” የ4 ሰዎች አስክሬን ከተለያየ ቦታ አውጥተናል። …‘13 ሰዎች በጎርፍ ተወሰዱ’ የሚለው ትክክለኛ መረጃ አይደለም ” – አቶ ንጋቱ ማሞ Leave a comment

ከቀናት በፊት “ ሰዓሊተ ምህረት ጀርባ ያድሩ የነበሩ 13 የጎዳና ተዳዳሪ ልጆች በጎርፍ ተወስደው ሕይወታቸው እንዳለፈ አካባቢው ላይ ተነግሯል ” ሲሉ ነዋሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

በስፍራው የእሳት አደጋ ሠራተኞች ፣ ዋናተኞች፣ የፌደራል ፓሊስ አባላት ተገኝተው አስክሬን ለማውጣት እንቅስቃሴ ሲያደርጉ እንደተመለከቱ የገለጹ ሲሆን ፤ ቲክቫህ ኢትዮጵያም ስለጉዳዩ የአዲስ አበባ እሳትና አደጋ ሥራ አመረራር ኮሚሽንን ጠይቋል።

የኮሚሽኑ የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ በሰጡት ምላሽ፤ “ ባለፈው እንደገለጽነው የ4 ሰዎች አስከሬን አውጥተናል። ‘13 ሰዎች በጎርፍ ተወሰዱ’ የሚለው ትክክለኛ መረጃ አይደለም። ጥቆማ ከሆነ ሊሆን ይችላል ” ብለዋል።

“ ምክንያቱም በየትኛውም ጉዳይ ሕይወቱ ያለፈ ሰው ቢኖር ወይ እሳት አደጋ ወይ ፓሊስ ነው የሚያነሳው፤ በግለሰብ ደረጃ አስከሬን አንስቶ ቀብር ያለ አይመስለኝም ” ነው ያሉት።

“ በቦታው ነበርን ግን ይሄ አሁን የተጠቀሰው ቁጥር (13) አስከሬን አልተገኘም። ያገኘነው 4 አስከሬን ነው ” ያሉት አቶ ንጋቱ ፣ 4ቱን አስክሬን ለፓሊስ አስረክበናል ሲሉ አስረድተዋል።

4 አስክሬን የት አካባቢ ነው የተገኘው ? ለሚለው ጥያቄ፣ “ ሰዓሊተ ምህረትም፤ ከተለያዩ ቦታም ነው የገኘነው። ጎዳና ተዳዳሪ ይሁኑ፣ እዛው አካባቢ ነዋሪ ይሁኑ እኛ መረጃ የለንም። ፓሊስ ነው የሚያረጋግጠው ” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

“ አሁን የሚሉት ጥቆማ ትክክለኛነቱ የሚረጋገጥ ከሆነ ከፓሊስ ጋር ሆነን ፍለጋ እናካሂዳለን። አንዳንድ ጊዜ ጥቆማ ትክክል አይደለም የሚል መደምደሚያ ላይኖር ይችላል” ሲሉ ተናግረዋል።

ጎርፉ ተቋማትን ጨምሮ በንብረት ላይ ጉዳት ማድረሱን፣ በተደጋጋሚ እየደረሰ ያለው ኑሯቸውንና እንቅስቃሴያቸውን ወንዝ አካባቢ ባደረጉ ሰዎች እንደሆነ፣ ማህበረሰቡ ጥንቃቄ እንዲያደርግ፣ አደጋ ከደረሰም በ #939  የኮሚሽኑ ስልክ በፍጥነት ደውለው እንዲያሳውቁ አስገንዝበዋል።

በድህረ ገጻችን ኢትዮ አማዞን በመግባት የሚፈልጉትን እቃ ማዘዝ  ብቻ  ሳይሆን የርስዎንም እቃዎች መሸጥ እንደሚችሉ ስናሳውቅዎት በደስታ ነው ። ለማስታወቂያ ወይንም ለመግቢያ ምንም ክፍያ አይጠበቅብዎትም፤  ለተጨማሪ መረጃ   ድህረ ገጻችንን ይጎብኙ። https://ethio-amazon.com/

ለበለጠ መረጃ ሊንኩን በመንካት የቴሌግራም ግሩፓችንን ይቀላቀሉ!https://t.me/ethioamazon

ምንጭ(@tikvahethiopia)

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Cart

Your Cart is Empty

Back To Shop

የሚፈልጉትን ይዘዙን

Order what you want