የብሔራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምሕረቱ ፥ እስካሁን ባለው ከዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (IMF) እና ዓለም ባንክ 2 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር ወደ ብሔራዊ ባንክ ገቢ መደረጉን ተናግረዋል።
በሌላ በኩል ፥ ከውጭ ከሚገቡ የፍጆታ ዕቃዎች 18 በመቶ ብቻ በውጭ ምንዛሬ እንደሚመጡ ገልፀዋል።
ሌሎቹ በአብዛኛው በኢ-መደበኛ ወይም በትይዩ ገበያ ወደ ሀገር ቤት ሲገቡ እንደነበር ጠቁመዋል።
በዚህም ” የምንዛሬ ተመኑ ወደ ገበያ መር መለወጡ በሸቀጦች ዋጋ ላይ ጭማሪ ሊፈጥር አይገባም ” ሲሉ ገልጸዋል።
ባንኩ ህገ-ወጥነትና አሉታዊ ጫና የሚፈጥሩ ጉዳዮች ከተከሰቱ ህጋዊ ምላሽ ለመስጠት መዘጋጀቱን ተናግረዋል።
በሌላ በኩል ፤ በፋይናንስ ተቋማት ላይ የሚከሰትን ህገወጥ አሰራር ለመቆጣጠር ጥብቅ የፊሲካል እና የገንዘብ ፖሊሲ ገቢራዊ ይደረጋል ሲሉ አውጀዋል።
በዚህም ” ቴክኖሎጂን መሰረት ያደረገ በቂ ዝግጅት አድርገናል ” ብለዋል።
በድህረ ገጻችን ኢትዮ አማዞን በመግባት የሚፈልጉትን እቃ ማዘዝ ብቻ ሳይሆን የርስዎንም እቃዎች መሸጥ እንደሚችሉ ስናሳውቅዎት በደስታ ነው ። ለማስታወቂያ ወይንም ለመግቢያ ምንም ክፍያ አይጠበቅብዎትም፤ ለተጨማሪ መረጃ ድህረ ገጻችንን ይጎብ/ኙ። https://ethio-amazon.com/
ለበለጠ መረጃ ሊንኩን በመንካት የቴሌግራም ግሩፓችንን ይቀላቀሉ!https://t.me/ethioamazon
ምንጭ፡– (@tikvahethiopia)