-25%

Fiction Books


$30.00 $40.00

  • ETB: Br3,726.00
  • UGX: UGX110,511.00

Compare

ደራሲ በዓሉ ግርማ በኢሊባቡር ክፍለ ሀገር ሱጴ በምትባል ሥፍራ በ1928 ዓ.ም. ተወለዱ። ዕድሜያቸው ለትምሕርት ሲደርስ የአንደኛ ደረጃ ትምሕርታቸውን በልዕልት ዘነበወርቅ ትምሕርት ቤት ፤ ሁለተኛ ደረጃ ትምሕርታቸውን ደግሞ በጄኔራል ዊንጌት ትምሕርት ቤት አጠናቀዋል። ከዚያም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በፖሊቲካል ሳይንስ እና ኢንተርናሽናል ሪሌሽንስ የ ቢ.ኤ. ዲግሪ ያገኙ ሲሆን፤ በዚሁ ተመሳሳይ መስክ ከአውሮፓ የማስተርስ ዲግሪያቸውን አግኝተዋል።

ደራሲ በዓሉ ግርማ በተለይ በልብ ወለድ እና በፈጠራ የሥነ ጽሑፍ ሥራዎች ከታወቁት የኢትዮጵያ የዘመኑ ደራሲዎች መካከል ተወዳጅነትና ዝናን ያተረፉ ዕውቅ ደራሲ ነበሩ። ከጻፏቸው በርካታ ድርሰቶቻቸው ውስጥ «ከአድማስ ባሻገር» የተሰኘው መጽሐፋቸው በሩስኛ ቋንቋ ተተርጉሞ በቀድሞዋ የሶቪየት ሶሽያሊስት ሕብረት ሪፑብሊክ ቀርቧል። በተጨማሪም በጋዜጠኝነት ሙያም ስማቸውን ያስጠሩ፤ ሙያቸውንም ያስከበሩ ደራሲ ነበሩ። «የዛሬይቱ ኢትዮጵያ» ጋዜጣ፤ የመነን መጽሔት፤ የአዲስ ሪፖርተር መጽሔት፤ የአዲስ ዘመን ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ በመሆን ከመሥራታቸውም ባሻገር፤ ብዙ ወጣት ጋዜጠኞችን ለማፍራት ጥረት አድርገዋል። አዲስ ሪፖርተር የተባለውን መጽሔትም ደረጃው ከፍ እንዲልና በዓለም አቀፍ ደረጃ እንዲገመገም አድርገዋል። በጋዜጠኝነት ሙያቸው በኢትዮጵያ ራዲዮ ሠርተዋል።

ደራሲ በዓሉ ግርማ ለኢትዮጵያ ሥነጽሑፍ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረከቱና ብዙ ሥራዎችን ያቀረቡ ሲሆን፤ የመጨረሻው መጽሐፋቸው «ኦሮማይ» በመባል ይታወቃል። ይኼውም መጽሐፍ በወቅቱ በነበረው የደርግ መንግሥት ሊደገፍ ባለመቻሉ በ1976 ዓ.ም. ለደራሲው ሕይወት መጥፋት መንስኤ ሊሆን በቅቷል።

Product Code: N/A Category:

Based on 0 reviews

0.0 overall
0
0
0
0
0

Be the first to review “Fiction Books”

There are no reviews yet.

Cart

Your Cart is Empty

Back To Shop