የኢራቅ ፓርላማ #ግብረሰዶም / የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነትን ከ10 እስከ 15 ዓመት በሚደርስ እስር የሚቀጣ አዲስ ሕግ አርቅቋል። Leave a comment

በአዲሱ ሕግ መሠረት ጾታቸውን የቀየሩ ሰዎች ከ1 እስከ 3 ዓመት ሊታሰሩ ይችላሉ።

በአዲሱ ሕግ ፦

➡️ የግብረሰዶም / የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነትን የሚያበረታቱ፣ የሚያስተዋውቁ፤

➡️ ሴተኛ አዳሪነትን የሚያራምዱ፤

➡️ ጾታ ለመቀየር ቀዶ ህክምና የሚያደርጉ ዶክተሮችን፤

➡️ ” ሆን ብለው ” እንደ #ሴት የሚሆኑ ወንዶች እና ” በሚስት መለዋወጥ ” ላይ የተሠማሩ ሰዎች እስራት ይጠብቃቸዋል ፤ ዘብጥያም ይወርዳሉ።

የሕጉ ዓለማ ፥ ” የኢራቅን ማህበረሰብ ከሞራል ዝቅጠትና ግብረ ሰዶማዊነት ከሚያደርሰው አደጋ ለመጠበቅ ነው ” ተብሏል።

ረቂቁ መጀመሪያ ላይ ግብረሰዶማውያን #በሞት እንዲቀጡ የሚል የነበረው ቢሆንም በአሜሪካ እና በአውሮፓ ሀገራት ከፍተኛ ተቃውሞ መሻሻሉ ነው የተሰማው።

የኢራቅ ፓርላማ አባል የሆኑት አሚር አል-ማሙሪ ፥ ” አዲሱ ሕግ #ኢስላማዊ እና ማህበረሰባዊ እሴቶችን የሚቃረኑ ልዩ ጉዳዮችን ለመዋጋት ትልቅ እርምጃ ነው ” ብለዋል።

#አሜሪካ በውጭ ጉዳይ መ/ ቤቷ በኩል ሕጉን ፤ ” ለሰብአዊ መብትና ነፃነት ጠንቅ ነው ” በማለት ሕጉን ተቃውማለች።

” ሕጉ የኢራቅን ኢኮኖሚ የሚያቀዛቅዝ እና የውጭ ኢንቨስትመንትን የመሳብ አቅምን ያዳክማል” ብላለች።

የምዕራቡ ዓለም ሀገራት ሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶችም ሕጉን ተቃውመዋል።

በድህረ ገጻችን ኢትዮ አማዞን በመግባት የሚፈልጉትን እቃ ማዘዝ  ብቻ  ሳይሆን የርስዎንም እቃዎች መሸጥ እንደሚችሉ ስናሳውቅዎት በደስታ ነው ። ለማስታወቂያ ወይንም ለመግቢያ ምንም ክፍያ አይጠበቅብዎትም፤  ለተጨማሪ መረጃ   ድህረ ገጻችንን ይጎብኙ። https://ethio-amazon.com/

ለበለጠ መረጃ ሊንኩን በመንካት የቴሌግራም ግሩፓችንን ይቀላቀሉ!https://t.me/ethioamazon

ምንጭ( ቢቢሲ ዜና )

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Cart

Your Cart is Empty

Back To Shop

የሚፈልጉትን ይዘዙን

Order what you want