አንድን ግለሰብ አስገድደው በያዙት ተሽከርካሪ ውስጥ በማገት ዶላርና የተለያዩ ንብረቶቹን ወስደዋል የተባሉ 3 የፖሊስ አባላት ላይ የፍትህ ሚኒስቴር የሙስና ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዐቃቤ ሕግ ክስ መስርቷል።
3ቱ የፖሊስ አባላት ፦
➡ ኮንስታብል ክብሩ በለጠ
➡ ረ/ሳጅን ያለምሰው ዱሬ
➡ ረ/ሳጅን ባህረዲን አለሙ ይባላሉ።
1ኛው ተከሳሽ በፌደራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ መምሪያ የተጠርጣሪ አስተዳደር ስር የጥበቃ አባል፣
2ኛው ተከሳሽ የተጠርጣሪ ክትትል እና ኦፕሬሽን ክፍል የኢኮኖሚ ነክ ጉዳዮች ወንጀሎች የፍርድ ቤት አስገዳጅ አባል፣
3ኛው ተከሳሽ በፎረንሲክ ምርመራ መምሪያ ስር በሹፌርነት ሲሰሩ ነበር።
ሰኔ 3 ቀን 2016 ዓ/ም ከቀኑ በ9 ሰዓት አካባቢ በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ‘ ጆን ጋራዥ ‘ አካባቢ ካልተያዘ ሲቪል ከለበሰ ግብረአበራቸው ጋር በመሆን አንድ የግል ተበዳይን አስገድደው 3ኛ ተከሳሽ ለስራ አላማ የተረከበው ተሽከርካሪ ውስጥ በማገት ያስገባሉ።
አግተው ተሽከርካሪ ውስጥ ካስገቡም በኃላ ከግል ተበዳዩ ፦
° 2 ሺህ 600 ዶላር፣
° 2 የእጅ ስልክ
° 50 ሺህ ብር አስገድደው በመውሰድ ከተሽከርካሪው ገፍትረው ጥለውት እንደሄዱ በዐቃቤ ህግ የቀረበው የክስ መግዘብ ያስረዳል።
የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 4ኛ የሙስና ጉዳዮች ወንጀል ችሎት በዐቃቤ ሕግ የተመሰረተውን ክስ ዝርዝር ለተከሳሾች እንዲደርሳቸው ካደረገ በኋላ ጉዳያቸውን ማረሚያ ቤት ወርደው እንዲከታተሉ በማዘዝ ለሰኔ 26 ቀን 2016 ዓ/ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል። #ኤፍቢሲ
በድህረ ገጻችን ኢትዮ አማዞን በመግባት የሚፈልጉትን እቃ ማዘዝ ብቻ ሳይሆን የርስዎንም እቃዎች መሸጥ እንደሚችሉ ስናሳውቅዎት በደስታ ነው ። ለማስታወቂያ ወይንም ለመግቢያ ምንም ክፍያ አይጠበቅብዎትም፤ ለተጨማሪ መረጃ ድህረ ገጻችንን ይጎብኙ። https://ethio-amazon.com/
ለበለጠ መረጃ ሊንኩን በመንካት የቴሌግራም ግሩፓችንን ይቀላቀሉ!https://t.me/ethioamazon
ምንጭ (@tikvahethiopia )