ቲክቶክ የተሰኘው የቪድዮ ማጋሪያ የማህበራዊ ሚዲያ ለአሜሪካ ኩባንያ የማይሸጥ ከሆነ በመላ አሜሪካ ለመታገድ ተቃርቧል።
እግዱ ተግባራዊ እንዳይደረግ ወይም ውድቅ እንዲሆን ቲክቶክ ወደ አሜሪካ ፍርድ ቤት አምርቷል፤ ሙግትም ከፍቷል።
መተግበሪያው ለፍ/ቤት ባቀረበው የአቤቱታ መዝገብ ” ከ9 ወር – 1 ዓመት ባለው ጊዜ ቲክቶክ ካልተሸጠ #ይታገድ ” የሚለው ሕግ ኢ-ሕገመንግስታዊ ነው ብሎታል።
” ሕጉ የአሜሪካውያንን የመናገር ነጻነትን የሚያደናቅፍ እና ሕጋዊ መረጃን እንዳያገኙ የሚከለክል ነው ” ሲል አክሏል።
አሜሪካ እርምጃውን ለመውሰድ ” ግምታዊ ስጋቶችን ” ብቻ እንዳቀረበች የገለጸው ቲክቶክ ፍርድ ቤት እግዱን እንዲያስቆምለት ጠይቋል።
ባይትዳንስ ኩባንያ ‘ቲክቶክ’ን አሁን ባለው አልጎሪዝም ከመሸጥ አሜሪካ ውስጥ ሙሉ በሙሉ #መዘጋትን እንደሚመርጥ የኩባንያው ምንጮች መናገራቸው ይታወሳል።
አሜሪካም ከሀገር ደህንነት ጋር በተያያዘ ” ካልተሸጠ ይታገድ ” በሚለው ሕግ ላይ አቋሟ ፍጹም የጸና ነው ተብሏል።
በቀሩት ጥቂት ወራት ውስጥ #ካልተሸጠ በመላው አሜሪካ መታገዱ የማይቀርለት ቲክቶክ 170 ሚሊዮን ተጠቃሚዎቹን ያጣል።
በድህረ ገጻችን ኢትዮ አማዞን በመግባት የሚፈልጉትን እቃ ማዘዝ ብቻ ሳይሆን የርስዎንም እቃዎች መሸጥ እንደሚችሉ ስናሳውቅዎት በደስታ ነው ። ለማስታወቂያ ወይንም ለመግቢያ ምንም ክፍያ አይጠበቅብዎትም፤ ለተጨማሪ መረጃ ድህረ ገጻችንን ይጎብኙ። https://ethio-amazon.com/
ለበለጠ መረጃ ሊንኩን በመንካት የቴሌግራም ግሩፓችንን ይቀላቀሉ!https://t.me/ethioamazon
ምንጭ ( @tikvahethiopia )