በአዲስ አበባ ፤ ‘ ከአከራይ ተከራይ የውል ስምምነት ‘ ጋር በተያያዘ ተከራዮች የሚገጥማቸውን ማንኛውም ችግር ጥቆማ ሊሰጡ እንደሚችሉ የከተማው የቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ አሳውቋል።
ቢሮው ማንኛውም አከራይ ከመጋቢት 24 ቀን 2016 ዓ/ም ጀምሮ የቤት ኪራይ መጨመርም ሆነ ተከራይን ማስወጣት ፈፅሞ የተከለከለ መሆኑን አስገንዝቧል።
ከዚህም ጋር በተያያዘ ተከራዮች የቤት ኪራይ ጭማሪ አልያም ‘ ቤቱን ይልቀቁልኝ ‘ የሚል ግፊት ከአከራዮች ከደረሰባቸው በስልክ ቁጥር +251118722917 / +251118553820 ላይ በመደወልና ጥቆማቸውን በመስጠት መብታቸውን ማስከበር እንደሚችሉ ገልጿል።
በሌላ በኩል ፤ ሰኔ 1 ላይ የጀመረው የአከራይ ተከራይ የውል ስምምነት ሊጠናቀቅ 14 ቀናት የቀሩት ሲሆን ዜጎች በአቅራቢያቸው በሚገኙት ወረዳዎች በማቅናት ምዝገባ እንዲያካሂዱ ማሳሰቢያ ተላልፏል።
አከራዮች የውል ስምምነቱን ሳይፈጽሙ እስከ ሶስት ወር ድረስ ከቆዩ የሁለት ወር የቤት ኪራይ እንዲከፍሉ እንደሚደረግ ተገልጿል።
መንግስት ጥናት በማድረግ በሚቀጥለው ዓመት ሰኔ ወር ላይ የዋጋ ጭማሪ እንደሚያደርግ አሳውቋል።
አከራይ የቤት ኪራይ ዋጋ ጭማሪ ማድረግ የሚችለው በዓመት አንዴ መንግስት በሚያወጣው ተመን ብቻ እንደሚሆን ተነግሯል።
በድህረ ገጻችን ኢትዮ አማዞን በመግባት የሚፈልጉትን እቃ ማዘዝ ብቻ ሳይሆን የርስዎንም እቃዎች መሸጥ እንደሚችሉ ስናሳውቅዎት በደስታ ነው ። ለማስታወቂያ ወይንም ለመግቢያ ምንም ክፍያ አይጠበቅብዎትም፤ ለተጨማሪ መረጃ ድህረ ገጻችንን ይጎብኙ። https://ethio-amazon.com/
ለበለጠ መረጃ ሊንኩን በመንካት የቴሌግራም ግሩፓችንን ይቀላቀሉ!https://t.me/ethioamazon
ምንጭ (@tikvahethiopia )