አኒሚያ በተለይ ለነፍሰጡር ሴቶች እና ለጽንሳቸው ደኅንነት ስጋት ከመሆን ባሻገር እስከ ሕልፈት የሚያደርስ የጤና ችግር ነው።
አኒሚያ ቀይ የደም ህዋሳት ወይም ሄሞግሎቢን ወደ ሌሎች የሰውነት ክፍሎች ኦክስጅንን ማጓጓዝ ሲሳነው የሚፈጠር ነው።
መህንሩኒሳ ሳለም ካህን በአኒሚያ ምክንያት በእርግዝና ወቅት መንታ ልጆቿን አጥታለች። ሁለተኛው እርግዝናዋም በተመሳሳይ አደጋ ላይ ነው።
ሕንድ ይህንን የጤና ችግር ለመቅረፍ የ50 ዓመት ዘመቻ አካሂዳለች። ነገር ግን አሁንም ግማሽ የሚሆኑት ሕንዳውያን ሴቶች ይህ አይነቱ ችግር አለባቸው።