዊ መንገድ ጾታ መቀየር ከ16 ዓመት ጀምሮ ቢቻልም እነዚህ ታዳጊዎች የወላጆቻቸውን ወይም የአሳዳጊዎቻቸውን ፈቃድ፣ የዶክተር እና የብሄራዊ ጤና እና ደህንነት ቦርድ ይሁንታ ያስፈልጋቸዋል።
አዲሱ ህግ፣ ህጋዊ ጾታ መቀየርን እና የቀዶ ህክምና ጾታ መቀየር በሚል የከፋፈለ ሲሆን ቀዶ ህክምና ለማድረግ ረዘም ያለ ግምገማ የሚያስፈልግ ሲሆን የሚፈቀደው ከ18 ዓመት ዕድሜ ጀምሮ ብቻ ነው።
“ጾታን በህጋዊ መንገድ ለመቀየር እና ሙሉ በሙሉ በማይመለስ መልኩ በቀዶ ህክምና ጾታን መለወጥ ላይ የተቀመጡት መስፈርቶች ተመሳሳይ መሆናቸው ምክንያታዊ አይደለም” ሲሉ የገዥው ፓርቲ አባል ዮሃን ሃልበርግ በፓርላማ ለስድስት ሰዓታት በፈጀው ክርክር ተናግረዋል።
አክለውም “አብዛኞቹ ስዊድናውያን ሕጉ መቀየሩን ፈጽሞ ላያስተውሉ ይችላሉ ነገር ግን ለበርካታ ትራንስጀንደር(ጾታቸውን ለቀየሩ ሰዎች) አዲሱ ህግ ትልቅ እና ጠቃሚ ለውጥ ያመጣል” ብለዋል።
ነገር ይህ አዲሱ ህግ በቀኝ አክራሪዎች ዘንድ ተቀባይነት አላገኘም።
በገዥው መንግሥት ጥምረት ውስጥ ያሉት የክርስቲያን ዴሞክራቶች ፓርቲ እና የቀኝ አክራሪው፣ ፋር ላይ ስዊድን ዴሞክራትስ ፓርቲ ህጉን አልደገፉም። በርካታ የፓርላማ አባላት በመጀመሪያ ጾታ የራሳቸው እንዳልሆነ በሚሰማቸው፣ ጄንደር ዲስፎሪያ ላይ ተጨማሪ ምርምራ እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።
የስዊድን ዴሞክራት ፓርቲ መሪ ጂሚ አኬሰን በህዝብ ድጋፍ የሌለው ህግ መጽቀዱ አሳዛኝ እንደሆነ ነው የገለጹት።
የስዊድን ጠቅላይ ሚኒስትር ኡልፍ ክሪስቴርሰን በበኩላቸው ህጉን ደግፈው የተከራከሩ ሲሆን “ሚዛናዊ እና ኃላፊነት” የተሞላበት ነው ሲሉ አወድሰውታል።
በድህረ ገጻችን ኢትዮ አማዞን በመግባት የሚፈልጉትን እቃ ማዘዝ ብቻ ሳይሆን የርስዎንም እቃዎች መሸጥ እንደሚችሉ ስናሳውቅዎት በደስታ ነው ። ለማስታወቂያ ወይንም ለመግቢያ ምንም ክፍያ አይጠበቅብዎትም፤ ለተጨማሪ መረጃ ድህረ ገጻችንን ይጎብኙ። https://ethio-amazon.com/
ለበለጠ መረጃ ሊንኩን በመንካት የቴሌግራም ግሩፓችንን ይቀላቀሉ!https://t.me/ethioamazon
ምንጭ ፡-(BBC)