ታዋቂዋ ደቡብ አፍሪካዊት ሙዚቀኛ ዛሐራ አረፈች Leave a comment

ታዋቂዋ ደቡብ አፍሪካዊቷ ሙዚቀኛ ዛሐራ 35 አመቷ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየች። አፍሮፖፕ በሚባል የሙዚቃ ስልት የምትታወቀው እና በርካታ ሽልማቶችን የተጎናጸፈችው ቡላም ማኩቱካ ወይም ዛህራ ማረፏንም ያስታወቁት የአገሪቱ የባህል ሚኒስትር ናቸው። በጉበት ህመም ምክንያት ህክምና ሲደረግላት እንደቆየ የተገለጸ ሲሆን መንግሥትም ቤተሰቧን ለተወሰነ ጊዜም ይረዳ እንደነበር የአገሪቱ ስፖርት፣ ስነ ጥበብ እና ባህል ሚኒስትር ዚዚ ኮድዋ ተናግረዋል።

ሙዚቀኛዋ በአውሮፓውያኑ 2011 ባወጣችው ሎሊዌ አልበሟ ከአገሯ አልፋ በበርካታ አፍሪካ አገራትም ታዋቂነትን እንዲሁም ተወዳጅነትን አትርፋለች። ዛህራ ከጥቂት አመታትም በፊት ከአልኮል ሱስ ለመላቀቅ እያደረገች ያለችውንም ትግል በግልጽ አውርታ ነበር። ባለፈው ወር ቤተሰቦቿ ሆስፒታል መግባቷን አረጋግጠው ደቡብ አፍሪካውያን ሙዚቀኛዋን በጸሎታቸው እንዲያስቧት ጠይቀዋል።

ሰኞ ምሽት በጆሐንስበርግ ሆስፒታል ህይወቷ ማለፉን የመንግሥት ሚዲያ የሆነው ኤስኤቢሲ ዘግቧል። ቤተሰቦቿ ሙዚቀኛዋ ማለፏን አስመልክቶ ይፋዊ መግለጫ እንደሚሰጡ እየተጠበቀ ባለበት ወቅትም በርካታ አድናቂዎቿ እና ደጋፊዎቿ ሃዘናቸውን በተለያዩ ማህበራዊ ድረ ገጾች እያጋሩ ይገኛል።

 ዛሐራ እና ጊታርዋ በደቡብ አፍሪካ ሙዚቃ ውስጥ አይረሴ እና ዘላላማዊ አሻራውን ጥለዋልሲሉ ኮድዋ በኤክስ (የቀድሞው ትዊተር) ገጽ አስፍረዋል።ምርጥ የሆኑ ሙዚቃዎችን ትታልናለችሲልም ሌላ አድናቂ በኤክስ ገጽ አጋርቷል።

አምስት አልበሞችን ያወጣችው ዛሐራ በርካታ የአገር ውስጥ እና የአለም አቀፍ ሽልማቶችን ተጎናጽፋለች። ቢቢሲም ከሶስት ዓመታት በፊት በምርጥ 100 ሴቶች ዝርዝር ውስጥ አካቷት ነበር። ዛሐራ ሙዚቃዋንም እንዲሁ ያላትን ታዋቂነት በሴቶች ላይ በሚደርሱ ጥቃቶች ላይ ድምጽ ለመሆን ተጠቅማበታለች። እሷም የጥቃት ሰለባም መሆኗንም ተናግራ ነበር።

ዛህራ ባለፈው ዓመት ከአገር ውስጥ ሬዲዮ ጋር ባደረገችው ቃለ ምልልስ ሙዚቃዋ ለእውቅናዋ ብቻ ሳይሆን ፈውስ ለሚያስፈልጋቸው መንፈሳቸው ለተሰበሩ ሰዎች በሙሉ እፎይታ እንዲሰጣቸውም እንደሆነ ተናግራ ነበር።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Cart

Your Cart is Empty

Back To Shop

የሚፈልጉትን ይዘዙን

Order what you want