ለናይጄሪያ ወላጅ አልባ ታዳጊዎች የታቀደው የጅምላ ሰርግ ቁጣ አስነሳ Leave a comment

በናይጄሪያ ወደ 100 ለሚጠጉ ወላጅ አልባ ሴት ታዳጊዎች ሊካሄድ የታቀደው የጅምላ ሰርግ በአገሪቱ ከፍተኛ ቁጣ ቀሰቀሰ።

ከወላጅ አልባዎቹ መካከል አንዳንዶቹ እድሜያቸው ያልደረሱ ታዳጊዎች ሊገኙበት እንደሚችል ተፈርቷል።

የጅምላ ሰርጉ የታቀደው በሚቀጥለው ወር ነው።

ሰርጉ ይደረግበታል የተባለው የተባለው የሰሜናዊ ምዕራብ ኒጀር ግዛት ሰላማዊ ሰዎች ላይ ያነጣጠረ ጥቃቶች በተደጋጋሚ የሚፈጸምበት አካባቢ ነው።

እነዚህ ወላጅ አልባዎች በታጠቁ ሽፍቶች ወላጆቻቸን አጥተዋል።

የናይጄሪያ የሴቶች ጉዳይ ሚንስትር ኡጁ ኬኔዲ-ኦሃንዬ የታቀደውን የሰርግ ስነ ስርዓት ለማስቆም ለፍርድ ቤት ትዕዛዝ ማስተላለፋቸውን ተናግረዋል።

የጅምላ ሰርጉን እያገዙ ያሉት የኒጀር ግዛት ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አብዱልማሊክ ሳሪን-ዳጂ ሲሆኑ የአካባቢው የሃይማኖት አባቶች የገንዘብ ድጋፍ እንዲያደርጉላቸው ጠይቀዋቸው እንደሆነ መናገራቸው በሪፖርቶች ወጥተዋል።

የኒጀር ኢማሞች ጉባኤ በበኩሉ የታዳጊዎቹ ዕድሜ ህጉ ከሚፈቅደው 18 ዓመት በታች እንዳልሆነ አጽንኦት ሰጥተው ሰርጉ ሊፈቀድ ይገባል ሲል ተከራክሯል።

ሆኖም ታዛቢዎች አንዳንዶቹ ከ18 ዓመት በታች ሊሆኑ እንደሚችሉ እና የገንዘብ ጥቅም ለማግኘት ሲሉ ለመታዘዝ እንደሚገደዱ ያላቸውን ስጋት ገልጸዋል።

ሚኒስትሯ ታዳጊዎቹ “ የተሻለ ህይወት ይገባቸዋል” ያሉ ሲሆን መስሪያ ቤታቸው የ100ዎቹን ሴቶች ማንነት፣ ዕድሜያቸውን እና ለትዳር ፈቃደኛ ናቸው በሚሉ ጉዳዮች ላይ እየመረመረ ነው ብለዋል።

አክለውም ለታዳጊዎቹ ትምህርት እና ስልጠና ለመስጠት እንደታቀደ ገልጸው የኒጀር ግዛት አፈ ጉባኤ እነዚህን ጥረቶች ለማደናቀፍ ቢሞክሩ “በእሱ እና በሴቶች ሚኒስቴር መካከል ከባድ የህግ ጦርነት ይፈጠራል” ሲሉ አጽንኦት ሰጥተዋል።

የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ከፍተኛ ረዳት አቢዮዲን ኢሴይት የሚኒስትሯን ሃሳብ ያጠናከረ መግለጫ ሰጥተዋል።

“ለሁሉም ባለድርሻ አካላት የማቀርበው ጥሪ በኢኮኖሚ አቅመ ደካሞችን የሚበዘብዙ፣ ድህነትን የሚያባብሱ እና ከአረንቋ የማያወጡ፣ ድንቁርናን የሚያስፋፉ ፖሊሲዎችን እና ፕሮግራሞችን ተግባራዊ ከማድረግ እንዲያቆሙ ነው” ብለዋል።

በናይጄሪያ የሚገኙ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾችም ይህንን የጅምላ ሰርግ ለማስቆም ፊርማ ማሰባሰብ ጀምረዋል።

እስከ አርብ ምሽት ድረስ 10 ሺህ 500 ፊርማዎች ማሰባሰብ ተችሏል።

የህጻናትን ጋብቻ ለመከላከል ዘመቻ እያደረጉ ያሉ አለም አቀፍ አካላት መረጃ ከሆነ በናይጄሪያ 30 በመቶ የሚሆኑ ሴቶች እና 1.6 በመቶ የሚሆኑ ወንዶች 18 ዓመት ሳይሞላቸው ይዳራሉ።

ከነዚህም ውስጥ 12 በመቶ የሚሆኑት 15 ዓመት ሳይሞላቸው እንደሆነ መረጃዎች ያሳያሉ።

በድህረ ገጻችን ኢትዮ አማዞን በመግባት የሚፈልጉትን እቃ ማዘዝ  ብቻ  ሳይሆን የርስዎንም እቃዎች መሸጥ እንደሚችሉ ስናሳውቅዎት በደስታ ነው ። ለማስታወቂያ ወይንም ለመግቢያ ምንም ክፍያ አይጠበቅብዎትም፤  ለተጨማሪ መረጃ   ድህረ ገጻችንን ይጎብኙ። https://ethio-amazon.com/

ለበለጠ መረጃ ሊንኩን በመንካት የቴሌግራም ግሩፓችንን ይቀላቀሉ!https://t.me/ethioamazon

ምንጭ፡- (ቢቢሲ )

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Cart

Your Cart is Empty

Back To Shop