ከቀጣሪ ድርጅቷ 28 ሚሊዮን ዶላር የሰረቀችው የሂሳብ ሠራተኛ የ 50 ዓመት እስር ተፈረደባት Leave a comment

9 ታህሳስ 2023

ከቀጣሪ ድርጅቷ 28 ሚሊዮን ዶላር የሰረቀችው ደቡብ አፍሪካዊት የሂሳብ ሠራተኛ 50 ዓመት እስር ተፈረደባት። ሂለዴጋርድ ስቲንካምፕ የተባለችው ይህች ሴት በድርጅቱ ውስጥ በሠራችባቸው 13 ዓመታት ውስጥ ብቻዋን 28 ሚሊዮን ዶላር የመስረቋ ዜና አገሬውን ጉድ አሰኘቷል።

ሂለዴጋርድ ለዓመታት በስም ባልተጠቀሰ የአንድ ጤና ተቋም የሂሳብ ሠራተኛ ሆና ስትሰራ የቆየች ሲሆን፣ በእነዚህ ዓመታት ኃላፊነቷን እና ሙያዋን ተጠቅማ ገንዘብ ስታጭበረብር ቆይታለች ተብሏል። የሂሳብ ሠራተኛዋ በፍርድ ቤት ለቀረቡባት 336 የማጭበርበር ክሶች ጥፋተኝነቷን አምናለች። የሂለዴጋርድ የወንጀል ክስን የተመለከቱት ዳኛ ይህን ያህል መጠን ያለው ስርቆት በአንድ ግለሰብ ተፈጽሟል ብሎ መገመት የማይቻል ነው ብለዋል።

ዳኛ ፊሊፕ ቬንተርአንድ ሰው ብቻውን ይህን ያህል ገንዘብ ከቀጣሪው ይሰርቃል ብሎ ማሰብ ከአእምሮ በላይ ነውብለዋል። ጠበቆች ሂለዴጋርድ ስቲንካምፕ ከቀጣሪዋ ገንዘብ እንድትሰርቅ ሲያስገድዳት የነበረው አሁኑ ላይ በሞት የተለየው የደንበኛችን የትዳር አጋር ነው ሲሉ ተከራክረዋል።

ዳኛው ግንየወንጀል ደርጊቱን የፈጸመችው ለብቻዋ ሆና ነውበማለት መከራከሪውን ውድቅ አድርገውታል። ሂለዴጋርድ ስቲንካምፕ ቅንጡ ሕይወቷን ለመምራት ገንዘቡን ወጪ ስታደርግ ቆይታለች የሚሉት ምርማሪዎች፣ ግለሰቧ ለቁማር እና ለውድ ጌጣ ጌጦች መግዣ እንዲሁም ለውጭ አገር ጉዞዎች ከፍተኛ ገንዘብ ወጪ ስታደርግ ቆይታለች ብለዋል።

እንደማሳያም በአንድ ቁማር መጫወቻ ቤት በአንድ ምሽት 263 ሺህ ዶላር ወጪ አድርጋለች ብለዋል።  ዱባይን ደጋግማ ትጎበኝ ነበረ የተባለችው ሂለዴጋርድ፣ ለዓለም አቀፍ ጉዞዎች 1.6 ሚሊዮን ዶላር ወጪ ማድረጓን ምርማሪዎች ለፍርድ ቤት አስረድተዋል። ሂለዴጋርድ ስቲንካምፕ በስም ላልተጠቀሰው የጤና ኩባንያ ከአውሮፓውያኑ 2004 እስከ 2017 ከሠራች በኋላ በራሷ ፍቃድ ሥራዋን ለቃ ነበር።

እንደ ደቡብ አፍሪካ ፖሊስ ከሆነ የሂሳብ ሠራተኛዋ ቀጣሪ ድርጅቷን አብዝታ መበዝበዝ የቻለችው በድርጅቱ ሰነድ ላይ አበዳሪዎችን የመመዝገብ እና የመሰረዝ ኃላፊነት ስለነበራት ነው ብለዋል። ታዲያ የሂሳብ ሠራተኛዋ ባለቤቷን አበዳሪ አድርጋ ከመዘገበች በኋላ ገንዘብ ወደ ባለቤቷ የባንክ ሂሳብ እንዲገባ ስታደርግ ቆይታለች ተብሏል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Cart

Your Cart is Empty

Back To Shop

የሚፈልጉትን ይዘዙን

Order what you want