አርቴፊሻል የአካል ድጋፍ የሚሰጡ የሕክምና ባለሙያዎች እጥረት መኖሩ ተገለጸ Leave a comment

አርቴፊሻል የአካል ድጋፍ የሚሰጡ የሕክምና ባለሙያዎች እጥረት መኖሩ ተገለጸ

መጋቢት 23/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) እንደ ሀገር የሰው ሰራሽ የአካል ድጋፍ የሚሰሩ እስፔሻሊስት የሕክምና ባለሙያዎች በከፍተኛ ሁኔታ እጥረት መኖሩን ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

ይህም የሆነበት ምክንያት ለስልጠና የሚወጣው ወጭ ከፍተኛ በመሆኑ ነው ተብሏል።

የጤና ሚኒስቴር የሰው ሀብት ልማት ዘርፍ መሪ ስራ አስፈፃሚ አሰግድ ሳሙኤል ለአሐዱ እንደተናገሩት፤ በተለያየ ሁኔታ አካላቸውን የሚያጡ እና የሰው ሰራሽ የአካል ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው ሰዎች የሚሰሩ እስፔሻሊስት የሕክምና ባለሙያዎች እጥረት ተከስቷል።

ይህን የሕክምና ስልጠና ይሰጥ የነበረው ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል እንደነበር ገልጸው በተለያየ ምክንያት የስልጠና ሂደቱ ተቋርጦ መቆየቱን አስታውቀው በአሁኑ ጊዜ ሕክምናውን ለማድረግ በተለያየ ምክንያት ፍላጎቱ እየጨመረ መምጣቱን ገልጸዋል።

የተገልጋዩ ቁጥር እየጨመረ በመምጣቱ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የስልጠና ሂደቱን መጀመሩን አቶ አሰግድ ተናግረዋል።

ችግሩን ለመፍታት በክልል ደረጃ ስልጠናውን ለመስጠት ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ እንደሆነ አንስተው፤ የሚሰለጥኑ የሕክምና ባለሙያዎች የምልመላ ሂደትም መጠናቀቁን ገልጸዋል።

የጤና ስልጠና በፍላጎት ላይ የተመሰረተ ሲሆን፤ በየ ጤና ተቋሙ የሚሰጠው አገልግሎት የተለያየ መሆኑን ተጠቁሟል፡፡

የጤና ሚኒስቴር ለጤና ባለሙያዎች ለሚሰጠው ስልጠና የበጀት እጥረት እና የሎጅስቲክ ችግር እየገጠመው መሆኑንም ሥራ አስፈጻሚው ጨምረው አስታውቀዋል።

የተፈጠረው የበጀት ችግር ለመፍታት በማህበራዊ ትስስር ስልጠና እየሰጠ ቢሆንም፤ የግድ በአካል ስልጠና መስጠት ሲፈልግ ችግር እንደሆነበት አስታውቋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

    Cart

    Your Cart is Empty

    Back To Shop
    COMPARE PRODUCTS