የአውሮፓ ህብረት በኢትዮጵያውያን ላይ የጣለው ጊዜያዊ የቪዛ ገደብ እንዳሳዘናት ኢትዮጵያ አስታውቃለች። Leave a comment

የአውሮፓ ህብረት ይህንን አቋሙን እንዲያጤነው ጠይቃለች። ብራስልስ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ትናንት መግለጫ አውጥቷል።

በመግለጫው ምን አለ ?

– የአውሮፓ ህብረት ም/ቤት ያስተላለፈው የእግድ ውሳኔ በህብረቱ አባል አገራት ለመኖር ህጋዊ ፍቃድ የተነፈጋቸው ኢትዮጵያዊ ዜጎችን በክብር፣ በስርዓት እና ዘላቂነት ባለው ሁኔታ እንዲመለሱ ለማድረግ ሁለቱ ወገኖች በቅርበት እየሰሩ ባለበት ወቅት ነው።

– ውሳኔው ኢትዮጵያውያንን ወደ አገራቸው ለመመለስና ከማህበረሰቡ ጋር መልሶ ለማዋሃድ በኢትዮጵያ እና በህብረቱ መካከል ያለውን ጠንካራ ትብብር ያላገናዘበ ነው።

– ውሳኔው ማንነትን ለማረጋጋጥ የሚደረገውን አድካሚ ሂደት ከግምት ውስጥ ማስገባት አልቻለም።

– ኢትዮጵያውያን ዜጎችን ከህብረቱ አባላት አገራት ወደ አገራቸው የሚመለሱበትን የቅበላ ስምምነት ተግባራዊ ለማድረግ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራዊ እርምጃዎች ላይ እንቅፋት የሚፈጥር ነው።

የአውሮፓ ኅብረት ም/ ቤት ከሰሞኑ በኅብረቱ ሕግ ሥር ያሉና ለኢትዮጵያውያን ቪዛ ለመስጠት ይውሉ የነበሩ አሠራሮች ላይ ገደብ ማድረጉ ይታወሳል።

በዚህ ዕገዳ መሠረት ፦

➡️ የአውሮፓ ኅብረት አባል አገራት ኢትዮጵያውያን በሚያቀርቧቸው ማስረጃዎች መሠረት ቪዛ ሲጠይቁ የሚያስፈልጓቸውን ቅድመ ሁኔታዎች ማንሳት (waiving requirements) አይችሉም፤

➡️ ኢትዮጵያውያን ከአንድ ጊዜ በላይ ወደ አውሮፓ ኅብረት አባል አገራት ገብተው መውጣት የሚችሉበት ቪዛ (multiple entry) ማግኘት አይችሉም፤

➡️ የዲፕሎማት እና አገልግሎት ፓስፖርት ያላቸው ኢትዮጵያውያን ያለ ክፍያ ቪዛ እንዲሰጣቸው አይደረግም።

ከዚህ በተጨማሪ ኢትዮጵያውያን የአውሮፓ ሀገራት ቪዛ ለማግኘት የሚጠብቁት ጊዜ ከ15 የሥራ ቀናት ወደ 45 የሥራ ቀናት ከፍ እንዲል ውሳኔ ተላልፏል።

የእገዳ ውሳኔው የኢትዮጵያ መንግስት በአውሮፓ ያሉ በህገወጥ መንገድ የሚኖሩትን ዜጎቹን ለመመለስ / ለመቀበል ያሳየው ተባባሪነት አናሳ በመሆኑ የተላለፈ መሆኑን አሳውቆ ነበር።

በድህረ ገጻችን ኢትዮ አማዞን በመግባት የሚፈልጉትን እቃ ማዘዝ  ብቻ  ሳይሆን የርስዎንም እቃዎች መሸጥ እንደሚችሉ ስናሳውቅዎት በደስታ ነው ። ለማስታወቂያ ወይንም ለመግቢያ ምንም ክፍያ አይጠበቅብዎትም፤  ለተጨማሪ መረጃ   ድህረ ገጻችንን ይጎብኙ። https://ethio-amazon.com/

ለበለጠ መረጃ ሊንኩን በመንካት የቴሌግራም ግሩፓችንን ይቀላቀሉ!https://t.me/ethioamazon

ምንጭ(ቢቢሲ/ በቤልጂየም የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ እና የአውሮፓ ኮሚሽን ድረገጽ ናቸው።)

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Cart

Your Cart is Empty

Back To Shop