ባይተዋር ከተማ፡ “ፒያሳ፣ ካዛንቺስ… ሰፈሬ አልመስል አሉኝ”!!! Leave a comment

ባለፉት ዓመታት በአዲስ አበባ በቅርስነት ተመዝግበው የነበሩ እንዲሁም ሌሎችም ታሪካዊ ሕንጻዎች፣ ቤቶች እና አካባቢዎች እንደ ዋዛ አፈር ለብሰዋል። በምትካቸው ሰማይ ጠቀስ ፎቆች ሊቆሙ አፈራቸው እየተማሰ ነው፤ ቀን ከሌት። ጥድፊያው ነጠላ ለመዘቅዘቅ ጊዜ አይሰጥም። በዚህ ዘገባ፣ አንድን ሕንጻ ወይም ቤት ቅርስ አልያም ታሪካዊ ሥፍራ ለማለት መስፈርቱ ምንድን ነው? የታሪካዊ ሕንጻዎች እና ቤቶች መፍረስ በታሪክ፣ በነዋሪዎች ሥነ ልቦና፣ በኪነ ሕንጻ እና በማኅበራዊ መስተጋብር ላይ ምን ጫና ያሳድራል? ቅርሶች እና ታሪካዊ ሥፍራዎችን እንዴት ጠብቆ ማደስ፣ ማዘመን፣ መልሰው አገልግሎት ላይ እንዲውሉ ማድረግ እንዲሁም ከሌሎች ግንባታዎች ጋር ጎን ለጎን እንዲሄዱ ማድረግ ይቻላል? የሚሉት እና ተያያዥ ነጥቦች ይዳሰሳሉ።

    “እናቴ ስትሞት መጽሐፍ ቅዱሷ መሀል አንድ ነገር አገኘሁ። የሚያምር ቤት ፎቶ። አባቷ የሰጣት ቤት ነው። . . . ምን ዋጋ አለው፣ ወደ 100 ዓመታት ያስቆጠረውን ቤት አፈረሱት፤ ታሪክና ትውስታ የሞላውን ቤት አወደሙት፤ ሳያመነቱ. . . ።

“. . . እናቴ ስለቤቱ የሰማቻቸውን ታሪኮች ነግራኛለች። አያቴ ፊታውራሪ አጥናፍሰገድ ወልደጊዮርጊስ ነው የገነባው። እናቴ ቤቱን የማደስ ሕልም ነበራት። አንድ ቀን ሰዎች መጥተው በታሪካዊው ቤት ውስጥ ይኖር የነበረውን ጀግና፣ ለአገሩ የነበረውን ሕልም፣ ለባለቤቱ የነበረውን ፍቅርና ሊያቅፋት ያልቻለውን ልጁን ናፍቆት እንዲመለከቱ ቤቱን ለማደስ ትመኝ ነበር። ይህን ቤት አድሰዋለሁ ትል ነበር።

“. . .ደርግ እስከሚያስወጣን ድረስ እዛ ቤት ነው ያደግኩት። አሁንም ድረስ ሳቅ ሲያስተጋባ ይሰማኛል። በጦርነት፣ በሞት፣ በማጣት ውስጥም ቤተሰባችንን ጠብቆ አቆይቷል። ዛሬ ግን ሁሉም ጠፍቷል። ቤቱን አድሼ ሕልሟን እውን ለማድረግ የምችለውን ሁሉ ለመሞከር ለእናቴ ቃል ገብቼ ነበር. . . አዬዬ አላሳካሁትም።

“ይሄን ታሪክ የማጋራው ፍትሕ ለመጠየቅ አይደለም። ፍትሕ እንደማይመጣ አውቀዋለሁ። ይሄን የማጋራው ለትውስታ ነው። አያቴ ፊታውራሪ አጥናፍሰገድ ወልደጊዮርጊስን እና ሌሎች ለኢትዮጵያ የሞቱ ቀደምቶችን እና ታሪኩን ማቆየትን ታልም የነበረችውን እናቴን ለማስታወስ ነው። የቀደመ ታሪካችን ዋጋ አለው። ጀግኖቻችን ዋጋ አላቸው። እኛን እኛ ያደረጉንን ትውስታዎችን ለመጠበቅ መታገል እንዳለብን ለማሳሰብ ነው…”

ይህ ጽሑፍ በሚድየም ድረ ገጽ ላይ Ethiopia’s Forgotten Heroes: The Price of ‘Progress’ በሚል በእንግሊዝኛ የታተመ ሲሆን፣ ለዚህ ዘገባ እንዲስማማ ሆኖ ወደ አማርኛ ተመልሷል።

የፀሐፊዋ አያት ፊታውራሪ አጥናፍሰገድ በፋሺስት ጣልያን ወረራ ወቅት በአርበኝነት ሲዋደቁ ነው የተሰውት። የአያታቸው አያትም በዓድዋ ጦርነት ተሰውተዋል።

ቤቱን “የፍቅር እና መስዋዕትነት ተምሳሌት” ሲሉ በጽሑፋቸው የገለጹትም ለዚሁ ይመስላል።

በፋሺስት ወረራ ዘመን ጣሊያኖች ቤቱን መቀመጫ አድርገው ይጠቀሙበት ነበር። ከድል በኋላ ቤቱ ለቤተሰቡ ተመለሰ።

ደርግ ከወረሰው በኋላ ቤቱን ለማስመለስ ቤተሰቡ ትልቅ ተጋድሎ አድርጓል። የፀሐፊዋ እናት ያደረጉት ጥረት እንዳልተሳካ ፀሐፊዋ ገልጸዋል።

“እናቴ ለ40 ዓመታት ቤቱን ከርቀት አዘውትራ ትመለከተው ነበር” ይላሉ።

“. . . በአዲስ አበባ በዘመናዊነት ስም ብዙ ታሪካዊ ሥፍራዎች እየጠፉ ነው። ከቀድሞው ጋር የሚያስተሳስረን አይተኬ ባህላዊ ሃብት ዋጋ እያጣ ነው። የከተማችን ነፍስ በእድገት ስም እየከሰመ ነው. . .” እያሉ ይቀጥላሉ ፀሐፊዋ።

በድህረ ገጻችን ኢትዮ አማዞን በመግባት የሚፈልጉትን እቃ ማዘዝ  ብቻ  ሳይሆን የርስዎንም እቃዎች መሸጥ እንደሚችሉ ስናሳውቅዎት በደስታ ነው ። ለማስታወቂያ ወይንም ለመግቢያ ምንም ክፍያ አይጠበቅብዎትም፤  ለተጨማሪ መረጃ   ድህረ ገጻችንን ይጎብ/ኙ። https://ethio-amazon.com/

ለበለጠ መረጃ ሊንኩን በመንካት የቴሌግራም ግሩፓችንን ይቀላቀሉ!https://t.me/ethioamazon

ምንጭ፡– (ቢቢሲ)

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Cart

Your Cart is Empty

Back To Shop