“ጦርነትን ለማውገዝ” በአዲስ አበባ ሊካሄድ የታቀደው ሰልፍ መከልከሉ በመንግሥት ባለሥልጣን ተቃውሞ ገጠመው Leave a comment

 በአማራ እና በኦሮሚያ ክልሎች የሚካሄደው ደም አፋሳሽ ግጭት እንዲቆም ለመጠየቅ በአዲስ አበባ ሊካሄድ ታቅዶ የነበረው ሰልፍ መከልከሉ በሰላም ሚኒስቴር ከፍተኛ ባለሥልጣን ተቃውሞ ገጠመው።

የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ የሆኑት አቶ ታዬ ደንደአ ይፋዊ በሆነው የፌስቡክ ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት ጽሑፍ፣የጦርነት ከበሮ በመታንበት አደባባይ ዜጎች በሰላማዊ ሰልፍ ጦርነትን እንዳይቃወሙ መከልከል መጥፎ ትርጉም አለውብለዋል።

ለመገናኛ ብዙኃን በሚሰጧቸው ቃለ ምልልስ እና በማኅበራዊ ሚዲያ ገጻቸው በሚያጋሯቸው ጽሑፎች መንግሥታቸውን በመክሰስ የሚታወቁት ሚኒስትሩ ዛሬ ረፋድ ላይ ባጋሩት ጽሑፍ፣ ሰልፉ በመከልከሉለመመለስ የሚከብድ ጥያቄ ሊነሳብን ይችላልሲሉም ስጋታቸውን ገልጸዋል።

መንግሥታቸው ሥልጣን ከተረከበ በኋላ በአገሪቷ ውስጥ የተከሰቱ ጦርነቶች፣ ግጭቶችን እና አፈናዎችን በማንሳትምየኢትዮጵያ ሕዝብ ለዴሞክራሲ የከፈለውን ውድ ዋጋ አራክሰናልሲሉ መንግሥት የወሰደውን እርምጃ ኮንነዋል።

ዛሬ በአዲስ አበባ ከተማ ሊካሄድ ታቅዶ የነበረውን ሰላማዊ ሰልፍ ሲያስተባብሩ ከነበሩ ፖለቲከኞች መካከል አራቱ ሐሙስ ዕለት ኅዳር 27/ 2016 . በፖሊስ መያዛቸው የተገለጸ ሲሆን፣ ከዚሁ ጋር በተያያዘ 97 ሰዎች በቁጥጥር መዋላቸውንም መንግሥት አስታውቋል።

አስተባባሪዎቹ በቁጥጥር ሥር የዋሉትየታቀደውን ሰላማዊ ሰልፍ ለማስቀረት ነውየሚል ጥርጣሬ እንዳላቸው ከሰልፉ አስተባባሪዎች አንዱ የሆኑት የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ) ሊቀመንበር ረዳት ፕሮፌሰር ዝናቡ አበራ ለቢቢሲ ተናግረው ነበር።

ሰልፉ በአማራ እና በኦሮሚያ ክልሎችደም አፋሳሽ ተግባር ውስጥይገኛል ያሉት የመከላከያ ሠራዊትያለምንም ቅድመ ሁኔታ ወደ ጠቅላይ ጦር ሰፈሩ እንዲገባ በአዲስ አበባ፣ በኦሮሚያ እና ሲዳማ ክልሎችያለ ምንም ምክንያትየታሰሩ የአማራ ተወላጆች ከእስር እንዲፈቱ እና በአገሪቷ ያሉ ተፈናቃዮችበአስቸኳይ ወደቀያቸው እንዲመለሱ ለመጠየቅ ያለመ መሆኑንም አስተባባሪዎቹ ገልጸው ነበር

ከአስተባባሪዎቹ መታሰር በኋላ ምሽት ላይ ከፀጥታ እና ደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይል የወጣ መግለጫ ደግሞበሰላማዊ ሰልፍ ሽፋን አዲስ አበባ ውስጥ ሁከት እና ብጥብጥ ለመፍጠር በኅቡዕ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ቡድኖች ሴራ መክሸፉንገልጿል።

ነገር ግን በጸጥታ ኃይሉ ከተያዙት ሰዎች መካከል አራቱ የሰልፉ አስተባባሪዎች ስለመኖራቸው መግለጫው ያለው ነገር የለም።

ዛሬ በአዲስ አበባ ሊካሄድ ታቅዶ የነበረው ሰላማዊ ሰልፍ መቼ እንደሆነ ባይገለጽም ለሌላ ጊዜ መተላለፉ ተዘግቧል።

የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ታዬ ደንደአ በማኅበራዊ ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ በሰላማዊ መንገድ መቃወም ወይም መደገፍ የዴሞክራሲ ምሰሶ መሆኑን ገልጸው፣ኢህአዴግም ሰላማዊ ሰልፎችን ሲከልክል አምባገነን በማለት ስንከስና ስንኮንን ነበር፤ ዛሬ ደግሞ በመስቀል አደባባይ ሰላማዊ ሰልፍ እንዳይደረግ ከልክለናልሲሉ በመንግሥታቸው የተሻለ ነገር እንደሌለ አመልክተዋል።

አቶ ታዬ ዜጎች በሰላማዊ መንገድ ጦርነት እንዳይቃወሙ የከለከሉትን አካላት ተጠያቂ ማድረግ እንደሚገባም ገልጸዋል። አቶ ታዬ ያሉበትን መንግሥት የሚከሱ እና የሚሞግቱ ሃሳቦችን በመሰንዘር ይታወቃሉ።

ቀደም ብሎ ለቢቢሲ የኦሮምኛ ክፍል በሰጡት ቃለ ምልልስ ላይም መንግሥት በሽብርተኝነት ከፈረጀው እና ሸኔ እያለ ከሚጠራው ከኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ታጣቂ ቡድን ጋር በታንዛንያ፣ ዳሬሰላም የተካሄደው ድርድር ላለመሳካቱ መንግሥታቸው ላይ ጣታቸውን ቀስረዋል። በተለያዩ ጊዜያት በአገሪቷ እየተፈጠሩ ባሉ ችግሮች ዙሪያ ስጋታቸውን እንደገለጹ ያስታወሱት አቶ ታዬ፣ሰሚ አጥቻለሁብለዋል።

አቶ ታዬ የኦሮሚያ ክልል ምክር ቤት (ጨፌ) አባል ሲሆኑ አገሪቷን በሚያስተዳድረው የብልጽግና ፓርቲ ውስጥ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባል ሆነው ያገለግላሉ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Cart

Your Cart is Empty

Back To Shop