የቅጣት ውሳኔውን ያሳለፈው የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ወንጀል ችሎት ነው።
ተከሳሾች ፦
1ኛ. ጫላ መገርሳ፣
2ኛ. ለሊሳ በቀለ፣
3ኛ ዳዊት ጉደታ፣
4ኛ. ዮሃንስ ደረጄ
5ኛ ብርቱካን ለታ ናቸው።
ከ1ኛ እስከ 4ኛ ተራ ቁጥር የተጠቀሱ ተከሳሾች በመጋቢት 19 ቀን 2015 ዓ.ም ከቀኑ 11:00 ሰዓት ላይ በሸገር ከተማ ገፈርሳ ክ/ ከተማ አካባቢ በሚገኝ የኖክ ነዳጅ ማደያ ስራ አስኪያጅ የሆነን የግል ተበዳይን ” የፀጥታ አካላት ነን ፣ በወንጀል ትፈለጋለህ ” በማለት መንገድ ላይ ያስቆሟቸዋል።
በኃላም ከውጭ ወደ ውስጥ እንዳይታይ አድርገው በስቲከር ሸፍነው ወደአዘጋጁት የቤት መኪና ውስጥ በማስገባት ወደ መልካ ናኖ ክ/ከ አንፎ ወደ ተባለ አካባቢ ይወስዷቸዋል።
ከዚህም በኋላ የሞተ ሰው ፎቶ ለግል ተበዳዩ በማሳየትና በመሳሪያ በማስፈራራት ግማሽ ሚሊየን ብር እንዲያመጣና እንደሚለቁት ይገልጻሉ።
ገንዘቡን ካልከፈለ ደግሞ ” ወደ ጦር ኃይሎች እንወስድኃለን ” በማለት ገንዘብ እንዲከፍል ያስፈራሩታል።
ይህን ተከትሎ የግል ተበዳዩ በባንክ ሂሳቡ ውስጥ 100 ሺህ እንዳለው ይገልጽላቸዋል።
በዚህም ጊዜ 1ኛ ተከሳሽ ባለቤቱ በሆነችው በ5ኛ ተከሳሽ የባንክ ሂሳብ በሞባይል ባንኪንግ የግል ተበዳዩ 100 ሺህ ብር እንዲያዘዋውር ያደረገና ቀሪውን 400 ሺህ ብር እንዲያመጣ በማስጠንቀቅ ይለቁታል።
በህገወጥ መንገድ የተገኘውን ገንዘብ ደግሞ 5ኛ ተከሳሽ ከአንደኛ ተከሳሽ ጋር በመሆን ምንጩን ለመደበቅ በማሰብ በተለያዩ መጠኖች ወጪ በማድረግ ለግል ጥቅም እንዳዋሉት የክስ መዝገቡ ያስረዳል።
ተከሳሾቹ ፍርድ ቤት ቀርበው ድርጊቱን ክደው የተከራከሩ ሲሆን ዐቃቤ ሕግ ያሉትን የሰው ምስክሮች ፣ አስረጂና ገላጭ የሰነድ ማስረጃዎች አቅርቧል።
ተከሳሾች የቀረበባቸውን ክስ መከላከል ስላልቻሉ ፍ/ቤቱ የጥፋተኝነት ፍርድ አስተላልፎባቸዋል። በዚህም ፦
1ኛ ተከሳሽ በ13 ዓመት ጽኑ እስራትና በ3 ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጣ፤
ከ2ኛ እስከ 4ኛ ተራ ቁጥር የተጠቀሱ ተከሳሾችን ደግሞ እያንዳንዳቸውን በ7 ዓመት ጽኑ እስራትና በ3 ሺህ ብር የገንዘብ ቅጣት እንዲቀጡ
5ኛ ተከሳሽ በ1 ዓመት እስራትና በ1 ሺህ ብር ገንዘብ እንዲቀጡ ፍርድ ቤት ወስኗል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የኤፍ ቢ ሲ (ታሪክ አዱኛ) መሆኑን ይገልጻል።
በድህረ ገጻችን ኢትዮ አማዞን በመግባት የሚፈልጉትን እቃ ማዘዝ ብቻ ሳይሆን የርስዎንም እቃዎች መሸጥ እንደሚችሉ ስናሳውቅዎት በደስታ ነው ። ለማስታወቂያ ወይንም ለመግቢያ ምንም ክፍያ አይጠበቅብዎትም፤ ለተጨማሪ መረጃ ድህረ ገጻችንን ይጎብኙ። https://ethio-amazon.com/
ለበለጠ መረጃ ሊንኩን በመንካት የቴሌግራም ግሩፓችንን ይቀላቀሉ!https://t.me/ethioamazon
ምንጭ (tikvahethiopia)