በአንድ ጨዋታ 31 ግቦች የተቆጠሩበት ግብ ጠባቂ Leave a comment

በእግር ኳስ ጨዋታ ላይ ሁሉም ተሰላላፊዎች ለቡድኑ ድል እና ሽንፈት ኃላፊነት ቢኖርባቸውም፣ የግብ ጠባቂን ያህል ግን የጎላ አይሆንም። በተለይ ደግሞ አንድ ቡድን በርካታ ግቦች ተቆጥረውበት ሲሸነፍ የሁሉም ዐይን የሚያርፈው በረኛ ላይ ነው። ታዲያ በአንድ ጨዋታ ከሦስት አስሮች በላይ ጎለረ ያስተናገደ በረኛ ምን ይሰማው ይሆን?

ሚያዝያ ወር ላይ እአአ 2001 በተካሄደ ጨዋታ የአሜሪካን ሳሞአ ግብ ጠባቂ 31 ግቦች ተቆጥረውበት በታሪክ በሰፊ የግብ ልዩነት የተጠናቀቀ ጨዋታ ሆኖ ተመዝግቧል።

ሳላፑ ስለዚያ ማስታወስ ስለማይፈልገው ቀን ለመጀመሪያ ጊዜ ለቢቢሲ አስተያየቱን ሰጥቷል።

ውድድሩ የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ነበር። አሜሪካን ሳሞአ በምድቧ ከአውስትራሊያ ጋር ተደላድላለች።

አሁን ላይ የ43 ዓመት ጎልማሳ የሆነው ሳላፑ ሁኔታውን ሲያስታውስ 31 ለ 0 የተሸነፉበት ጨዋታ ገና ሳይጠናቀቅ ከቡድን አጋሮቹ ተደብቆ ማልቀስ ጀምሮ እንደነበር ይናገራል።

“ጨዋታው እስኪጠናቀቅ ስሜታዊ ላለመሆን ሞክሬ ነበር። ግን አልተሳካም” ይላል።

አሜሪካን ሳሞአ በታሪክ ትልቁን ሽንፍት እንድታስተናግድ የሆነችባቸው ምክንያቶች አሉ ይላል የብሔራዊ ቡድን ጠባቂው ሳላፑ።

በወቅቱ የአሜሪካን ሳሞአ ሕዝብ ቁጥር 58 ሺህ ብቻ ነበር። የአውስራሊያ ደግሞ ቢያንስ 19 ሚሊዮን ነው።

ለ2002 የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ ላይ ፊፋ ለአሜሪካን ሳሞአ መጫወት የሚችሉት የአገሪቱን ፓስፖርት የያዙ መሆን አለባቸው የሚል ውሳኔ ማስተላለፉ ቀድሞዉኑ ደካማ የነበረውን ብሔራዊ ቡድን ጨርሶ ያፈረሰ ነበር ይላል።

ከ20 የብሔራዊ ቡድን አባላት ሳላፑ ብቻ ነበር የአገሪቱ ፓስፖርት የነበረው። ከዚያች አነስተኛ ደሴት የብሔራዊ ቡድን ተጫዋች ፍለጋ ተነሳን ይላል።

“በሁለት ሳምንታት ውስጥ ተጫዋቾችን መፈለግ ነበረብን። ብዙ ታዳጊዎችን ከሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መሰብሰብ ግድ ሆኖብናል” ይላል።

የ15 ዓመት ዕድሜ ያላቸውን ሦስት ተጫዋቾች ይዞ የተመሠረተው ቡድን አማካኝ ዕድሜው 18 ነበር። በወቅቱ 20 ዓመቱ የነበረው ግብ ጠባቂ በቡድኑ ‘አንጋፋው’ ተጫዋች ሆነ።

31 ለ 0

እንደተጠበቀው ከታሪካዊ ሽንፈት ቀደም ብሎ በዓለም ዋንጫ ማጣሪያ የምድብ ጨዋታዎች ቡድኑ በፊጂ እና ቶንጋ በሰፊ የግብ ልዩነት ተሸነፈ።

በመጀመሪያው ጨዋታ 13 ለ 0 በፊጂ ተሸነፉ። በሁለተኛው ጨዋታ በሳሞአ 8 ለ 0 ተሸነፉ። በሦስተኛው ጨዋታ በቶንጋ 5 ለ 0 መሸነፋቸው እንደመሻሻል ተቆጥሮ ለአውስራሊያው ጨዋታ መዘጋጀት ጀመሩ።

በምድብ ጨዋታዎች ላይ ቶንጋን 22 ለ 0 ያሸነፈችው አውስራሊያ ጠንካራዋ ተጋጣሚያቸው እንደምትሆን ሳላፑ ጠንቅቆ ያውቃል።

“በአውስራሊያው ጨዋታ እንደምንም ከ22 ጎል በላይ እንዳይቆጠርብን ነበር ጥረቴ” ይላል።

ጨዋታው ተጀመረ። የአውስራሊያው ኮን ጎል ለማስቆጠር የወሰደበት 8 ደቂቃዎች ነበሩ። ከሦስት ደቂቃ በኋላ አርቺ ቶምፕሰን የተባለው ተጫዋች ሁለተኛዋን ጎል አስቆጠረ።

27ኛው ደቂቃ ላይ አርቺ ቶምፕሰን ሃትሪኩን ሠርቷል። 75ኛው ደቂቃ ላይ ደግሞ ለራሱ 13ኛ ጎሉን አስቆጥሯል።

ዴቪድ ዛደሪሊክ የተባለው ተጫዋች 8 ጎል አስቆጥሯል። የጨዋታው ፍጻሜም 31 ለ 0 ሆነ።

ሳላፑ በጨዋታው ወቅት የቡድን አጋሮቼ ከእኔ ፊት ቆመው ከሚከላከሉ ይልቅ ወደፊት ሄደው እንዲያጠቁ ስወተውታቸው ነበር ይላል።

“ወደ ፊት ሂዱ። ፊት ለፊቴ አትቁሙ እያልኩ እናገራቸው ነበር። እየከለሉኝ ኳሷን ሳላያት ታልፈኝ ነበር” በማለት ያን ጨዋታ ያስታውሳል።

በዕለቱ የአውስራሊያ ብሔራዊ ቡድን ውሳኔ “ስፖርታዊ ጨዋነት አልነበረውም” ይላል። “ስንት ጎል ሲያገቡ ነው የሚበቃቸው? ምን ያህል የግብ ልዩነት ቢያስፈልጋቸው ነው?” ሲል በምሬት ይጠይቃል።

የቡድኑ አሠልጣኝ ብሆን ኖሮ 20 ጎል ካገቡ በኋላ ጨዋታው እስኪያልቅ ኳሱን ይዛችሁ ቆዩ ብዬ እነግራቸው ነበር ይላል።

በድህረ ገጻችን ኢትዮ አማዞን በመግባት የሚፈልጉትን እቃ ማዘዝ  ብቻ  ሳይሆን የርስዎንም እቃዎች መሸጥ እንደሚችሉ ስናሳውቅዎት በደስታ ነው ። ለማስታወቂያ ወይንም ለመግቢያ ምንም ክፍያ አይጠበቅብዎትም፤  ለተጨማሪ መረጃ   ድህረ ገጻችንን ይጎብኙ። https://ethio-amazon.com/

ለበለጠ መረጃ ሊንኩን በመንካት የቴሌግራም ግሩፓችንን ይቀላቀሉ!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Cart

Your Cart is Empty

Back To Shop