ኢትዮጵያዊያን በግዳጅ ወንጀል በሚፈጽሙበት ካምፕ ታግቶ የተገኘው ቻይናዊ ተዋናይ….. Leave a comment

ብዙም ታዋቂ ያልሆነ ቻይናዊ ተዋናይ ለሁለት ቀናት ታይላንድ ውስጥ ጠፋ።

ፍቅረኛው ማኅበራዊ መዲያ ላይ ታፈላልገው ጀመር።

የዋንግ ዢንግ ፍቅረኛ በቻይና ማኅበራዊ ሚዲያ “ድምጻችንን ለማሰማት ኢንተርኔት ከመጠቀም ውጭ አማራጭ የለንም” ብላለች።

ታዋቂ ቻይናውያን መልዕክቷን ካጋሩት በኋላ ዋነኛ መነጋገሪያ ጉዳይ ሆነ።

የ31 ዓመቱ ዋንግ የቻይናውያንና የመንግሥታቸውንም ትኩረት አገኘ።

እአአ ታኅሣሥ 7 ሚያንማር ድንበር አቅራቢያ በሚገኝ የበይነ መረብ አጭበርባሪዎች ማቆያ ውስጥ ዋንግ ተገኘ።

ድንገት መገኘቱ ግን ጥያቄ አስነሳ።

በወንጀለኞች በሚመሩት እነዚህ ማዕከሎች ውስጥ የሚያዙ ሰዎች እጣ ፈንታ አነጋጋሪ ሆነ።

በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች እየተያዙ የበይነ መረብ ወንጀል እንዲፈጽሙ ይገደዳሉ።

ከእነዚህ መካከል በደላሎች ተታልለው ወደ ካምፖቹ ያቀኑ በርካታ ኢትዮጵያዊያን ይገኙበታል። በቅርቡ ቢቢሲ በሠራው ልዩ ዘገባ ከካምፑ ገንዘብ ከፍሎ የወጣ ኢትዮጵያዊ ማናገሩ ይታወሳል።

በዚህ የግዳጅ ማቆያ ውስጥ ቤተበሳቸው የተያዘባቸው ቻይናውያን ፊርማ በማሰማሰብ መንግሥታቸው ጣልቃ እንዲገባ ጠይቀዋል።

እስካሁን ሰዎች እንደተያዙባቸው የገለጹ ሰዎች 600 ሲሆኑ ቁጥሩ እየጨመረ ነው። ዋንግ ለፖሊስ እንደገለጸው በማቆያ ውስጥ 50 ቻይናውያን ተይዘዋል።

“የተቀሩት ቻይናውያንን ፖሊስ ይታደጋቸዋል ወይ የሚለው አሳስቦናል። ሌሎች በማቆያው የተያዙ ሰዎች ሕይወትም ዋጋ አለው” ሲሉ የቻይና ማኅበራዊ መዲያ ዌቦ ተጠቃሚዎች ጽፈዋል።

ዋንግ የጠፋው ታኅሣሥ 3 በታይላንድ ድንበር ከተማ ማይ ሶት ሲሆን ቦታው ወደ ሚያንማር ሰዎችን በሕገ ወጥ መንገድ በማዘዋወር ታዋቂ ነው።

የታይላንድ ፖሊስ እንዳለው፣ ተዋናዩ የቻይና ማኅበራዊ ሚዲያ ዊቻት ላይ ያገኘው የፊልም ሥራ ላይ ለመሳተፍ ነበር ወደ ባንግኮክ ያቀናው።

እአአ በ2018 በታይላንድ ሌላ ፊልም ስለቀረፀ አሁንም የተደረገለት ጥሪ እውነተኛ እንደሆነ ነው ያመነው።

ታይላንድ ሲደርስ አንድ መኪና ጠበቀው። ወደ ሚያንማር ተወሰደ።

ፀጉሩን በግድ ላጭተው እንዴት በበይነ መረብ ሰዎችን ማጭበርበር እንደሚቻል የግዳጅ ሥልጠና ሰጡት።

ስልክ ደውለው ሰዎችን በማቆያው ያጭበረብራሉ።

ፍቅረኛው መጥፋቱን በዊቦ ላይ ጻፈች።

ከተዋናዩ ወንድም ጋር ቢፈልጉትም ሊያገኙት እንዳልቻሉ ጻፈች።

ፖሊስም ምንም መረጃ ሊሰጣት አልቻለም ነበር።

ታይላንድ ፖሊስ ጋር በመሄድ የቻይና ኤምባሲ ጉዳዩን ማስመዝገብ ነበረበት።

በቻይና ማኅበራዊ ሚዲያ ተዋናዩን የሚፈልጉ ሰዎች ቁጥር ሲጨምር ባለሥልጣኖች የበለጠ ተባባሪ ሆኑ።

ፖሊስ ለጉዳዩ ትኩረት እንደሰጠም ገለጸ።

በቀጣዩ ቀን የቻይናና ታይላንድ ባለሥልጣኖች ተዋናዩ ዋንግ መገኘቱን አስታወቁ።

እንዴት ሊያገኙት እንደቻሉ ግልጽ ነገር አልተናገሩም።

በየትኛው የግዳጅ ማቆያ ተይዞ እንደነበርም ይፋ አልተደረገም።

ከዚህ ቀደም የታገቱ ሰዎችን በማስለቀቅ ውስጥ የተሳተፈና ስሙ እንዳይጠቀስ የጠየቀ ባለሙያ እንዳለው፣ የወንጀል ቡድኖቹ ተዋናዩን ለመልቀቅ የተስማሙት ስለነሱ መረጃ እንደማይወጣ በማረጋጥ ሊሆን ይችላል።

የግዳጅ ማቆያው ከሚጋለጥ ይልቅ ተዋናዩን መልቀቅ የተሻለ ሆኖ አግኝተውት እንደሆነ ግምቱን ያስቀምጣል።

ተዋናዩን የሚፈልጉ ሰዎች መብዛታቸው የግዳጅ ማቆያውን የወንጀል ድርጊት የሚያሰናክል ሆኖ አግኝተውታል።

የቻይና መንግሥትም ሕዝቡ መጠየቅ እንዲያቆምና ተዋናዩን ለማግኘት መንግሥት ግዴታውን መወጣቱን እንዲረዳ ይፈልጋል።

አምና በቻይና እና በአንድ ታጣቂ ቡድን ጥምር ኦፕሬሽን በሚያንማር ሻን ግዛት ሰዎችን በግዳጅ የበይረ መረብ ወንጀል የሚያስፈጽሙ ቡድኖች የከፈቷቸው የግዳጅ ማቆያዎችን ለመዝጋት ንቅናቄ ተደርጓል።

ሆኖም ግን የግዳጅ ማቆያዎቹ ወደ ገጠራማ አካባቢዎችም እየተስፋፉ መሆኑን መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅት ሠራተኞች ለቢቢሲ ገልጸዋል።

የታይላንድና ሚያንማር ድንበር የዓለም አቀፍ በይረ መረብ ወንጀል ማዕከል ሆኗል። በአካባቢው ያለውን የሥልጣን ሽኩቻ በመጠቀም ወንጀሉ ተስፋፍቷል።

ሰዎችን በግዳጅ ሥራ ውስጥ በማስገባትና በብዝበዛ ከሚታወቁ ማቆያዎች አንደኛው በታይላንድ ድንበር በማያዋዲ ከተማ ይገኛል።

ከቻይናና ከሌሎችም አገራት በሚሄዱ ቱሪስቶች ምጣኔ ሃብቷ የተገነባው ታይላንድ እርምጃ እንድትወስድ የሚያስገድድ ነው ሁኔታው።

ተዋናዩ ከታገተ በኋላ ቻይናውያን ወደ ታይላንድ ሄደው መዝናናት እንዳስፈራቸው እየተናገሩ ነው።

ተዋናዩ ዋንግ በታይላንድ ተይዞ ሳለ የሚበላው ምግብ በጣም ውስን እንደነበርና መጸዳጃ ቤት ለመሄድ ጊዜ እንደማይሰጠው መናገሩ ተዘግቧል።

ሌሎች ቻይናውያን ተዋንያንም ታይላንድ ሥራ አለ በሚል የሐሰት ሰበብ ወደ ታይላንድ ከሄዱ በኋላ በወንጀለኞች እጅ መውደቃቸውን እየተናገሩ ነው።

የታይላንድ ፖሊስ እንዳለው ዋንግ ተይዞ የነበረው በታይላንዳውያን አይደለም።

ታይላንድ ለሥራ ተጋብዛ ከሄደች በኋላ በታይላንድና ሚያንማር ድንበር የጠፋች ሞዴል ጉዳይ በቻይና ፖሊስ እየተመረመረ ነው።

ዋንግ ዕድለኛ ሆኖ ነው ከወንጀለኞቹ ይዞታ በፖሊስ የዳነው።

ከቻይና፣ ታይዋን፣ ማሌዥያና ሲንጋፖር በተጨማሪ ኢትዮጵያን ጨምሮ ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የተያዙ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች አሁንም በግዳጅ ማቆያዎቹ ተይዘዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Cart

Your Cart is Empty

Back To Shop