ጥያቄ ያስነሳው ሰኔ ላይ የኢትዮጵያን የዋጋንረት ወደ 20% የማውረድ ዕቅድ Leave a comment

30 ህዳር 2023

በኢትዮጵያ አሳሳቢ የሆነውን የዋጋ ንረት በዚህ ዓመት መጨረሻ ላይ ወደ 20 በመቶ ዝቅ ለማድረግ ዕቅድ ይዞ እየሠራ ያለው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ፣ ዕቅዱ ምን ያህል እውን ሊሆን የሚችል ነው በሚለው ላይ ጥያቄ እየተነሳ ነው። ነገር ግን የብሔራዊው ባንክ ገዢ አቶ ማሞ ምህረቱ ባንኩ በያዘው ዕቅድ መሠረት በቀጣዮቹ ሰባት ወራት ውስጥ በአገሪቱ ያለውን የዋጋ ንረት ወደ 20 በመቶ ለመቀነስ እየሠሩ መሆናቸውን አስረግጠው ተናግረዋል። ይህ የባንኩ ዕቅድ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴየተለጠጠ ነውየሚል ጥያቄ የተነሳበት ሲሆን፣ አንድ የምጣኔ ሃብት ባለሙያም የባንኩ ዕቅድ በዚህ አጭር ጊዜሊደረስበት የሚችል አይደለምሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። አቶ ማሞ ከዋጋ ንረት ጋር በተያያዘ የብሔራዊ ባንክን ዕቅድ እና ሥራን በተመለከተ ማብራሪያ የሰጡት ረቡዕ ኅዳር 19/2016 .. የተቋማቸውን የሩብ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፕላን፣ በጀት እና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ባቀረቡበት ወቅት ነው።

አቶ ማሞግልጽ በሆነ መልኩ በዓመቱ መጨረሻ ሰኔ ወር ላይ የዋጋ ንረቱን 20 በመቶ ለማድረስ መሥራት እንደ ዕቅድ ይዘናል። በሚቀጥለው ዓመት ሰኔ ላይ ደግሞ ወደ 10 በመቶ ለመቀነስ እንሠራለን ብለናልሲሉ የባንኩን ዕቅድ አብራርተዋል። ኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባለፈው ዓመት መጨረሻ ላይ የዋጋ ንረትን ለማረጋጋት የገንዘብ ፖሊሲ ማሻሻያ ባደረገበትም ወቅት ይሄንኑ ተመሳሳይ ዕቅድ ይፋ አድርጎ ነበር። በተወካዮች ምክር ቤት በነበረው የዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ ላይ ይህ የብሔራዊ ባንኩ ዕቅድ ተግባራዊነት ጥያቄ ተነስቶበታል። የፕላን፣ በጀት እና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢው / አብርሃም አለማየሁባንኩ የዋጋ ንረትን ወደ 20.3 በመቶ አደርሳለሁ ብሎ ያስቀመጠው ዕቅድ የተለጠጠ ነውሲሉ ተናግረዋል። / አብርሃም ዕቅዱ ላይየተለጠጠ ነውየሚል ትችት ቢያቀርቡም፤መከፈል ያለበት መስዋትነት ተከፍሎ ወደዚህ [ዕቅድ] ለመድረስ የሚያስችሉ ሥራዎችን መሥራት ግን አስፈላጊ መሆኑንአጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል። / ሚልኪያስ አየለ የተባሉ የፕላን በጀት እና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባል ደግሞ፤ተቋሙ ያስቀመጠውን ዓመታዊ የዋጋ ግሽበትን ወደ 20.3 በመቶ የማውረድ ግብን ለማሳካት ምን አስቻይ ሁኔታዎች አሉ?” የሚል ጥያቄ አቅርበዋል። / ሚሊኪያስ አክለውምየዋጋ ንረትን ለማረጋጋት የተወሰዱ የገንዘብ ፖሊስ ማሻሻያ እና አስተዳደራዊ እርምጃዎች ውጤታማነት እንዴት ይታያል?” ሲሉ ጠይቀዋል።

ለተነሱት ጥያቄዎች ምላሽ የሰጡት የባንኩ ገዢ፤የገንዘብ ፖሊሲ እርምጃዎች የተወሰዱት በቅርብ ጊዜ ቢሆንም፣ ካለፈው ነሐሴ ወር ጀምሮ አንዳንድ ለውጦችን ማየት ጀምረናልብለዋል። ለዚህም በብረት፣ በሲሚንቶ እና ከውጭ በሚገቡ ሸቀጦች ላይ የታየውንየዋጋ መቀነስበማሳያነት ጠቅሰዋል። አንድ ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈቀዱ የምጣኔ ሃብት ባለሙያ እና ተመራማሪ ግን ይህ የብሔራዊ ባንክ ዕቅድ ተግባራዊነትአጠያያቂ ነውሲሉ ጥርጣሬያቸውን ለቢቢሲ ገልጸዋል። ባለሙያው የባንኩ ዕቅድ ተግባራዊነት አጠያያቂ የሚሆንበትን ምክንያት ሲብራሩ፤ዓለም አቀፍ ተጽዕኖዎች፣ የኢኮኖሚ መዋቅር ችግር፣ ተፈጥሯዊ የአቅርቦት እና ፍላጎት ችግር ባለበት ሁኔታ ትንሽ ከአምናው ዘንድሮ ቀነስ ያለ ነገር ስላለ ብሔራዊ ባንክ ብቻውን ይሄን እወጣዋለሁ ማለትየመፎከርዓይነት እንጂ የሚሳካ አይደለም። ምክንያቱም የችግሩ ስፋት ጠለቅ ያለ ነውይላሉ።

ባለፈው ዓመት ጥር ወር በብሔራዊ ባንክ ገዢነት የተሾሙት አቶ ማሞ ምህረቱ ለምክር ቤቱ ባቀረቡት ሪፖርታቸው ላይ ከዳሰሷቸው ጉዳዮች መካከል በአገሪቱ አሳሳቢ የሆነው የዋጋ ንረት ጉዳይ ዋነኛው ነው። የማዕከላዊው ባንኩ ገዢ በሪፖርታቸው ላይ ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ የዋጋ ንረትበተከታታየይ ቅናሽ አስመዝግቧልሲሉ ተደምጠዋል። አቶ ማሞ ዋጋ ንረቱ እሳቸው በባንኩ ገዢነት ከተሾሙ ሁለት ወራት በኋላ መጋቢት 2015 .. የነበረው የዋጋ ንረት 35 በመቶ፣ መስከረም 2016 ላይ ወደ 27̀.7 በመቶ ቅናሽ ማሳየቱን በአስረጂነት አቅርበዋል። የባንኩ ገዢ ይህንን ቢሉም ምግብ ነክ ያልሆኑ ሸቀጦች የዋጋ ንረት አሁንም 30 በመቶ በታች አለመውረዱን ግን አልሸሸጉም። ይህ የሆነበትን ምክንያት ሲያብራሩም፤የቤት ኪራይ የመድኃኒት እና የሕክምና አገልግሎት እንዲሁም የቤት ዕቃዎች ዋጋ በመጨመሩ ነውብለዋል።እንደ አጠቃላይ ሲታይ ዋጋ ንረት የቆየ ችግር ነውያሉት አቶ ማሞ፤ነገር ግን የዋጋ ንረት እየቀነሰ እንደሆነ ማየት ይቻላልሲሉ የሚመሩትን ተቋም ለሚከታተሉት የአገሪቱ ሕግ አውጪዎች ተናግረዋል።

አቶ ማሞ ትናንት ረቡዕ ባቀረቡት ሪፖርታቸው ላይ በኢትዯጵያ ለሚታየው የዋጋ ንረት አምስት ምክንያቶችን አቅርበዋል። የዓለም አቀፍ የሸቀጦች ዋጋ መናር ከምክንያቶቹ መካከል ቀዳሚው ነው።  የትራንስፖርት አውታሮች፣ የሎጀስቲክስ ሥርዓት እና የችርቻሮ ንግድ ተወዳዳሪነት፣ የአቅርቦት እና የፍላጎት አለመመጣጠን እንዲሁም የፊስካል እና የገንዘብ ፖሊሲ ልል መሆንም በአቶ ማሞ በምክንያትነት ተነስተዋል። አቶ ማሞበአንዳንድ የኢትዮጵያ ክፍሎች ውስጥ ያለው የፖለቲካ አለመረጋጋት እንዲሁም አሁን ለሚታየው የዋጋ አለመረጋጋት የራሱን አስተዋጽኦ አድርጓልሲሉ የአገሪቱ የፀጥታ ሁኔታ ለዋጋ ንረት ምክንያት መሆኑንም ጠቁመዋል። በአገሪቱ የሚስተዋለውን የዋጋ ንረት ለመቆጣጠር ብሔራዊ ባንክ የወሰዳቸውንም እርምጃዎች አቶ ማሞ ለቋሚ ኮሚቴ አባላቱ አብራርተዋል። በዚህም መሠረትመንግሥት ከብሔራዊ ባንክ የሚወስደውን ቀጥታ ብድር 75 በመቶ እንዲቀንስ አድርገናል። ይህን ያደረግንበት ቁልፍ ምክንያት በኢትዮጵያ ውስጥ የተረጋጋ የዋጋ ሁኔታ እንዲኖር ለማስቻል ነውሲሉ ምክንያቱን አስረድተዋል። አቶ ማሞ አክለውምአሁን ባለን ግምገማ አንዳንድ ለውጦች መታየት ጀምረዋል። አንዳንድ ምርቶች ላይ የዋጋ መረጋጋት ከዚያም አልፎ የመቀነስ አዝማሚያ እያየን ነውሲሉ ተናግረዋል። አቶ ማሞ እየታየ ነው ካሉትለውጥበተጨማሪ ባንኩባልተለመደ ሁኔታ ዋጋ ንረትን በተመለከተ ራሳችን ተጠያቂ (accountable) የምንሆንበት በተቻለ መጠን ለማሳካት ጥረት የምናደርገው ዕቅድ አውጥተናልሲሉ ለተግባራዊነቱ ቁርጠኛ መሆናቸውን አመልክተዋል።

 ባለፉት ዓመታት የአገር ውስጥ እና ዓለም አቀፋዊ ክስተቶች ባስከተሉት ጫና ምክንያ በኢትዮጵያ ውስጥ የታየው የዋጋ ንረት ከዚህ ቀደም ታይቶ ከሚታወቀው የከፋ መሆኑ ሲነገር ቆይቷል። የዋጋ ንረቱ በተከታታይ ሲጨምር ቆይቶ 35 በመቶ በላይ ደርሶ እንደነበር ይታወቃል። ይህ ሁኔታም በከተሞች እና በገጠር አካባቢዎች ጭምር ባለው ሕዝብ የዕለት ከዕለት ሕይወት ላይ ከባድ ጫናን ከመፍጠሩ በተጨማሪ የመሻሻል ሁኔታዎች ሳይታዩበት ቆይቷል። በዚህም ሳቢያ ባለፈው ዓመት ማብቂያ ላይ የዋጋ ንረቱን ለመቆጣጠር እና ለመቀነስ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የፖሊሲ ማሻሻያ ለማድረግ የሚያስችሉትን ውሳኔዎች ይፋ አድርጎ የተለያዩ እርምጃ እየወሰደ ይገኛል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Cart

Your Cart is Empty

Back To Shop