” የሟች ኪስ ውስጥ #ማንነቱን የሚገልጽ መረጃ ስላላገኘን ፎቶውን ለማሰራጨት ተገደናል ” – የዓዲግራት ከተማ ፓሊስ……. Leave a comment

በትግራይ ምስራቃዊ ዞን ዓዲግራት ከተማ  ቀበሌ 03 በተባለ መጠጥ ቤቶች በብዛት በሚገኙበት ቦታ ሚያዝያ 9/2016 ዓ.ም ሌሊት አሰቃቂ ግድያ ተፈፅሟል።

አስቃቂ ግድያው በመፈፀም የተጠረጠሩ 3 ግለሰቦች በህዝብ ጥቆማ የሟቹ አስከሬን በወደቀበት አከባቢ በሚገኝ መጠጥ ቤት በቁጥጥር ስር ውለው የሟች አስከሬን ወደ ዒድግራት ሆስፒታል ተወስደዋል።

የዓዲግራት ከተማ ፓሊስ ምርመራው ጨርሶ ለቀብር የሟቹ ቤተሰብ ቢያፈላልግም ዜናው እስከ ተጠናቀረበት ቀን ሰዓትና ደቂቃ የሟች ቤተሰብ አልተገኙም።

በሟቹ ኪስ ማንነቱ የሚጠቅስ መረጃ እንዳላገኘ የገለፀው የዓዲግራት ፓሊስ ፤ የሟቹ ፎቶ በሚድያና በማህበራዊ የትስስር ገፅ ለማስራጨት መገደዱን ገልጿል።

ሟቹን የሚያውቅ ካለ ወደ ዓዲግራት ከተማ ፓሊስ ፅህፈት ቤት ደውሎ እንዲያሳውቅ ፖሊስ ትብብር ጠይቋል።

ለሟች ቤተሰቦች በሙሉ መጽናናትን እንመኛለን!!!!

በድህረ ገጻችን ኢትዮ አማዞን በመግባት የሚፈልጉትን እቃ ማዘዝ  ብቻ  ሳይሆን የርስዎንም እቃዎች መሸጥ እንደሚችሉ ስናሳውቅዎት በደስታ ነው ። ለማስታወቂያ ወይንም ለመግቢያ ምንም ክፍያ አይጠበቅብዎትም፤  ለተጨማሪ መረጃ   ድህረ ገጻችንን ይጎብኙ። https://ethio-amazon.com/

ለበለጠ መረጃ ሊንኩን በመንካት የቴሌግራም ግሩፓችንን ይቀላቀሉ!https://t.me/ethioamazon

ምንጭ ፡-(#TikvahEthiopiaFamilyMekelle)

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Cart

Your Cart is Empty

Back To Shop