“ … ‘ ልጄ በአጋቾች እየተሰቃየች ነው። ገንዘብ ካላክሽ ልጅሽን እንገድላታለን ’ አሉኝ። አጋቾቹ 300 ሺሕ ብር ጠየቁኝ ” – እንባ የሚተናነቃቸው እናት Leave a comment

የ20 ዓመት ሴት ልጃቸው በሳዑዲ አረቢያ እና የመን ድንበር በደላሎች እንደታገተችባቸው፣ አጋቾቹ የጠየቁት ገንዘብ ሰሞኑን ካልተላከላቸው እንደሚገድሏት ማስጠንቀቂያ መስጠታቸውን፣ አጋቾቹ ይህን ያሉት ከአንድ ቀን በፊት መሆኑን የታጋቿ እናት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

እያለቀሱ ቃላቸውን የሰጡት እኚሁ እናት፣ “ ‘ልጄ በአጋቾች እየተሰቃየች ነው። ገንዘብ ካላክሽ ልጅሽን እንገድላታለን’ አሉኝ። አጋቾቹ 300 ሺሕ ብር ጠየቁኝ። ይህን ገንዘብ ለመላክ አቅሙ የለኝም። እባካችሁ ወገኖቼ ልጄን አድኑልኝ ” ሲሉ በውስጥም በውጪም ላሉ ወገኖች የእርዳታ ጥሪ አቅርበዋል።

አክለውም፣ “ ልጄም ‘እማዬ ገንዘቡን ካላክሽ ይገድሉኛልና እባክሽ ከዚህ ጉድ አውጪኝ’ አለችኝ። አጋቾቹም ‘ልጅሽ ያለችው በሳዑዲና የመን ድንበር ራጎ ነው’ የልጅሽን ደህንነት የምትፈልጊ ከሆነ ገንዘቡን ላኪ’ ብለው ስልኩን ዘጉት። ልጄን በሕይወት ላጣት ነው። እባካችሁ ወገን ድረሱልኝ ” ሲሉ ተማጸነዋል።

ልጃቸው ይህ ችግር የገጠማት ሕይወቷን ለመለወጥ ወደ ሳዑዲ አረቢያ #እየተሰደደች በነበረበት ወቅት መሆኑን ገለጸው፣ “ የቀን ሥራ እየሰራሁ ነው ያስተማርኳት። የልጄ ደህንነት አስጨንቆኛል። ወላጆች፣ እህት ወንድም ያላች ሁሉ፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ ሆይ እጃችሁን ዘርጉልኝ ” ሲሉ ተማጽነዋል።

የወጣቷን ቤተሰብ መርዳት ለምትፈልጉ በታጋቿ ወንድም መስፍን መኮንን ባዬ ንግድ ባንክ አካውንት 1000264883893 ዳግፋችሁን መላክ ትችላላችሁ።

የታጋቿ ቤተሰብ በስልክ ማነጋገር ለምትፈልጉ በ0945592726 ፍቅር ምስጋንን ማግኘት ይቻላል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ፥ ስለጉዳዩ ያነጋገራቸው አንድ ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ ወደ ሳዑዲ የሚሄዱ ኢትዮጵያዊያንን ደህንነት በተመለከተ በሳዑዲ አስተባባሪ በሰጡት ቃል ፣ “ራጎ ረግረጋማና ከባድ ምሽግ ነው። ደላሎች ተጓዦችን አግተው ከ250 ሺሕ ብር ጀምሮ ይጠይቃሉ ” ብለዋል።

እኝሁ አካል አክለውም ፣ #በርካታ_ኢትዮጵዊያን ስደተኞች “ #ራጎ ” በሌሎች አካባቢዎች በስቃይ እንደሚገኙ፣ ወጣቱ  ከእነዚህ ወገኖች ትሞህርት ወስዶ በእንዲህ አይነት መንገድ ወደ ሳዑዲ አረቢያ ከመሰደድ እንዲቆጠብ አስገንዝበዋል።

በድህረ ገጻችን ኢትዮ አማዞን በመግባት የሚፈልጉትን እቃ ማዘዝ  ብቻ  ሳይሆን የርስዎንም እቃዎች መሸጥ እንደሚችሉ ስናሳውቅዎት በደስታ ነው ። ለማስታወቂያ ወይንም ለመግቢያ ምንም ክፍያ አይጠበቅብዎትም፤  ለተጨማሪ መረጃ   ድህረ ገጻችንን ይጎብኙ። https://ethio-amazon.com/

ለበለጠ መረጃ ሊንኩን በመንካት የቴሌግራም ግሩፓችንን ይቀላቀሉ!https://t.me/ethioamazon

ምንጭ ፡-(@tikvahethiopia)

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Cart

Your Cart is Empty

Back To Shop