የአውስትራሊያ ቴሌኮም ሥራ አስኪያጅ ኔትዎርክ ለሰዓታት በመቋረጡ ሥልጣናቸውን ለቀቁ Leave a comment

ኦፕተስ የተባለው የአውስትራሊያው ቴሌኮም አገልግሎት ኃላፊ ኔትዎርክ በሃገሪቱ ኔትዎርክ በመቋረጡ ሥልጣናቸውን ለቀዋል።

ኬሊ ባየር ሮዝማሪን ለሶስት ዓመታት መሥሪያ ቤቱን ካገለገሉ በኋላ ነው በደረሰባቸው ጫና ምክንያት ከመንበራቸው የተነሱት።

በያዝነው የአውሮፓውያኑ ወር ኔትዎርክ በመቋሯጡ ምክንያት ግማሽ አውስትራሊያ ከግንኙነት ውጭ ሆኗል።

አልፎም ባለፈው ዓመት እሳቸው በሚመሩት መሥሪያ ቤት የመረጃ ደኅንነት ጥሰት ተፈፅሟል የሚል ክስ ይደርስባቸዋል።

ኃላፊዋ በለቀቁት መግለጫመሥሪያ ቤቱን በማገልገሌ ክብር ይሰማኛልብለው ነገር ግን ከሥልጣን መውረዳቸው ተገቢ እንደሆነ ገልጠዋል።

ከራሴ ጋር ለመምከር ጊዜ ከወሰድኩ በኋላ ሥልጣኔን በገዛ ፈቃዴ መልቀቄ ኦፕተስ ወደፊት እንዲራመድ ትክክለኛው እርምጃ ነው ብዬ አምናለሁብለዋል።

ባየር ሮዝማሪንን የሚተካ ኃላፊ እስኪገኝ ድረስ የቴሌኮም አገልግሎቱ ዋና የፋይናንስ ኦፊሰር የሆኑት ማይክል ቬንተር የኦፕተስ ሥራ አስኪያጅ ሆነው ያገለግላሉ።

የኦፕተስ እናት ኩባንያ የሆነው የሲንጋፖሩ ሲንግቴል ግሩፕ ዋና ሥራ አስኪያጅ ዩዌን ሙን፤ ለሮዝማሪን ያላቸውን ክብር በምስጋና ገልጠዋል።

· 

በተለይ ደግሞ የተሾሙትበፈታኙየኮቪድ ወቅት ቢሆንም ፋይናንስ ዘርፉ እንዲያድግ ትልቅ አስተዋፅዖ አድርገዋል ብለዋል።

በአውስትራሊያ የኦፕተስ ቴሌኮም አገልግሎት የተቋረጠው በአውሮፓውያኑ ኅዳር 8 ነበር።

10 ሚሊዮን የሚሆኑ የአግልግሎቱ ተጠቃሚዎች የሞባይልም የሆነ የኢንተርኔት አገልግሎት 12 ሰዓታት ተቋርጦበቸዋል።

በኔትዎርክ መቋረጥ ምክንያት የትራንስፖርት አገልግሎት ተስተጓጉሏል፤ የሆስፒታል መስመሮች ተቋርጠዋል፤ የክፍያ አገልግሎትም ከጥቅም ውጭ ሆኗል፤ አልፎም 200 ሰዎች የአደጋ ጊዜ ጥሪ ማድረግ አልቻሉም።


ባየር ሮዝማሪን በወቅቱ በሰጡት ምላሽ ምክንያት ብዙ ትችት ያስተናገዱ ሲሆን ባለፈው አርብ በአውስትራሊያ ምክር ቤት ቀርበው ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በማብራሪያቸው ወቅት በሺዎች የሚቆጠሩ አውስትራሊያዊያን ቴሌኮሙን ካሳ እየጠየቁ እንደሆነ ገልጠዋል።

ኩባንያው ከዚህም አልፎም መስከረም 2022 በተከሰተው የመረጃ ጥሰት ምክንያት 100 ሺህ ገደማ ሰዎች ክስ እንደመሰረቱበት ተሰምቷል።

10 ሚሊዮን ገደማ ሰዎች በመረጃ ጥሰቱ የተጠቁ ሲሆን በአውስትራሊያ ታሪክ ትልቁ ነው ተብሏል።

ኦፕተስ በወቅቱ ይቅርታ ጠይቆ በጣም ውስብስብ የሆነ የሳይበር ጥቃት ነው ለዚህ የዳረገኝ ብሏል።

ነገር ግን ተቺዎችም ሆኑ የሃገሪቱ የሳይበር ሴኪዩሪቲ ሚኒስትር በኩባንያውንዝህላልነት ምክንያት ነውመረጃ የተሰረቀው ሲሉ ይወቅሳሉ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Cart

Your Cart is Empty

Back To Shop

የሚፈልጉትን ይዘዙን

Order what you want