ግዙፉ የእስያ ባንክ 4 ሺህ ሠራተኞቹን አሰናብቶ ሥራቸውን በኤአይ ሊተካ ነው……. Leave a comment

በአህጉረ እሲያ ግዙፉ የሆነው የሲንጋፖር ባንክ በሚቀጥሉት ሦስት ዓመታት 4 ሺህ ሠራተኞችን አሰናብቶ ሥራቸውን በሰው ሠራሽ አስተውሎት (ኤአይ) ሊተካ መሆኑን አስታውቋል።

ባንኩ በአሁኑ ወቅት በሰዎች የሚሠሩ ተግባራትን በኤአይ በታገዘ መልኩ ለመከወን አቅዷል።

ይህ ዲቢኤስ የተባለው ብንክ ቃል አቀባይ ለቢቢሲ እንደተናገሩት ባንኩ “በሚቀጥሉት ጥቂት ዓመታት በጊዜያዊነት እና በኮንትራክት የተቀጠሩ ሠራተኞችን መቀነስ” ይጀምራል።

በቋሚነት የተቀጠሩ ሠራተኞች ሥራቸውን እንደማያጡ ተነግሯል።

ተሰናባቹ የባንኩ ሥራ አስፈፃሚ ፖዩሽ ጉፕታ እንደተናገሩት 1 ሺህ ገደማ የሚሆኑ አዲስ የሥራ ቦታዎች በሰው ሠራሽ አስተውሎት (ኤአይ) ይሸፈናሉ።

ዲቢኤስ በኤአይ ምክንያት ሠራተኞቹን ለማሰናበት ያቀደ የመጀመሪያው ባንክ ሆኗል።

ኩባንያው በሲንጋፖር ከሚገኙ ሠራተኞች መካከል ምን ያክሉ ሥራቸውን ሊያጡ እንደሚችሉ እንዲሁም ምን ዓይነት የሥራ ቦታዎች እንሚዘጉ ዝርዝር መረጃ ከመስጠት ተቆጥቧል።

ዲቢኤስ በአሁኑ ወቅት ከ8 እስከ 9 ሺህ ድረስ ጊዜያዊ እና በኮንትራክት የሚሠሩ ሠራተኞች አሉት። ባንኩ በጠቅላላው 41 ሺህ ሠራተኞች አሉት።

ባለፈው ዓመት ሥራ አስፈፃሚው ጉፕታ ባንኩ በኤአይ ላይ ላለፉት 10 ዓመታት ሲመራመር እንደቆየ ተናግረው ነበር።

“ዛሬ 800 የኤአይ ሞዴሎችን ወደ ሥራ እናሰማራለን። ይህም በ2025 አንድ ቢሊዮን ዶላር የሚያወጣ ምጣኔ ሀብታዊ ተፅዕኖ ሊኖረው እንደሚችል ይገመታል” ብለዋል።

ሥራ አስፈፃሚው በአውሮፓውያኑ መጋቢት መገባደጃ ላይ ሥራቸውን ይለቃሉ ተብሎ ይጠበቃል። ምክትላቸው ታን ሱ ሻን ተክተዋቸው እንደሚሠሩም ተነግሯል።

ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (አይኤምኤፍ) ባለፈው ዓመት ባወጣው መግለጫ በሰው ሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂ ምክንያት በዓለም አቀፍ ደረጃ 40 በመቶ ያህል የሥራ ቦታዎች ሊነኩ እንደሚችሉ አስታውቆ ነበር።

የአይኤምኤፍ ማኔጂንግ ዳይሬክተር ክሪስታሊና ጆርጂየቫ “በአብዛኛው ኤአይ እኩልነትን ሊጎዳ ይችላል” የሚል አስተያየት ሰጥተዋል።

የባንክ ኦፍ ኢንግላንድ ገዢ አንድሩ ቤይሊ ባለፈው ዓመት ለቢቢሲ በሰጡት አስተያየት ኤአይ “የሥራ ፀር አይሆንም” ብለው እንደነበር አይዘነጋም። አክለው የሰው ልጅ ከኤአይ ጋር እንዴት ሊሠራ እንደሚችል መማር አለበት ብለዋል።

በድህረ ገጻችን ኢትዮ አማዞን በመግባት የሚፈልጉትን እቃ ማዘዝ  ብቻ  ሳይሆን የርስዎንም እቃዎች መሸጥ እንደሚችሉ ስናሳውቅዎት በደስታ ነው ። ለማስታወቂያ ወይንም ለመግቢያ ምንም ክፍያ አይጠበቅብዎትም፤  ለተጨማሪ መረጃ   ድህረ ገጻችንን ይጎብ/ኙ። https://ethio-amazon.com/

ለበለጠ መረጃ ሊንኩን በመንካት የቴሌግራም ግሩፓችንን ይቀላቀሉ!https://t.me/ethioamazon

ምንጭ፡– (ቢቢሲ)

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Cart

Your Cart is Empty

Back To Shop