ኢራን እስራኤልን ማስፈራራቷን ተከትሎ አሜሪካ ተዋጊ ጄቶች እና የጦር መርከቦች ልታሰማራ ነው……. Leave a comment

አሜሪካ እስራኤልን ከኢራን እና አጋሮቿ ከሚደርስ ጥቃት ለመከላከል በሚል ተጨማሪ የጦር መርከቦችን እና ተዋጊ ጄቶችን ወደ መካከለኛው ምስራቅ እንደምታሰማራ ፔንታጎን ገለጸ።

በቅርቡ የሐማስ የፖለቲካ መሪ ኢስማኤል ሃኒያ በኢራን እንዲሁም የሊባኖስ ታጣቂ ቡድን ሄዝቦላ ከፍተኛ አዛዥ መገደላቸውን ተከትሎ በቀጣናው ውጥረት ነግሷል።

በመካከለኛው ምስራቅ የሚሳኤል መከላከያ ኃይል ለማሰማራት ዝግጅት መጠናቀቁን የገለጸው ፔንታጎን እስራኤልን ለመከካለል “የማያወላውል ቁርጠኝነት” አለ ብሏል።

የኢራን መንፈሳዊ መሪ አያቶላ አሊ ኻሚኒ እስራኤል በሃኒያ ግድያ “ከባድ ቅጣት” እንደሚጠብቃት ቃል ገብተው በአገሪቱ የሶስት ቀናት ብሄራዊ ሃዘን አውጀዋል።

የሐማሱ መሪ ኢስማኤል ሃኒያ ማክሰኞ ሌሊት ሐምሌ 23/ 2016 ዓ.ም ስምንት ሰዓት ላይ በኢራኗ መዲና ቴህራን ቤት ውስጥ ሳሉ ተገድለዋል። ኢራን እና ሐማስ መሪውን በሚሳኤል ጥቃት የገደለቻቸው እስራኤል ናት ቢሉም እስራኤል ይፋዊ አስተያየት ከመስጠት ተቆጥባለች።

በጋዛ የተኩስ አቁም ድርድር ላይ ትልቅ ሚና የነበራቸው የ62 ዓመቱ ሃኒያ በቴህራን የኢራን ፕሬዚዳንት ማስዑድ ፔዜሽኪያን በዓለ ሲመት ላይ ከታደሙ ከሰዓታት በኋላ ነው የተገደሉት።

የሃኒያ መገደል የተሰማው እስራኤል የሄዝቦላህ ከፍተኛ አዛዥ የሆነውን ፉአድ ሹክርን መግደሏን ባሳወቀች በሰዓታት ውስጥ ነው።

የፔንታጎን መግለጫ እንዳስታወቀው የሚሰማራው አዲሱ ወታደራዊ ኃይል “ የአሜሪካ ጥበቃን በማሻሻል ለእስራኤል መከላከያ የሚሰጠውን ድጋፍ የሚያሳድግ እንዲሁም አሜሪካ ለተለያዩ ድንገተኛ ጥቃቶች ምላሽ ለመስጠት ዝግጁነቷን የሚያረጋግጥ ነው” ብሏል።

የባለስቲክ ሚሳኤል መከላከያም እንዲሁ በተጨማሪም እንደሚሰማሩ ተገልጿል።

ኢራን በእስራኤል ላይ በሰው አልባ አውሮፕላኖች እና ሚሳኤሎች ጥቃት ከሰነዘረችበት ከሚያዝያ ወር በፊትም የአሜሪካ ጦር ስምሪቱን አጠናክሮ ነበር።

እስራኤል እና አጋሮቿ የተወነጨፉባቸውን ወደ 300 የሚጠጉ ሚሳኤሎችን እና ሰው አልባ አውሮፕላኖችን አክሽፈናል ብለዋል።

እስራኤል ስለ ሐማሱ መሪ ግድያ በቀጥታ የሰጠችው አስተያየት የለም።

ይሁን እንጂ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ አገራቸው ባለፉት ቀናት በጠላቶቿ ላይ “የከፉ ጥቃቶችን” አድርሳለች ብለዋል። ጨምረውም በቴህራን ከተፈጸመው ጥቃት በፊት በሊባኖስ የሄዝቦላህ ከፍተኛ አዛዥን መግደላቸውን ተናግረዋል።

ሌሎች የመካከለኛው ምሥራቅ አገራትን ያሳተፈ ጦርነት በቀጣናው ሊጀመር ይችላል የሚለው ስጋት እየጨመረ መጥቷል።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ በቀጣናው ውጥረቱ በአደገኛ ሁኔታ መባባሱን አስመልክቶ አስጠንቅቀዋል።

በድህረ ገጻችን ኢትዮ አማዞን በመግባት የሚፈልጉትን እቃ ማዘዝ  ብቻ  ሳይሆን የርስዎንም እቃዎች መሸጥ እንደሚችሉ ስናሳውቅዎት በደስታ ነው ። ለማስታወቂያ ወይንም ለመግቢያ ምንም ክፍያ አይጠበቅብዎትም፤  ለተጨማሪ መረጃ   ድህረ ገጻችንን ይጎብ/ኙ። https://ethio-amazon.com/

ለበለጠ መረጃ ሊንኩን በመንካት የቴሌግራም ግሩፓችንን ይቀላቀሉ!https://t.me/ethioamazon

ምንጭ፡– (ቢቢሲ)

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Cart

Your Cart is Empty

Back To Shop