በእስረኞች ልውውጥ ከሩሲያ የተለቀቁት ሰዎች ፑቲንን ይቅርታ እንደማይጠይቁ ገለጹ……. Leave a comment

ባለፈው ሳምንት በተደረገ የእስረኞች ልውውጥ ከሩሲያ ነጻ የወጡ ሁለት የሩሲያ የዘር ሐረግ ያላቸው ግለሰቦች፣ ከሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ይቅርታ እንዲያገኙ የሚያስችል ደብዳቤ ላይ እንደማይፈርሙ አስታወቁ።

በዚህ ደብዳቤ ላይ መፈረም ከማረሚያ ቤት አስተዳደር የወጣ አሠራር ነው።

ጀርመን ውስጥ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ቭላድሚር ካራ-ሙርዛ እና ኢልያ ያሺን የተባሉት ግለሰቦች ጥፋተኛ ነን ብለው እንደማያምኑ አስታውቀዋል።

የሩሲያ ባለሥልጣናት አንድ ቀን ወደ አገራቸው እንዲመልሷቸው ፈቃድ እንደማይሰጡም ተናግረዋል።

ካራ-ሙዛ የእስረኞች ለውውጡ “16 ሕይወት አድኗል” ብሏል። ከእስር ባይለቀቅ ኖሮ እዛው እስር ቤት እያለ ይሞት እንደነበር ተናግሯል።

ብዙ ሩሲያውያን “የፑቲንን የዩክሬን ጦርነት” ይቃወማሉ ብሏል።

አጠቃላይ የእስረኞች ልውውጥ የተደረገው ለ26 ሰዎች ነው። እስረኞቹ ከአሜሪካ፣ ጀርመን፣ ፖላንድ፣ ስሎቬንያ፣ ኖርዌይ፣ ሩሲያ እና ቤላሩስ ናቸው።

ሦስት አሜሪካውያን ከሩሲያ ተለቀው አሜሪካ የገቡ ሲሆን፣ ከሦስቱ አንደኛው የዋል ስትሪት ጆርናል ጋዜጠኛ ኢቫን ግሪሽኮቪች ነው።

ነጻ ከወጡ መካከል የቀድሞው የአሜሪካ ባሕር ኃይል ፓል ዌን ይገኝበታል።

ሩሲያ ካስለቀቀቻቸው መካከል ቫዲም ክራስኮቭ ይገኝበታል።

በጀርመን፣ በርሊን ፓርክ ውስጥ ግድያ በመፈፀም የዕድሜ ልክ እስራት ተፈርዶበት የነበረ ሲሆን፣ አሁን ወደ ሩሲያ ተመልሷል።

ከእስር የተለቀቀው ክራስኮቭ የሩሲያ ደኅንነት ሠራተኛ ሲሆን የቀድሞ የቸቸን አማጺያን ኮማንደርን እንዲሁም ለስሎቬንያ በመሰለል ጥፋተኛ የተባሉ ሩሲያውያን ጥንዶችን በመግደል ነበር ጀርመን ውስጥ ታስሮ የነበረው።

ካራ-ሙዛ እና ያሺን ከሦስተኛው አጋራቸው አንድሪ ፒቮቫሮቭ ጋር በመሆን “ነጻ” ሩሲያን ለመገንባትና የፖለቲካ እስረኞች ለማስፈታት ትግላቸውን እንደሚቀጥሉ አስታውቀዋል።

ያሺን በእስረኛ ልውውጡ “ሁለት የሚቃረኑ ስሜቶች” አሉኝ ብሏል።

ነጻ በመውጣቱ ደስተኛ ቢሆንም ወደ አገሩ መመለስ ይፈልጋል።

ፑቲን “ከአገር የተሰደደ ተቃዋሚ ቢኖረው ይሻለዋል። ምክንያቱም በእስር ያለ ተቃዋሚ ከተሰደደ ተቃዋሚ የበለጠ ተደማጭነት አለው” ሲል ለቢቢሲ ገልጿል።

ራሱን ከሩሲያ ውጭ ሲኖር አስቦት እንደማያውቅ ይናገራል።

ነጻ እንዲወጣ ያደረጉትን ሰዎች አመስግኖ ጀርመን ውስጥ ግን “እንግዳ ነኝ። ግቤ ሩስያ መመለስ ነው” ብሏል።ኢልያ ያሺንወደ ሩስያ ቢመለስ ሌሎች እስረኞችን በእስረኛ ልውውጥ ለማስለቀቅ ከባድ እንደሚሆንና ጀርመንን የፖለቲካ አጣብቂኝ ውስጥ እንደሚከት ያምናል።

የሩሲያ የመብት ተሟጋቾች በመቶዎች የሚቆጠሩ እስረኞች እንዳሉ ይናገራሉ።

ሌላው ከእስር ነጻ የወጣው ፒቮቫሮቭ የእስረኞች ለውውጡ “የብርሃን ጭላንጭል ነው” ብሏል።

ካራ-ሙርዛ ሩሲያዊና እንግሊዛዊ ሲሆን፣ ለ10 ወራት ለብቻው ታስሮ እንደነበር ተናግሯል።

ለሁለት ዓመት ተኩል ሲታሰር ባለቤቱን በስልክ ያነጋገራት አንዴ ብቻ እንደሆነም ገልጿል።

“ባለቤቴን ደግሜ አያታለሁ ብዬ አላሰብኩም። ቤተሰቤን አያለሁ ብዬ አላሰብኩም። ፊልም ውስጥ እንዳለው ነው እየተሰማኝ ያለው” ብሏል።

ከሩሲያ ለመውጣት አውሮፕላን ውስጥ ሳለ አንድ የመንግሥት ባለሥልጣን አገርህን የምታያት ለመጨረሻ ጊዜ ነው እንዳለው ተናግሯል።

እሱ ግን “ወደ አገሬ እንደምመለስ አውቃለሁ” ብሏል።

ከሩሲያ ከተለቀቁት መካከል አርቲስቷ ሳሻ ስኮቺሌንኮ ትገኝበታለች። አንድ ቀን እገደላለሁ ብላ ታስብ እንደነበር ለቢቢሲ ገልጻለች።

አሁን ነጻ ሴት መሆኗ እንዳስደሰታትና እንዳስደነገጣትም ተናግራለች።

“በጣም ደስ ብሎኛል። በጣም ዕድለኛ ነኝ። ከምወደው ቤተሰቤ ጋር ተቀላቅያለሁ። ከእጮኛዬ ጋር ተገናኝቻለሁ። እንጋባለን። ወደ ጀርመንም እንሄዳለን። በሕይወቴ ደስ ያለኝ ቀን ዛሬ ነው” ብላለች።

ዋነኛ የፑቲን ተቃዋሚ የነበረው አሌክሲ ናቫልኒ በእስረኞች ልውውጡ ሊካተት እንደነበር ዋይት ሀውስ አስታውቋል።

ናቫልኒ ከወራት በፊት እስር ቤት ሳለ መሞቱ ይታወሳል።

ያሺን “የናቫልኒ መሞት የፑቲን ወንጀል ነው። ለግድያው ኃላፊነቱን ይወስዳል” ብሏል።

ካራ-ሙርዛ በበኩሉ “ሩሲያ እና ፑቲን አንድ አይደሉም። አገሬን እወዳለሁ። ከሙሰኛና የኬጂቢ አምባገነን የተሻለ መሪ ይገባታል። ጤናማ፣ ዘመናዊ፣ ዴሞክራሲያዊ አገር መሆን ትችላለች” ሲል አስተያየቱን ሰጥቷል።

በድህረ ገጻችን ኢትዮ አማዞን በመግባት የሚፈልጉትን እቃ ማዘዝ  ብቻ  ሳይሆን የርስዎንም እቃዎች መሸጥ እንደሚችሉ ስናሳውቅዎት በደስታ ነው ። ለማስታወቂያ ወይንም ለመግቢያ ምንም ክፍያ አይጠበቅብዎትም፤  ለተጨማሪ መረጃ   ድህረ ገጻችንን ይጎብ/ኙ። https://ethio-amazon.com/

ለበለጠ መረጃ ሊንኩን በመንካት የቴሌግራም ግሩፓችንን ይቀላቀሉ!https://t.me/ethioamazon

ምንጭ፡– (ቢቢሲ)

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Cart

Your Cart is Empty

Back To Shop